በኢህአዴግ ዉስጥ የተፈጠረዉ የስልጣን ሽኩቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሕይወት መኖር አለመኖር አጠያያቂ በሆነበት በዚህ ሰዓት በኢህአዴግ ዉስጥ የተፈጠረዉ የስልጣን ሽኩቻ እያደገ መምጣቱንና በተለይም ሰሞኑን አፍለኛ የከተማ ካድሬዎች በበረከት ስምዖን ዙሪያ መሰባሰብ መጀመራቸዉን የኢህአፓ ድምፅ የሆነዉ ፍኖተ ህብረት የተሰኘዉ ሬድዮ ዘግቧል፡፡

በተያያዘም በዘገባዉ እንደተጠቆመዉ የኢህአዴግ የደቡብ ክንፍ የሆነዉ ደኢህዴን ከህወሓት ጋር እየወገነ ሲሆን ብአዴን ግን አሁንም በልዩነቱ ፀንቶ የዉስጥ ለዉስጥ ፍትጊያዉን አፋፍሞ ቀጥሏል፡፡

በቤተ-መንግስት አካባቢ አቶ በረከት ስምዖን እንዲሁም የጤና ጥበቃ ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ቴወድሮስ አድሀኖ እና የመከላካያዉ ኢታማጆር ሹም ሳሞራ የኑስ ብቻ በብዛት እንደሚታዩ የቤተ-መንግስት ምንጮችን ጠቅሶ የዘገበዉ ፍኖተ ህብረት ብዙ ሰዎች አገሪቱ በእነዚህ ሰዎች መዳፍ ስር ናት እያሉ ይገኛል ሲል አትቷል፡፡

አያይዞም የመከላካያዉ ኢታማጆር ሹም ሳሞራ የኑስ ቤተ-መንግስቱን በተጠናከረ ሁኔታ እየጠበቀ ነዉ ያለ ሲሆን ፤ በአሁኑ ሰዓት እየተካሄደ ያለዉን የስልጣን ሽኩቻ ተከትሎ ጀነራሉ አንዳንድ እርምጃዎችንም መዉሰድ ጀምሯል ሲል ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
በተያያዘ ዜና የአገዛዙ የመኮንኖች ኮሌጅ ለ5ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸዉን ከፍተኛ መኮንኖችና የጦር አለቆች ትናንት ነሐሴ 6ቀን ማስመረቁ ታዉቋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ በዚሁ የምረቃ በዓል ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እንደሚገኙ ለተመራቂዎች በተበተኑ በራሪ ወረቀቾች ላይ እንደተጠቀሰ ኢሳት በዚህ ሳምንት መዘገቡ የሚታወስ ነዉ ፤ ሆኖም ግን የተባለዉ በነበር ቀርቶ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በበዓሉ ላይ ሳይገኙ ቀርተዋል፡፡ በምትኩ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ሐይለማሪያም ደሳለኝ በበዓሉ ላይ በመገኘት ተማሪዎች መርቀዋል፡፡

የመንግስት የኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ የሆነዉ አቶ በረከት ስምዖን በመንግስት ስር በሚገኘዉ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እየቀረበ የመለስን በፅኑ መታመም ሆነ መሞት እያስተባበለ ሲሆን ፤ በቅርቡም እንደተለመደዉ ከኢትዮጵያዉያን የዘመን መለወጫ መስከረም በፊት በስራ ገበታቸዉ ይገኛሉ በማለት ተናግሯል፡፡ ሆኖም ግን ጠ/ሚኒስትሩ የት እንደሚገኙ አሁንም ሊገልፅ አልቻለም፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ አቶ ስብሀት ነጋ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕይወት አሉ ወይ ? ተብለዉ ሲጠየቁ ከት ብለዉ የሳቁ ሲሆን ፤ ይህም የነበረከት ስምዖንን መግለጫ ታማኝነት ትልቅ ጥያቄ ዉስጥ ከትቶታል ፤ በተጨማሪም የዉስጥ ሽኩቻዉ እየከረረ መምጣቱን ፍንትዉ አድርጎ አሳይቷል፡፡

የተለያዩ የፖለቲካ ተንታኞች በረከት ስምዖን እንዲህ እያስተባበለ ያለዉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መሞት ይፋ ከመደረጉ ጋር ተያይዞ ሊመጣ የሚችለዉን ሕዝባዊ ተቃዉሞ በመፍራት እና በተፈጠረዉ የዉስጥ የስልጣን ሽኩቻ ምክንያት ጠቅላይ ሚኒስትሩን በሌላ ሰዉ መተካት ስላልቻሉ ነዉ እያሉ ይገኛል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s