የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች በግምገማ ተጠምደዋል

ኢሳት ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበዉ በአንደኛ ደረጃ ተጠንቀቅ ላይ የቆመዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች በከፍተኛ ግምገማ ላይ ሲሆኑ ፤ ግምገማዉም ባለበት በየደረጃዉ ይቀጥላል ብሏል፡፡

ግምገማዉ ከሻለቃ ማዕረግ ጀምሮ እስከ ጀኔራል ማዕረግ ድረስ የሚገኙ የሰራዊቱ አባላትን ያጠቃልላል ያለዉ የኢሳት ዘገባ ግምገማ በሚደረግባቸዉ አካቢዎች የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጥ ተደርጓል ሲል አትቷል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ነፃ የኢትዮጵያ ሰራዊት ንቅናቄ የሚባለዉ ሕቡዕ ድርጅት ለዚህ ግምገማ ምክንያቱ እኔ በሰራዊቱ ዉስጥ እያደረኩት ያለዉ የህዝቡን ጥቅም የማስጠበቅ የቅስቀሳ ስራና ሰራዊቱ ለስርዓቱ ከበርቴ መኮንኖች በሎሌነት ከማይገዛበት ደረጃ ላይ በመድረሱ ሰራዊቱን ለማጥራትና በስብሰባዎች ለመጥመድ የተደረገ ነዉ ሲል አስታዉቋል፡፡

እንደሚታወቀዉ የኢትዮጵያ ነፃ ሰራዊት ንቅናቄ ሰራዊቱ የአገዛዙ መጠቀሚያ እንዳይሆንና ዓላማዉ የህዝብን ደህንነትና ጥቅም ማስጠበቅ ከመሆኑ አንፃር ሁሌም ከህዝቡ ጎን እንዲቆም መጠነ ሰፊ ስራ በሰራዊቱ ዉስጥ እየሰራ ያለ ሕቡዕ ድርጅት ነዉ፡፡

ከግምገማዉ ጋር በተያያዘ አንዳንድ ተጨማሪ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት መንግስት በሰራዊቱ ዉስጥ የተቃዉሞ እንቅስቃሴ ሊያደርጉ ይችላሉ ብሎ ያሰባቸዉን የከፍተኛ መኮንኖች ስም ዝርዝር በሚስጥር የያዘ ሲሆን ፤ በዚህ ግምገማ ከሰራዊቱ አባልነታቸዉ ሊያሰናብቷቸዉ ወይም ሌላም እርምጃ ሊወስዱባቸዉ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡  ከእነዚህ መኮንኖች ዉስጥም ብዙዎቹ የአማራ ክልል ተወላጅ እንደሆኑ መረጃዉ አያይዞ ይጠቁማል፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s