በኢትዮጵያ ላይ አስከፊ የድርቅና የርሀብ አደጋ እንዳንዣበበ ኢህአዴግ አመነ

Imageየኢህአፓ ልሳን የሆነዉ ፍኖተ ህብረት ሬድዮ በግብርና ሚኒስትር የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት የምግብ ዋስትና ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑትን  አቶ ምትኩ ካሳን ጠቅሶ በነሐሴ 12/2004 እንደዘገበዉ በኢትዮጵያ የድርቅና የርሀብ አደጋ እንደገና ያንዣበበ ሲሆን ፤ የተረጅዎች ቁጥርም ካለፈዉ ዓመት 16 በመቶ ብልጫ አሳይቷል ሲል ገልጧል፡፡

ፍኖተ ህብረት በዚህ ዘገባዉ እንደገለፀዉ በሚሊየኖች የሚቆጠር ሕዝብ ተጨማሪ 314 ሺህ ሜትሪክ ቶን ምግብ  የሚያስፈልገዉ ሲሆኑ ፤ መንግስት ለጋሽ አገሮችና የተለያዩ ድርጅቶች የእርዳታ እጃቸዉን እንዲዘረጉለት ጠይቋል፡፡ የሚያስፈልገዉ የምግብ አቅርቦትም በገንዘብ ሲተመን  149.4 ሚሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ታዉቋል፡፡

ኢህአዴግ የበልግ ዝናብ መቀነስን ፣ የተዛባ የዝናብ መጠን እና የምግብ ዋጋ መናርን እንደ ዋና ምክንያት ጠቅሷል ያለዉ ይህ የፍኖተ ህብረት ዘገባ ፤ አያይዞም ኢህአዴግ የሀገሪቱን ለም መሬት ለቻይና ፣ ለሕንድና ለአረብ ባላሀብቶች  እየቸበቸበና ምርቱን በአዉሮፓና በአረብ ሀገራት ሱቆች እየደረደረ ኢትዮጵያዉያንን ለልመና መዳረጉ የራሱ ብልሹ አስተዳደርና ፖሊሲ ዉጤት ነዉ ብሏል፡፡

እንደሚታወቀዉ ኢህአዴግ 11 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግቢያለሁ የኢትዮጵያዉያንንም ኑሮ አሻሽያለሁ እያለ ማዉራት ከጀመረ አመታት ቢቆጠሩም ዛሬም በየአመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን የምግብ እርዳታን ይሻሉ ፤ መንግስትም በየጊዜዉ እርዱን ከማለት ሊወጣ አልቻለም፡፡ እንዲያዉም እያየለ የመጣዉ የኑሮ ዉድነትና የምግብ ዋጋ መናር ለብዙዎች ፈታኝ እየሆነ የመጣ ሲሆን ፤ ከቅርብ ግዜ ወዲህ በከተሞች አካባቢ ያለዉን የህብረተሰብ ክፍልም ከፍተኛ ችግር ላይ ጥሎታል፡፡

ብዙዎች እንደሚሉት ለምግብ ዋስትና አለመረጋገጥ ምክንያቱ የኢትዮጵያ ግብርና አሁንም ከባሕላዊ ይዞታዉ ያልተላቀቀና የተፈጥሮ ችሮታን መሰረት ያደረገ መሆኑ ሲሆን ፤ ከዚህም ጋር በተያያዘ ለድርቅና መሰል ተዛማጅ የተፈጥሮ አደጋዎች ተጋላጭ መሆኑ ነዉ፡፡

የ2011 የአለም የምግብ ድርጅት መረጃ እንደሚያመላክተዉ ባለፈዉ ዓመት ብቻ 3.7 ሚሊዮን ኢትዮጵያዉያን አፋጣኝ  የምግብ እርዳታ አስፈልጓቸዉ የነበረ ሲሆን ፤ ከተለያዩ ለጋሽ አገራትና ድርጅቶች በተገኘ የገንዘብ እርዳታ ችግሩ ለጊዜዉም ቢሆን ሊቃለል ችሎ ነበር፡፡   

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s