የብአዴን ከፍተኛ ባለስልጣናት ወደ ዉጭ ሀገራት መሰደድ ጀምረዋል

Imageየጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ከእይታ መሰወር ተከትሎ ትልልቅ የብአዴን ባለስልጣናት ወደ ተለያዩ ሀገራት ጥገኝነት እየጠየቁ መሰደድ መጀመራቸዉን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸዉ ምንጮች ጠቆሙ፡፡

ምንጮቹ የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳዳሪ ፣ የጎንደር ከተማ ከንቲባ እና ሌሎችም ከፍተኛ ባለስልጣናት በቅርቡ ድንገት ብድግ ብለዉ ከሀገር ጠፍተዉ ሄደዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ምንጮቹ አያይዘዉ እንደጠቆሙት እነዚህ የብአዴን ከፍተኛ ባለስልጣናት በከባድ ሙስና ይጠረጠሩ የነበረ ሲሆን ከሀገር ዉጭ ከፍተኛ መጠን ያለዉ ገንዘብ አግዘዋል ይባላሉ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ መሰወር በተለያየ የስልጣን ደረጃ ላይ ባሉ የመንግስት ባለስልጣናት ዘንድ ፍርሀትና ተስፋ መቁረጥ ፈጥሯል ያሉት እነዚህ ታማኝ ምንጮች ብዙ በሙስና የተጨማለቁ ባለስልጣናት አስቀድመዉ የህዝብን  ሀብት ወደ ዉጭ ሀገራት እያጋዙ ነገ ከነገ ወዲያ ለመሰደድ በዝግጅት ላይ ናቸዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አነዚህ ምንጮች ባለስልጣናቱ የሚሸሹት በአገዛዙ ቀጣይነት ላይ ከፍተኛ ጥርጣሬ ስላላቸዉና ከአገዛዙ መዉደቅ ጋር ተያይዞ በፈፀሙት የሙስና ወንጀልና  በህዝቡ ላይ በፈፀሙት ግፍ ከመጠየቅ ለማምለጥ እንዲሁም የመዘበሩትን የህዝብ ሀብት ከመነጠቅ ለማዳን ነዉ ሲሉ አብራርተዋል፡፡ 

እንደሚታወቀዉ የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ የነሐሴ 8/2004 እትም “የአቶ መለስ መታመም ያስደነገጣቸው ሙሰኞች ለማምለጥ እየተሯሯጡ ይሆን?” በሚል አርዕስት ስር  “ስልጣንን መከታ በማድረግ እና ከባለሥልጣን በመጠጋት አላግባብ የሕዝብን ገንዘብና ሀብት በመዝረፍ የበለፀጉ ሙሰኞችና ባንዳዎች የአቶ መለስ መታመም ስለ አስደነገጣቸው ፣ የዘረፉትን ለመደበቅና ለማሸሽ እንዲሁም ራሳቸውን ለማዳን በየአቅጣጫው እየተሯሯጡ ስለሆነ እነዚህ ሰዎች ለፍርድ ሳይቀርቡ እንዳያመልጡ የቻልነውን ያህል ለማድረግ መሞከር ይገባናል” ሲል እዉነቱን አፍረጥርጦ አስነብቦ ነበር፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ኢሳት በቅርቡ ትላልቅ የመንግስት  ባለስልጣናት ከፍተኛ መጠን ያለዉ ገንዘብ ወደ ዉጭ ሀገራት እያሸሹ ነዉ በማለት ዘግቦ የነበረ ሲሆን ፤ አይይዞም በተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ አንዳንድ የኢትዮጵያ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በየሚገኙባቸዉ ሀገራት ጥገኝነት እየጠየቁ በዚያዉ እየቀሩ ነዉ ብሎ ነበር፡፡

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s