በዋልድባ ገዳም መነኮሳት እየታደኑ እንደሆነ ተገለፀ

Image
Photo from:-diaspora-newcitizens.nationbuilder.com

አንድ ስማቸዉ እንዳይገለፅ ለኢሳት የገለፁ መነኩሴ እንደተናገሩት መንግስት ለህዝብ ተቃዉሞ ጀሮ ዳባ ልበስ በማለት የገዳሙን አካባቢ ማረስ መጀመሩን የተቃወሙ አምስት መነኮሳት  በፌደራል ፖሊስ ተይዘዉ ታስረዋል፡፡ ሶስቱ መነኮሳት ማይፀበርዩ አካባበቢ ተወስደዉ መታሰራቸዉን የገለፁት አባት ሁለቱ ግን አድርቃይ መታሰራቸዉን እንደሚያዉቁ ተናግረዋል፡፡

ጨሞ-በር እና አጣላ በሚባሉ አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች የመነኮሳቱን መታሰር በማስመልከት የተቃዉሞ ሰልፍ ቢያደርጉም በፖሊስ እንዲበተን ተደርጓል፡፡

የመንግስት ባለስልጣናት ህብረተሰቡ የእርሻ ስራዉ በገዳሙ ላይ ምንም ችግር እንደማያመጣ ተረድቶ ተቃዉሞዉን አቁሟል ብለዉ አየተናገሩ ነዉ፡፡ ይህ እዉነቱን ነዉ ወይ….ተብሎ ለቀረበላቸዉ ጥያቄ መነኩሴዉ በፍፁም ሀሰት ነዉ ብለዋል፡፡  መንግስት የእርሻ ስራዉ ገዳሙን አይነካም በማለት የሚያካሂደዉ ቅስቀሳ የተሳሳተ ና ህዝቡን ለማደናገር ተብሎ የሚነገር መሆኑን መነኩሴዉ ያጋልጣሉ፡፡

የዋልድባ ገዳም መነኮሳት ለህይወታቸዉ ዋስትና እያጡ መምጣታቸዉንም መነኩሴዉ ጨምረዉ ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፡- ኢሳት ሬድዮ

One comment

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s