ያረጀ ያፈጀዉ የአንባገነኖች የነፃዉን ፕሬስ እና ሰላማዊዉን የፖለቲካ ተቃዉሞ ማፈኛ ስልት ፤ ሽብርተኛ እና ሁከት ፈጣሪ

እስክንድር ነጋና የሙያ አጋሮቹ ምን ቢያደርጉ ነዉ ወደ እስር ቤት የተወረወሩት ? መቸም በዚህ የመረጃ ዘመን ተቀምጠህ አገር ለማሸበር ሞክረዉ እንደማትል እርግጠኛ ነኝ፡፡ ይህ ሰንካላ ያረጀና ያፈጀ ምክንያት አንባገነኑ የመለስ መንግስት የነፃዉን ፕሬስ እና ሰላማዊዉን የፖለቲካ ተቃዉሞ ለማፈን የሚደሰኩረዉ ተራ ድስኩር ነዉ፡፡ ይልቁንም  በወገናቸዉ ላይ ይፈፀም የነበረዉን በደል በግልፅ በመቃወማቸዉና ለፍትህና ዲሞክራሲ በመከራከራቸዉ እንዲሁም አንባገነኖቹን እባካችሁ አደብ ግዙ በማለታቸዉ ነዉ እንደምትል አልጠራጠርም፡፡ ዛሬ እነዚህ ንፁሐን ለበጎ ስራቸዉ መመስገን ሲገባቸዉ እነሱ ግን በድቅድቅ ጨለማ ክፍል ዉስጥ ባሰቃቂ ሁኔታ ተቆልፎባቸዉ የአንባገነኖች ዕቃ ዕቃ መጫወቻ ሆነዋል ፡፡

አንባገነኖች ግፋቸዉ ለብዙሀን ጀሮ እንዳይደርስ በንፁሐን ላይ የሚፈፅሙት ይህ ግፍ በአገራችን ኢትዮጵያ ለዘመናት ሲፈፀም የኖረ ሲሆን ፤ እንደነእስክንድር ነጋ ሁሉ ብዙ ኢትዮጵያዉያን የአሸባሪነት ስም እየተለጠፈባቸዉ ለእስርና እንግልት ተዳርገዋል ሲልም የሞትን ፅዋ ተጎንጭተዋል፡፡ ምንም እንኳን ዛሬ አቶ መለስና ጀሌወቻቸዉ ደጋግመዉ አሸባሪ ይበሉ እንጅ እነርሱም የመጡት እንደነ እስክንድር ነጋ ባሉ ቅንና ለእዉነት በቆሙ ኢትዮያዉያን መስዋትነት ነዉ፡፡

ከዚህ በታች የምታዩት ምስል (የፖሊስና እርምጃዉ ጋዜጣ 1965 እትም) እንደሚያሳየዉ ሽብር ነፃዉን ፕሬስና ሰላማዊዉን የፖለቲካ ተቃዉሞ ለማፈን አንባገነኖች ትናንት ሲጠቀሙበት የነበር ዛሬም እየተጠቀሙበት ያለ የሐሰት ካባ ሲሆን ፤ እንዴዉም ዛሬ በነአቶ መለስ መንግስት በደንብ ተቀነባብሮ የህግ ማዕቀፍ ወጦለት ህጋዊ ሽፋን ተሰጦት ይገኛል፡፡ እስቲ ልብ ብላችሁ ጋዜጣዉን ተመልከቱት ፤ በዋልልኝ መኮንን ፣ ጌታቸዉ ሻራዉ ፣ ገዛኸኝ መኮንን ፣ አያሌዉ አክሊሉ እና  ፋንታሁን ጥሩነህ ላይ የተፈፀመዉ ዛሬ በነእስክንድር ነጋ ላይ ከተፈፀመዉ በምን ይለያል ? በምንም!! እንዲያዉም የጋዜጣዉና የሰወቹ ስም ካልተለየ በስተቀር አጠቃላይ ፅሑፉ ቁርጥ ዛሬ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ እነእስክንድር ነጋን በተመለከተ የምናነባቸዉን ፅሁፎች ይመስላል ልትሉ ትችላላችሁ፡፡

Image 

የሚያሳዝነዉ እነእስክንድር የተከራከሩለትና የደሙለት ህዝብ  የሚፈፀምባቸዉን የጭካኔ ተግባር  በዝምታ መመልከቱ ሲሆን ፤ ይህ ዝምታ አንባገነኖቹን የልብ ልብ እንዲሰማቸዉ እያደረገ ይገኛል ፤ ነገ ከነገ ወዲያ እንደተመስገን ያሉ ብቸኛ የሀገሪቱ ነፃ ጋዜጠኖችን እንድናጣቸዉም ያደርገናል፡፡

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s