መንግስት በሙስሊም ተቃዋሚዎች ላይ የሐይል እርምጃ መዉሰድ ከመጀመሩ ጋር በተያያዘ ዉጥረቱ ጨምሯል ፤ ሁሉን አቀፍ ህዝባዊ ተቃዉሞ በመንግስት ላይ ሊነሳ ይችላል

Image
Photo from:-http://ethiomuslimsmedia.com

የእስልምና እምነት ተከታዮች የሚመሯቸውን የሀይማኖት አባቶች ከመምረጥና ከእምነታችን አስተምህሮት ውጪ የሚሰብክ መጤ እስላማዊ እምነት በመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣኖችና ካድሬዎች ማስፈራሪያ እንድንቀበል ጫና እየተደረገብን ነው ሲሉ የሚያካሂዱት የተቃዉሞ እንቅስቃሴ ከዕለት ወደ ዕለት አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሰ ሲሆን ፤ በትናንትናዉ እለት ማለትም በ6/11/2004 መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ በወሰደዉ እርምጃ የ4 ሰዎች ህይወት ሊያልፍ ችሏል፡፡ 

በቦታዉ የተገኙ አንድ አንድ ሰዎች እንደገለፁት በከፍተኛ ደረጃ የታጠቁ የመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ጉለሌ አካባቢ ወደ  ሚገኘው አወሊያ መስጂድ ዘልቆ በመግባት እሁድ በ8/11/2004 ሊካሄድ ለታሰበዉ የአንድነትና የሰዶቃ ፕሮግራም የተዘጋጀዉን ዳስ በጉልበት በማፈራረስ ሸራዎቹን ሰብስበዉ ወስደዋል፡፡ ለፕሮግራሙ ታስበዉ የተገዙ በሬዎችንም ከመስጅዱ በማዉጣት ወስደዋል፡፡ ይህንንም ለምን ሲሉ ለመቃወም በሞከሩ የእምነቱ ተከታዮች ላይ በከፈቱት የተኩስ እሩምታ 4 ሰዎችን የገደሉ ሲሆን ብዙ ሰዎችንም እስኪበቃቸዉ ወደ እስር ቤት አጉዘዋል፡፡ 

ሳምንታዊውን የአርብ ሶላት የፀሎት ሥነ-ሥርዓት ተከትሎ አወሊያና አንዋር መስጊድ የሚሰባሰበው የእምነቱ ተከታይ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉን እያለ በሰላማዊ መንገድ የሚያሰማው የአቤቱታ ድምፅ ወደ ሌሎችም አካባቢዎችና መስጊዶች በመዛመት ላይ ሲሆን ፤ አገሪቱን በተለይም የአዲስ አበባ ከተማን ዉጥረት ላይ ጥሎ ይገኛል፡፡ ይህንን ሰላማዊ ተቃዉሞ ሠላማዊ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ ሀይልንና አፈናን እንደ አማራጭ የወሰደዉ አንባገነኑ የመለስ መንግስት እየወሰደ ባለዉ እርምጃ ህዝበ ሙስሊሙ ቁጣዉ የበለጠ እያለ የመጣ ሲሆን ፤ የስራ ማቆም አድማ ለማድረግ ወስነዋል፡፡ 

በአሁኑ ሰዓት የእሁዱን ፕሮግራም ለማሰናከል ሲባል አወሊያ መስጊድ በታጠቁ የመንግስት ሀይሎች የተከበበ ሲሆን ፤  የከተማዋ መብራትም ሆን ተብሎ መጥፋት ጀምሯል፡፡ ሆኖም ሙስሊሙ የህብረተሰብ ክፍል በአንዋር መስጊድ ተሰባስቦ ተቃዉሞ ማሰማቱን ቀጥሏል ፤ በመስጊዱ ቅጥር ግቢ ዉስጥ በማደርም የነገዉን ፕሮግራም በዚያዉ ያካሂዳሉ ተብሎ ይጠበቃል ፡፡ 

ብዙ ሰዎች እንደሚናገሩት ከቅርብ ግዜ ወዲህ በሀገቱ ዉስጥ የኑሮ ዉድነትና ከተለያዩ ኢ-ፍሀዊ የመንግስት እርምጃወች ጋር በተያያዘ የህዝቡ ብሶት ከምን ግዜዉም በላይ ጨምሯል፡፡ ሆኖም ግን አምባገነኑ መንግስት በሚወስደዉ የተጠናከረ የአፈና እርምጃ ምክንያት ህዝቡ ለግዜዉም ቢሆን ዝም ለማለት ተገዷል፡፡ ይህ በሆነበት ሁኔታ ዛሬ እየተጠናከረ የመጣዉ የሙስሊሞች ተቃዉሞ ለመላዉ የኢትዮይያ ህዝብ የልብ ልብ እንዲሰማዉ የሚያደርግ ሲሆን ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ተቃዉሞ በሀገሪቱ እንዲነሳም በር ይከፍታል፡፡

 

2 comments

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s