የሙስሊሙ ጥያቄና የመንግስት ምላሽ ፤ ፍየል ወዲህ – ቅዝምዝም ወዲያ

የሀገራችን ህገ-መንግስት አንቀፅ 11 በማያሻማ መንገድ የመንግስትንና የሀይማኖትን ልዩነትና አንዱ በአንዱ ጣልቃ አለመግባት በተመለከተ የሚከተሉትን አስፍሮ ነበር፡፡

1. መንግስትና ሐይማኖት የተለያዩ ናቸዉ፡፡

2. መንግስታዊ ሐይማኖት አይኖርም፡፡

3. መንግስት በሐይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ፤ ሐይማኖትም በመንግስት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፡፡

ሆኖም ከቅርብ ግዜ ወዲህ አንባገነኑ የመለስ መንግስት ይህን የህገ-መንግስት አንቀፅ በመተላለፍ የተለመደዉን እርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማትረፍ ሲል ብቻ በሀይማኖት ዉስጥ መፈትፈት መጀመሩ የአደባባይ ሚስጥር ነዉ፡፡ በተለይም ከቅርብ ግዜ ወዲህ ከእምነት ተቋምትና ተከታዮች ጋር እየፈጠረ ያለዉ እሰጣ-ገባ የዚህ የጣልቃ ገብነቱ አይነተኛ ማሳያ ነዉ፡፡

እዚህ ላይ በጣም የሚያሳዝነዉ ጣልቃ ገብነቱ እንዳለ ሆኖ ለምን የሚሉ የእምነቱ መሪወችንና ተከታዮች ላይ አሸባሪና የመሳሰሉ ስሞችን እየለጠፈ ማሳደድ መጀመሩ ነዉ፡፡ ለምሳሌ ያህል በአሁኑ ሰዓት እየተካሄደ ያለዉን የሙስሊሞች ተቃዉሞ እየመራ ባለዉ  ኮሚቴ ላይ እየተፈፀመ  ያለዉን አሳፋሪ ወንጀል መጥቀስ ይቻላል፡፡

ይህ ኮሚቴ ከ500000 በላይ የሚሆን ህዝብ በፊርማዉ ትወክሉናላችሁና ጥያቄያችንን ለመንግስት አቅርቡልን ተብሎ የተወከለ ቢሆንም በአሸባሪነት የስም ካባ አንባገነኖች ህገ-ወጥ አፈናና ሽብር እየፈፀሙበት ይገኛል፡፡ እስቲ ይታያችሁ እንዴት ብሎ ነዉ 500000 ኢትዮጵያዊ ለአሸባሪ ቡድን በፍቃደኝነት ፊርማዉን ተወክሉናላችሁ ብሎ የሚያኖረዉ ? ነዉ ወይስ የኢትዮጵያ ህዝብ ክፉና በጎን መለየት አይችልም ? ያን ያህል ህዝብስ እንደጉንዳን አወሊያንና አንዋር መስጊድን ወሮ “አላህ ዋአክብር” እያለ የሚጮኸዉ ተታሎ ነዉ ?

Image

እዉነቱ ይህ ኮሚቴ ከህብረተሰቡ በወጡና ህብረተሰቡ የተሰጣቸዉን ትልቅ ሀላፊነት መወጣት ይችላሉ ብሎ ባመነባቸዉ ሰዎች የተዋቀረ ሲሆን ፤ እነዚህ አባላቱም ከጅምሩ ጀምሮ የህብረተሰቡን ጥያቄ ለማስመለስ መንግስት እንደሚያወራዉ አፍራሽ ሳይሆን ህጋዊና ገንቢ ሊባል የሚችሉ አካሄዶችን የተከተሉ ናቸዉ፡፡ መንግስት ጥያቄዉን በ6/11/2004 በወሰደዉ አይነት የጉልበት እርምጃ ሳሆን በህጋዊ መንገድ ለመፍታት እንዲሞክር ጥረት ሲያደርጉ ቆይቷል ፤ አሁንም ቢሆን ይህንን ማድረግ ቀጥለዋል፡፡ 

እስቲ ይታያችሁ እነዚህ ሰዎች እኮ የጠየቁት ህጋዊ ጥያቄ ነዉ ፤ ማንም ኢትዮጵያዊ ሊጠይቀዉ ህገ-መንግስቱ የሚፈቅድለት ጥያቄ፡፡ መጅሊሱ ይቀየር ፣ የመጅሊስ ምርጫ በቀበሌ ሳይሆን በሐይማኖት ቦታዎች ይካሄዱ ፣ መጤ ሀይማኖት በግድ ሊጫንብን አይገባም… ማለት በምን መስፈርት ነዉ አሸባሪ የሚያስብለዉ፡፡

ከዚህ በታች ኮሚቴዉ ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር ከተፃፃፋቸዉን ደብዳቤወች መካከል አንዱን የዚህን ኮሚቴ ህጋዊ አካሄድ በተወሰነ መንገድ ሊያሳይ ይችላል በሚል እምነት አቅርቤላችኋለሁ፡፡

Image

 

Image<a

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s