አቡነ ጳዉሎስ በጠና ታመዉ የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸዉ ነዉ ተባለ

Imageኢሳት ደጀ-ሰላም የተሰኘ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ትኩረት ሰጥቶ የሚዘግብ ድህረ-ገፅ ጠቅሶ እንደዘገበዉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክና የአለም አቢያተ-ክርስቲያናት ፕሬዝዳንት የሆኑት አብነ ጳዉሎስ በገጠማቸዉ ከባድ የጤና እክል ምክንያት በባልቻ ሆስፒታል ተኝተዉ ከባድ የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸዉ ይገኛሉ አለ፡፡

ከገባ ሳምንት ያስቆጠረዉን የፍልሰታ ማሪያም ፆም ተከትሎ በቅዱሰ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በፀሎተ ቅዳሴ ላይ እንደነበሩ ድህረ ገፁን ጠቅሶ ያተተዉ የኢሳት ዘገባ ትናንት ማለትም ሐምሌ 8/2004 በጠና በመታመማቸዉ ባልቻ ሆስፒታል መግባታቸዉን ገልጧል፡፡

ኢሳት አያይዞም ድህረ-ገፁን በመጥቀስ ፓትርያርኩ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጤንነት ሁኔታቸዉ እየተባባሰ በመምጣቱ ምክንያት ወደ መኪናቸዉ ሲገቡም ሆነ ሲወጡ ከግራና ከቀኝ ሰዎች እየደገፋቸዉ እንደ ነበር ጠቁሟል፡፡

የፓትሪያርኩን ታመዋል መባል ተከትሎ ኢሳት የቅርብ ረዳታቸዉ የሆኑትን አባ እንቁ ባሕሪን በስልክ አነጋግሮ የነበረ ሲሆን ፤ ፓትርያርኩ በጠና ታመዉ ባልቻ ሆስፒታል ተኝተዋል እየተባለ ነዉና በጉዳዩ ላይ ምን ይላሉ ? ተብሎ ለቀረበላቸዉ ጥያቄ “ሐሰት ነዉ ፣ አልታመሙም ፣ ቤት ነዉ ያሉት” ሲሉ አስተባብለዋል፡፡

ካልታመሙ ይህ ወሬ ከየት መጣ ? ተብለዉ ሲጠየቁም ቅዳሜ ቤተክርስቲያን ባለመሄዳቸዉ ነዉ ሲሉ የተናገሩ ሲሆን ፤ ቅዳሜ ለምን አልገቡም ? ተብሎ ለቀረበላቸዉ ጥያቄ “አንድ ጉዳይ ነበራቸዉ…” በማለት መልሰዋል፡፡ ሆኖም ወደ መጨረሻ ባልቻ ሆስፒታል ታይተዋል እየተባለ እኮ ነዉ ተብለዉ ሲጠየቁ “ምናልባት ሰዉ ለመጠየቅ ሄደዉ ሊሆን ይችላል” ሲሉ ተደምጠል፡፡

እኒህ የፓትርያርኩ እረዳት አሁን ፓትርያርኩን ማግኘትና ማነጋገር እንችላለን ወይ ተብለዉ ሲጠየቁ አዎ! ከሰላሳ ደቂቃ በኃላ ደዉሉ ያሉ ሲሆን ፤ ከሰላሳ ደቂቃ በኃላ ሲደወልላቸዉ ግን የተለያ ምክንያቶችን በመደርደር ሊያገናኟቸዉ እንዳልቻሉ ኢሳት ጠቅሷል፡፡

ኢሳት አያይዞ ምንም እንኳን እኒህ አባት የፓትሪያርኩን መታመም ያስተባብሉ እንጅ በሌላ ወገን በኩል ባደረግኩት ጥናት ፓትርያርኩ በጠና መታመማቸዉንና በባልቻ ሆስፒታል በህክምና እርዳታ ላይ እንደሚገኙ አረጋግጫለሁ ሲል ዘግቧል፡፡

ኢሳት ድህረ ገፁን ጠቅሶ እንደዘገበዉ ፓትርያርኩ ለህክምናቸዉ በሳምንት 60 ሺህ ብር እየተከፈለላቸዉ ይገኛል፡፡

  

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s