ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለዩ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን አረጋገጠ

በትረ ያዕቆብ

Imageየኢትዮጵያ ቴሌቭዥን “ላለፉት 21 ዓመታት በከፍተኛ ብስለትና ብቃት ሀገራችንን ሲመሩ የቆዩት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ” በዉጭ ሀገር የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸዉ ከቆዩ በኃላ በ57 ዓመታቸዉ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ ሲል ሲያወዛግብ የነበረዉን የጠቅላይ ሚኒስትሩን መሞት ለህዝብ ይፋ አድርጓል፡፡ አያይዞም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሞት በተመለከተ በተመረጡ ቃላት የተከሸነ ከመንግስት የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ አስተላልፏል፡፡

“ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ከድህነትና ኃላ ቀርነት ለማላቀቅ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ አገልግለዉ ከፍተኛ የለዉጥ ተስፋ ያሳዩትን የክብር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ህልፈተ ሕይወት ስንገልፅ በታላቅ ሀዘን በተሰበረ ልብ ነዉ” ያለዉ የመንግስት ይፋዊ መግለጫ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላለፉት ሁለት ወራት በተደረገላቸዉ ከፍተኛ የህክምና እርዳታ ጥሩ የጤና መሻሻል አሳይተዉ የነበረ ቢሆንም ከትናንት በስቲያ  በተከሰተ ድንገተኛ ኢንፌክሽን ምክንያት ትናንት ከምሽቱ 5 ሰዓት ከ40 ደቂቃ በድንገት አርፈዋል ብሏል፡፡

“ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከምንም በላይ ሀገራዉንና ህዝባቸዉን የሚወዱ ለዚህ ሀገርና ህዝብ የላቀ ራዕይ የነበራቸዉ መሪ ነበሩ” ሲል  ስለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጎ በጎዉን ያተተዉ ይህ የመንግስት ይፋዊ መግለጫ “ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ራዕያቸዉን እዉን ማድረግ የጀመሩና አስተማማኝ ዉጤት ማምጣት የቻለ ድርጅትና መንግስት የገነቡ እንዲሁም ኢትዮጵያ በአለም አደባባይ ከፍ ብላ መጠራት እንድትጀምር ያደረጉ ታላቅና እጅግ አርቆ አሳቢ መሪ ነበሩ” ሲል  አሞካሽቷቸል፡፡

አያይዞም “ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሀገራችን ህገ-መንግስታዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እዲገነባ  ፤ የዜጎች እኩልነትና የዜጎች ዲሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶች ህገ-ምንግስታዊ ዋስትና አግኝተዉ በተግባር ላይ እንዲዉሉ ፤ በሀገራችን መልካም አስተዳደር እንዲሰፍንና በድህነት የሚማስኑ ወገኞችን የንሮ ሁኔታ ለማሻሻል የተስፋ ብርሀን የፈነጠቀ ተግባር  የፈፀሙ ፤ ኢትዮጵያን በአዲስና ጥሩ ዲሞክራሲያዊ መሰረት ላይ ያዋቀሩ ታላቅ መሪ ነበሩ” ሲል አትቷል፡፡

ይህ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን “ሀገራችንን በከፍተኛ ደረጃ ለመለወጥ የሚያስችለዉ የታላቁ የ5 ዓመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መሀንዲስ” ሲል የጠራዉ የመንግስት መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካዉያንም ኩራትና ክብር የነበሩ በአፍሪካ መልካም አስተዳደርና ዲሞክራሲ እንዲያብብ የሰሩ መላዉ ዓለም ብቃታቸዉን የመሰከረላቸዉ  ታላቅ መሪ ነበሩ ሲል ጠቅላይ ሚኒስትሩን አወድሷል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም የመንግስት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን ረፋዱ ላይ ለተለያዩ ሚዲያወች የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሞት ያረዳ ሲሆን ፤ ዛሬ ማለትም ነሐሴ 15/2012 በመላ ሀገሪቱ የሀዘን ቀን ሆኖ እንደሚዉልና ባንዲራም ዝቅ ብሎ እንደሚዉለበለብ አስታዉቋል፡፡ በተያያዘም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሞት ተከትሎ በሀገሪቱ ምንም አይነት የፖሊሲና የስትራቴጅ ለዉጥ አይኖርም ሲል የተናገረ ሲሆን ፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ህገመንግስቱን ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ቦታ ይይዛሉ ብሏል፡፡

እንደሚታወቀዉ ግንቦት 10/2004 በዋሽንግተን ሬገን ሕንፃ ከባድ የሚባል ተቃዉሞ ከገጠማቸዉ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላለፉት 2 ወራት ከአይን ተሰዉረዉ የቆዩ ሲሆን ፤ ይህንን ተከትሎ የተለያዩ ሚዲያዎች ፣ ተቋማት እና ግለሰቦች ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጠና ታመዉ በሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኙ ሲናገሩ የነበረ ሲሆን  ቆይቶም መሞታቸዉን ሲገልፁ ቆይተዋል፡፡ ሆኖም የመንግስት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ ናቸዉ… ወደ ስራቸዉ ይመለሳሉ በማለት ሲያስተባብሉ የቆየ ሲሆን ፤ በቅርቡም ከኢትዮጵያዉያን የዘመን መለወጫ መስከረም በፊት በስራ ገበታቸዉ ላይ ይገኛሉ በማለት ተናግሮ ነበር፡፡ ይህም  ኢትዮጵያዉያን  በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁኔታ ላይ ግራ እንዲጋቡ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

የተለያዩ የፖለቲካ ተንታኞች መንግስት የጠቅላይ ሚኒስትሩን መሞት ሲያስተባብል የቆየዉ ይፋ ከመደረጉ ጋር ተያይዞ ሊመጣ የሚችለዉን ሕዝባዊ ተቃዉሞ በመፍራትና በተፈጠረዉ የዉስጥ የስልጣን ሽኩቻ ምክንያት ጠቅላይ ሚኒስትሩን በሌላ ሰዉ መተካት ስላልቻሉ ነዉ ሲሉ የቆዩ ሲሆን ፤ በርግጥም በፓርቲዉ መንደር መደናገጥ ፣ ዉዥንብርና ሽኩቻ በግልፅ እየተስተዋለ ይገኛል፡፡

Advertisements

One comment

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s