በመተማ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የሚገኙ ወጣቶች ያለምንም ምክንያት ለእስርና ስቃይ ተዳርገናል በማለት እያማረሩ ነዉ

ወጣቶቹ የመተማ ወረዳ የፍትህ አካላት በህገ-ወጥ የሰዎች ዝዉዉር ስራ ላይ ከተሰማሩ ግለሰቦች ጋር ባላቸዉ ጠንካራ የጥቅም ግንኙነት ምክንያት እነርሱን በቁጥጥር ስር እንዲያዉሉ ትዛዝ ከበላይ አካል ሲመጣላቸዉ እነርሱን ወደ ጎን በመተዉ በእነርሱ ስም እኛን “አዘዋዋሪዎች” በማለት ምክንያት እየፈለጉ አስረዉናል ሲሉ እንባ እየተናነቃቸዉ ተናግረዋል፡፡

ምንም እንኳን ሰላማዊና ህግን አክብረን በላባችን ሰርተን የምናድር ብንሆንም በአካባቢዉ የሚገኙ የፍትህ አካላት ያለ አግባብ ሆን ብለዉ ለእስር ዳርገናዉናል የሚሉት እነዚህ ወጣቶች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ከ8 እስከ 9 ወር እንደታሰሩ ገልፀዋል፡፡

ወጣቶቹ ደጋግመን “ወንጀለኛ አይደለንምና ፍቱን ወይም ደግሞ ፍርድ ቤት አቅርቡንና እዉነታዉን አስረድተን ትክክለኛዉን ፍርድ እናግኝ “ ብንልም የሚሰማን ልናገኝ አልቻልንም ያሉ ሲሆን ፤ “የናንተ ጉዳይ የሚታየዉ በክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነዉ ፣ ፋይላችሁን ልከናል ፣ ከላይ መልስ ስላልመጣልን ነዉ…” እያሉ ቀን በመቅጠር እያንገላቱን ይገኛል ብለዋል፡፡

አያይዘዉም “እኛን ያሰራችሁን ጥቅማችሁ እንዳይቀርባችሁ በማሰብ ነዉ እንጅ ወንጀለኞችንማ በደንብ ታዉቋቸዋላችሁ ፤ ግድ የለም! ነገ ከነገ ወዲያ እዉነቱ ይወጣል…” ስንላቸዉ ያስፈራሩናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እነዚህ በፖሊስ ጣቢያዉ በእስር ላይ የሚገኙ በቁጥር ከ15 በላይ የሚሆኑ ከ15-30 የእድሜ ክልል ዉስጥ የሚገኙ ወጣቶች “የመተማ ወጣቶች እሮሮ” በሚል አርዕስት የእትዮጵያ ህዝብ እየተፈፀመባቸዉ ያለዉን አሰቃቂ የሰባዊ መብት ጥሰት እንዲያዉቅ በፃፉት 2 ገፅ ደብዳቤ ያለ ጥፋታቸዉ 45°ሴ በሚደርሰዉ የመተማ ሙቀት በጠባብ ክፍል ዉስጥ ለጤና አስጊ በሆነ ሁኔታ እንደሚቆለፍባቸዉ ተናግረዋል፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ አንዳንድ የመተማ ከተማ ነዋሪዎች እንደተናገሩት ህገ-ወጥ የሰዎች ዝዉዉር ዳጎስ ያለ ትርፍ የሚያስገኝ ስራ በመሆኑ አዘዋዋሪዎቹ ጠረፍ ለሚጠብቁ የፌደራል ፖሊሶች ፣ ለከተማዋ መደበኛ ፖሊሶችና ለሌላም የፍትህ አካላት ከሚያገኙት ትርፍ በፐርሰንት ያስቡላቸዋል፡፡ ስለሆነም ምንም ቢሆን እነርሱን ለሕግ አሳልፈዉ አይሰጡም ፤ ይልቁንም ስራ እንሰራለን ለማለት ያህል አልጋና መኪና በመደለልና በመሳሰሉ ቀላል ስራዎች ላይ የተሰማሩ ታዳጊ ወጣቶችን በማሳደድ ያስራሉ ብለዋል፡፡

“ህብረተሰቡ ማን አዘዋዋሪ እንደሆነ ጠንቅቆ ያዉቃል” ስትል አስተያየቷን የሰጠች አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያላት የመተማ ነዋሪ በበኩሏ “ለግል ጥቅም ሲባል በፍትህ ስም ወጣቱን ማሰርና ማሰቃየት ተገቢ አይደለም” በማለት ተናግራለች፡፡

አያይዛም ህገ-ወጥ የሰዎች ዝዉዉሩን መግታት ካስፈለገ ባዘዋዋሪዎችና በፍትህ አካላት መካከል ያለዉን  ሠንሰለት መበጠስና ትክክለኛ ወንጀለኞችን ለፍርድ ማቅረብ ይገባል ብላለች፡፡

እንደሚታወቀዉ በቅርቡ በባሕር ዳር ዩንቨርስቲ ስር በመተማ-ገላባት በኩል በሚደረገዉ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝዉዉር ላይ ትኩረት አድርጎ የተካሔደ አንድ ጥናት በአካባቢዉ የሚካሄደዉ ህገ-ወጥ የሰወች ዝዉዉር ከቁጥጥር ዉጭ መሆኑን በመጥቀስ አንዳንድ በአካባቢዉ የሚገኙ የፍትህ አካላት በወንጀሉ እጃቸዉ እንዳለበት ጠቁሞ ነበር፡፡

 

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s