ኢትዮጵያ በቡድን እየተመራች እንደሆነ ታወቀ

Imageኢሳት የዲፕሎማቲክ ምንጮቹን ጠቅሶ ትናንት እንደዘገበዉ የቀድሞዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአሁኑ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር በሆኑት በአቶ ስዩም መስፍን የበላይነት የሚመራ 7 አባላትን ያቀፈ አንድ ቡድን ሀገሪቱን የመምራት ስራ የተረከበ ሲሆን ፤ 4 አባላቱ የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት ናቸዉ፡፡

ምንም እንኳን ሐይለማሪያም ደሳለኝ በግዜያዊነት ጠቅላይ ሚኒስትሩን በመተካት የአመራሩን ቦታ እንደተረከቡ በኢትዮጵያ መንግስት በይፋ ቢገለፅም ሀገሪቱን የመምራት ስልጣን ግን በዚህ ቡድን እጅ ነዉ ሲል ያተተዉ ይህ የኢሳት ዘገባ ቡድኑ የትግራዮች የበላይነት በሰፊዉ የነገሰበት ነዉ ሲል አብራርቷል፡፡

በዚህ የኢሳት ዘገባ እንደተገለፀዉ በአቶ ስዮም መስፍን በሚመራዉ ቡድን ዉስጥ ምክትል የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ብርሀነ ገብረ ክርስቶስ በምክትል ሊቀመንበርነት የተሰየሙ ሲሆን ፤ የመከላከያ ኢታማጆር ሹም የሆነዉ ጀኔራል ሳሞራ የኑስና የሀገሪቱ የፀጥታ መስሪያ ቤት ሀላፊ አቶ ጌታቸዉ አሰፋ በአባልነት ይገኙበታል፡፡ ተያይዞም እንደተጠቆመዉ በቡድኑ ዉስጥ ከብአዴን ፣ ኦህዴድና ዴህዴን አንድ አንድ አባላት ተካተዋል፡፡

ቡድኑ ላዕላይና ታህታይ በሚል መዋቅር የተከፈለ ነዉ ያለዉ የኢሳት ዘገባ ምንም እንኳን በላዕላይ የአመራር መዋቅር ዉስጥ አጋር ድርጅቶች ባይሳተፉም በታችኛዉ መዋቅር ዉስጥ ይገኛሉ ሲል ጠቁሟል፡፡

ዘገባዉ አያይዞ እንደገለፀዉ ስርዓቱ ይህንን የአመራር ቡድን ለመፍጠር የተገደደዉ ምራባዉያኑንም ያስማማዉ በህወሓት ዉስጥ ጭምር በታየዉ የጎላ መከፋፈል ምክንያት ሁሉን የሚያስማማ መሪ መምረጥ አስቸጋሪ ሁኖ በመገኘቱ ነዉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ከታሰቡ ሰዎች መካከል አቶ ስዩም መስፍንን ጨምሮ ዋና ዋና የህወሓት ባለስልጣናት የፓርላማ አባል አለመሆናቸዉ ሌላ እንቅፋት ነበር፡፡

በሌላ የኢሳት ዘገባ እንደተገለፀዉ የአለም አቀፉ የግጭት ተንታኝ ቡድን (ICG) የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ በመስከረም ሊያወጣዉ አስቦት የነበረዉን ሪፖርቱን ያወጣ ሲሆን ፤ በሪፖርቱም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት በምስራቅ አፍሪካ የሚታይ ተፅዕኖ እንደሚፈጥር ጠቁሟል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የህወሓትን የበላይነት በማስፈንና አፈናን በማንገስ ሀገሪቱን በመዳፋቸዉ አስገብተዉ ሲገዙ ነበር ያለዉ ሪፖርቱ የእርሱን ሞት ተከትሎ ህወሓት ብቻዉን የስልጣን ሽግግር ሊያደርግ እንደሆነ አጋልጦል፡፡

አያይዞም አለም አቀፉ ህብረተሰብ ፣ አሜሪካ ፣ እንግሊዝና የአዉሮፓ ህብረት ሽግግሩ ሁሉንም ብሔር ብሔረሰብ ያሳተፈ እንዲሆን ሊንቀሳቀሱ ይገባል ሲል ጥሪ አቅርቧል፡፡

By Betre Yacob

2 comments

  1. «««@»»»፦ እንደዚህ፡የተምታታ፡ሁኔታ፡ተፈጥሮ፡የምክር፡ቤቱም፡ሊወስን፡በማይችልበት፡ወቅት፡ምርጫ፡እንዲደረግና፡መሪውን፡ ሕዝብ፡እንዲወስን፡መገፋፋት፡የነበረባቸው፡የተቃዋሚ፡ድርጅቶች፡ነበሩና፡ምን፡ነካቸው?።ሕዝብ፡የመሪ፡ያልለህ፡እያለ፡የትግሬ፡ ወያኔዎች፡ሲያሠቃዩት፡ቆርራጥ፡ተቃዋሚዎች፡መሥዋዕትነትን፡ለመውሰድ፡አለምዘጋጀታቸው፡ያስገርማል።የትግሬ፡ወያኔዎች፡ እንደ፡ሆኑ፡እንካችሁ፡ብለው፡ሊሰጧቸው፡የሚቃጡት፡ምንም፡ነገር፡እንደ፡ሌላቸው፡የታወቀ፡ነው።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s