Ethiopia: ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ተከሰሰ

Image
የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ

የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅና “የመለስ አምልኮ” መፅሐፍ ፀሐፊ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፍትህ ጋዜጣ ላይ በወጡ ፅሑፎቹ ክስ ተመስርቶበት  ዛሬ  ማዕከላዊ ምርመራ ጣቢያ ቃሉን እንዲሰጥ ተደርጓል ፤ በቅርቡ ፍርድ ቤት እንደሚቀርብም ታዉቋል፡፡

ጋዜጠኛዉ በፌስ ቡክ ገፁ እንደገለፀዉ ፍትህ ሚኒስትር ክስ መስርቶብሀል ስለዚህ መጥተህ ቃልህን ስጥ ተብሎ በፌደራል ፖሊስ በቀረበለት ጥሪ መሰረት ማዕከላዊ ምርመራ ጣቢያ የቀረበ ሲሆን ፤  በሚያስገርም ሁኔታ የዛሬ አመት  ታትመዉ በተሰራጩ 7 የፍትህ ጋዜጣ እትሞች ላይ በወጡ ፅሑፎች  8 ክሶች እንደተመሰረቱበት ተነግሮት ቃሉን ሰጥቷል፡፡

የዛሬዎቹ መርማሪዎች ከምግዜዉም በላይ በታላቅ ትህትና ተቀብለዉ አሰተናግደዉኛል ያለዉ ጋዜጠኛዉ ቃሉን ሰጥቶ ሲጨርስ ከተለመደዉ አሰራር በተለየ መልኩ ዋስ መጥራት ሳያስፈልገዉ  መለቀቁን አያይዞ ጠቅሷል፡፡

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ባለፉት ጊዜያት 35 ጊዜ ያህል ህዝብን በመንግስት ላይ ማነሳሳት ፣ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ መሞከር…በሚል  ክስ የተመሰረተበት ሲሆን ፤ ይህኛዉ ለ36ኛ ጊዜ ነዉ፡፡ 

እንደሚታወቀዉ ማስፈራሪያ ከመንግስት የደህንነት ሐይሎች በተደጋጋሚ እንደሚሰጠዉ ጋዜጠኛዉ ሲገልፅ የቆየ ሲሆን ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጋዜጠኛዉ ስም አልሻባብ ከተባለ አሸባሪ ቡድን የተላኩ በማስመሰል በኢሜል ሆን ተብለዉ ከሚላኩለት መልዕክቶች ጋር በተያያዘ  ደህንነቱ ይበልጥ አደጋ ላይ መዉደቁ ሲጠቀስ ቆይቷል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s