ኢህአዴግ ሕዝቡ ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት ሀዘኑን እንዲገልፅ በማስገደድ ላይ ይገኛል

Imageየተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደገለፁት መንግስት የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ህልፈተ ሕይወት በቴሌቭዥን ይፋ ካደረገበት ጊዜ ጀምሮ ህዝቡ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት ሀዘን እንዲቀመጥና እንዲያለቅስ እያስገደደ ይገኛል፡፡

እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደገለፁት በሚሰሩባቸዉ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ፕሮግራም እየወጣላቸዉ ጥቁር የሀዘን ልብስ በመልበስ በቤተ-መንግስት እየተገኙ ሀዘናቸዉን እንዲገልፁ የተገደዱ ሲሆን ፤ ሀዘን መድረሳቸዉን ለማረጋገጥም ሰነድ ተዘጋጅቶላቸዉ እዚያ ላይ ስማቸዉን እንዲያሰፍሩና እንዲፈርሙ ተደርገዋል፡፡

አንዳንድ የንግዱ ህብረተሰብ አካላትም እንደገለፁት የንግዱ ህብረተሰብ ከዚህ በፊት በተለያየ መልኩ የተደራጀ በመሆኑ በራሱ አደረጃጀቶችና በሚመለከታቸዉ የመንግስት አካላት ጥሪ እየቀረበለት በቤተ-መንግስት እየተገኘ ሀዘኑን እንዲገልፅ እየተደረገ ይገኛል፡፡

አያይዘዉም በቤተ-መንግስቱ የሀዘን ስነ-ስርዓት ላይ ከመገኘት ባሻገር ለሀዘን ስነ-ስርዓቱ ማድመቂያ የሚዉል በተለይም የቀብር ስነ-ስርዓቱ በሚፈፀምበት ቀን የሚለበስ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፎቶ የታተመበት ቲሸርት ለማዘጋጀት እስፖንሰር እንዲሆኑ የተጠየቁ ሲሆን ፤ ለዚህም የሚዉል ከፍተኛ መጠን ያለዉ ገንዘብ በማዋጣት ላይ ይገኛሉ፡፡

የቀረዉ የህብረተሰብ ክፍል በየቀበሌዉ በተጣለለት ድንኳን እየተገኘ የሀዘኑ ተካፋይ እንዲሆን እንዲሁም ፊርማዉን በተዘጋጀለት ሰነድ ላይ እንዲያኖር እየተደረገ ሲሆን ፤ በቀበሌ ደረጃ ከሚካሄዱ የሀዘን ፕሮግራሞች ጋር በተያያዘ በሁሉም የአዲስ አበባ ቀበሌወች የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓትም እየተካሄደ ይገኛል፡፡

እነዚህ በቀበሌ ደረጃ የሚካሄዱ የሀዘን ፕሮግራሞች የጠቅላይ ሚኒስትሩን ምስል በሚያሳዩ ትላልቅ ቢልቦርዶች ፣ ባነሮችና ፖስተሮች ያሸበረቁ ሲሆን ፤ “ጀግና ነህ ! ጀግና ቢሞትም ራዕይ አይሞትም ! ሁሌም እናስብሀለን! ሁሌም እናከብርሀለን! እንወድሀለን! የጀመርከዉን ከግብ እናደርሳለን! መልየ አናሳፍርህም! …”  የሚሉ መልዕክቶች በጉልህ ተንፀባርቀዉባቸዋል፡፡

ይህ ህዝቡን በሀዘን ስነ-ስርዓት ላይ ተካፋይ እንዲሆን በመንግስት የሚደረገዉ ግፊት በክልሎች ፤ ዞኖች ፣ ወረዳዎችና የገጠር ቀበሌዎች ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ፤ ህዝቡ ከስራ መባረርን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት እርምጃዎችን በመፍራት  ሳይወድ በግዱ በተለያዩ የሀዘን መግለጫ ፕሮግራሞች ላይ ተካፋይ በመሆን ላይ ነዉ፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እንዲህ አይነት የሀዘን ፕሮግራሞችን ደግሞ ደጋግሞ በማስተላለፍ ላይ ሲሆን ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለሀገርና ለህዝብ አሳቢ ታላቅ የሀገር መሪ ስለነበሩ ህብረተሰቡ በእርሳቸዉ ሞት ከመጠን በላይ አዝኗል በማለት ፕሮፖጋንዳዉን ተያይዞታል፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ በረከት ስምዖን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥንና ሬድዮ በሰጡት መግለጫ “ለመላ የኢትዮጵያ ህዝቦች በዚህ አጋጣሚ ባሳዩት ፅናት ፣ ወገናዊነትና ለመለስ በሰጡት ክብር የተሰማንን ክብርና ያለንን አድናቆት ለመግለፅ ”  እወዳለሁ ያሉ ሲሆን ፤ መንግስት “ህዝቡ በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች የጀመረዉን በመሪዉ ድንገተኛ ሞት የተሰማዉን መሪር ሀዘን የሚገልፅበትን ሁኔታ በቀጣይነት ያደራጃል”  ያሉ ሲሆን ፤ አያይዘዉም “ዋናዉ ስራችን ይሄ ነዉ” በማለት ተናግረዋል፡፡

የተለያዩ የፖለቲካ ተንታኞች መንግስት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሞት ተከትሎ ህዝቡ ይነሳብናል በሚል ፍርሀት ተሸብቧል ፤ ስለዚህም አሁን እያደረገ ያለዉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደር የለሽ ፣ ለህዝብ አዛኝና አሌንታ ነበሩ በማለት የአገዘዛዙን የተበላሸ ስም ለማስተካከልና ህዝቡ ክፉኛ ያዘነ በማስመሰል የህዝቡን ስሜት ለማቀዝቀዝ ነዉ ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ 

መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለህዝብ አዛኝና አሌንታ የነበሩ ወደር የማይገኝላቸዉ ሰዉ ነበሩ ፤ ለዚህም ህብረተሰቡ መሪር ሀዘን ተሰምቶታል በማለት ፕሮፖጋንዳዉን አጠናክሮ በቀጠለበት በዚህ ሰዓት የተለያዩ አለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ትክክለኛ ማንነት የሚያሳይ የተለያዩ ዘገባዎችን እያቀረቡ ሲሆን ፤ ብዙዎቹ ዘገባዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ህገመንግስትን እንደሽፋን የሚጠቀሙ ፣ የዜጎችን ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች የጨፈለቁ ፣ አፋኝ ፣ የአንድ ጎሳ የበላይነት የሰፈነበት አገዛዝ የገነቡ… አንባገነን” ነበሩ ብለዋቸዋል፡፡

By Betre Yacob

Advertisements

One comment

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s