የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ደህንነት አደጋ ላይ እየወደቀ ነዉ

እንደሚታወቀዉ አንባገነኑ የኢትዮጵያ መንግስት ከቅርብ ግዜ ወዲህ በነፃዉ ፕረስ ጋዜጠኞች ላይ ግልፅ ጦርነት ከፍቷል፡፡ በተለይም የሀገርንና የህዝብን ደህንነት መጠበቅ በሚል ሰበብ የፀረ ሽብር ህግ ካፀደቀበት ግዜ ጀምሮ ህገ መንግስቱን ፍፁም በተቃረነ መልኩ ለህዝብ ታማኝ የመረጃ ምንጭ በሆኑት ጋዜጠኞችና የድህረ-ገፅ ፀሐፊዎች (Bloggers) ላይ አሸባሪ ፣ ሁከት ፈጣሪ ፣ ነጭ ለባሽ … የሚል ሰንካላ ስም እየለጠፈ ብዙዎችን ወደ ማጎሪያዎቹ  መወርወር ችሏል ፣ ብዙዎችንም የሚወዷትን አገራቸዉን ጥለዉ እንዲሰደዱ አድርጓል፡፡ እዚህ ላይ በ2004 የአመቱን አለም አቀፍ የፕረስ ነፃት ሽልማት በማግኘት የሀገሩን ስም በጋዜጠኝነት የሙያ መስክ ማስጠራት በቻለዉ በተወዳጁ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ፈገግ እያደረጉ በሚያስተምሩ ፅሑፎቹ በሚታወቀዉ ጋዜጠኛ አቤ ቶኪቻዉ ላይ የደረሰዉ  እንደ ምሳሌ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

መንግስት አሁንም ይህንን እርምጃዉን በቀሩት ጥቂት የነፃዉ ፕሬስ ጋዜጠኞችና የድህረ-ገፅ ፀሐፊዎች ላይ ይበልጥ አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ፤ ሁሉም በሐሰት ዉንጀላ የመታሰር እና ከዛም የከፋ አደጋ ከፊታቸዉ ተጋርጦባቸዉ ይገኛል፡፡  

Image
የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ

ከነዚህ አደጋ አንዣቦባቸዉ ከሚገኙ ጋዜጠኞች መካከል የተወዳጇየፍትህ ጋዜጣ ባልደረቦች ተጠቃሾች ሲሆኑ ፤ የጋዜጣዋ ዋና አዘጋጅ እና “አንድ በሉ” በሚለዉ አምዱ ስር በሚፅፋቸዉ ተነበዉ በማይጠገቡ ፅሑፎቹና ከዲሞክራሲ ፣ ነፃነት እና ፍትህ ጋር በተያያዘ በመንግስት ላይ በሚሰነዝራቸዉ የሰሉ ትችቶቹ የሚታወቀዉ ወጣት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዋናዉ ነዉ፡፡

ጋዜጠኛ ተመስገን ለሙያዉና ለህዝቡ ባለዉ ልዩ ፍቅር ምክንያት ለበርካታ የመንግስት የሐሰት ክሶች እና በተደጋጋሚ ለሚደርሱበት የደህንነት ሰራተኞች ማስፈራሪያ ሳይንበረከክ ስራዉን በቆራጥነትና በፅናት መቀጠል የቻለ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የጋዜጠኛዉ ደህንነት ቀስ በቀስ ወደ ከፋ ደረጃ የደረሰ ይመስላል፡፡ በተለይም በቅርቡ አልሻባብ ተብሎ ከሚጠራዉ የአሸባሪ ቡድን የተላኩ በማስመሰል ወደ ፍትህ ጋዜጣ ኢሜል ኢምቦክስ በጋዜጠኛዉ ስም እንዲገቡ የሚደረጉ የሐሰት መልዕክቶች የአይበገሬዉን ጋዜጠኛ ደህንነት ስጋት ላይ ጥለዋል ፤ የተወዳጇን ጋዜጣ የወደፊት ህልዉናም ጥያቄ ዉስጥ ከትቷል ፡፡

እነዚህ የኢሜል መልዕክቶች ተመስገንን (ፍትህ ጋዜጣንም ይጨምራል) ከአልሻባብ ጋር ጥብቅ ግንኙነት እንዳለዉ ለማስመሰል በአምባገነኑ የወያኔ መንግስት እየተደረጉ ያሉ ሙከራዎች ሲሆኑ ፤ ለከባድ ዉንጀላ እያሰናዱት ስለመሆኑ የማያሻሙ ማስረጃወች ናቸዉ፡፡ 

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡   

ወደ ፍትህ ጋዜጣ ኢሜል ኢምቦክስ በጋዜጠኛዉ ስም እንዲገቡ ከተደረጉት የሐሰት የኢሜል መልክቶች መካከል አንዱ እንደሚከተለዉ የሚል ነበር፡-

ሰላም ተመስገን!

ከአልሸባብልዑክጋርችግር ውስጥባትገባየተሻለነውምንአልባት ያልተፈታችግርካለለሚመለከተው ክፍልብትተወውይሻላል።ካንተ የሚጠበቀውበኢትዮጵያመንግሥት እናኢኮኖሚውላይየከፈትከውን የማጥላላትዘመቻመቀጠልብቻነው። ከዚህቀደምከነበረውበበለጠመልኩ በደንብአድርገህእንድትቀጠቅጠው ያስፈልጋል፡፡ ለጀመርከውፕሮፓጋንዳ እቅድናዲዛይኑንበማውጣት እንዲተባበርህናውጤታማእንድትሆን አጋርህንፋሲልየኔአለምልታማክረው ይገባል።አንዳንድጊዜፋሲልንሳታማክር በራስህየምትሰራቸውስራዎችእንዳሉ ተረድተናል።ይሄመልካምናየሚደገፍ ሆኖአላገኘነውም።

 ከአክብሮትጋር

ተወልደኃብቴነጋሽ (ኮሎኔል)

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s