መንግስት የፍትህ ጋዜጣ አዘጋጆችን በአንድ ላይ ለማሰር እየተዘጋጀ ነዉ

By Betre Yacob

ኢሳት ታማኝ ምንጮቹን ጠቅሶ በ21/1/2005 እንደዘገበዉ መንግስት የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የሆነዉንና “አንድ በሉ” በሚል የጋዜጣዋ አምድ ስር በዲሞክራሲ ፣ ነፃነት እና ፍትህ ዙሪያ በመንግስት ላይ በሚሰነዝራቸዉ የሰሉ ትችቶቹ የሚታወቀዉ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝንና ሌሎች ከፍተኛ የጋዜጣዋ አዘጋጆችን በአንድ ላይ ለማሰር ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ነዉ፡፡

በዚህ የኢሳት ዘገባ እንደተገለፀዉ ድሮ አቃቤ ህግ የነበሩትና በአሁኑ ሰዓት የአቶ በረከት ስምዖን ረዳት በመሆን በሚንስትር ድኤታ ማዕረግ በኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዉስጥ በመስራት ላይ የሚገኙት አቶ ሽመልስ ከማል በጋዜጠኞቹ ላይ የሚቀርበዉን ክስ ድራፍት እንዲያሻሽሉ በፍትህ ሚኒስቴር ታዝዘዉ የፈጠራ ወንጀል በማዘጋጀት ስራ ተጠምደዉ ደፋ ቀና እያሉ ይገኛሉ፡፡

ኢሳት በዘገባዉ የደህንነት ሰዎች የጋዜጠኛ ተመስገንን ዉሎና አዳር በተለየ ሁኔታ መከታተል ጀምረዋል ያለ ሲሆን ፤ ከኢሳት ጋዜጠኛ ጋር በስልክ ቃለ-መጠየቅ በሚያደርግበት ወቅትም ስልኩ ባልተለመደ ሁኔታ እየተቆራረጠ ሲያስቸግረዉ እንደነበር አያይዞ ጠቁሟል፡፡

ይህን የኢሳት ዘገባ ተከትሎ አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋዜጠኞቹ ለኢትዮጵያ ህዝብ አይንና ጀሮ በመሆን በሙያቸዉ የሚጠበቅባቸዉን ከማበርከታቸዉ ጋር በተያያዘ በመንግስት ኢ-ፍትሀዊ እርምጃ ሲወሰድባቸዉ ዝም ብሎ ማየት ዉለታ ቢስነት በመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ለጋዜጠኞቹ ዘብ ሊቆምላቸዉና ሊከራከርላቸዉ ይገባል በማለት እየተናገሩ ይገኛል፡፡

ፍትህ ጋዜጣ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት በመንግስት ጥብቅ ሚስጥር ተደርጎ ተይዞ በነበረበት ወቅት ይዛዉ በወጣችዉ የጠቅላይ ሚኒስትሩን መሞት የሚያጋልጥ ጽሑፍ ምክንያት ከሕትመት የታገደች ሲሆን ፤ እገዳዉን ተከትሎም ዋና አዘጋጇ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከአንድ አመት በፊት በፃፋቸዉ ጽሑፎቹ ክስ ተመስርቶበትና አወዛጋቢ በሆነ ሁኔታ የዋስ መብቱን ተነፍጎ ለ6 ቀናት በቃሊቲ እንዲታሰር ከተደረገ በኋላ ግልፅ ባልሆነ ሁኔታ ክሱ እንዲነሳለት ተደርጎ ነበር፡፡

መንግስት የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ የሚዲያ አፈናዉን አጠናክሮ በመቀጠል ከፍትህ ጋዜጣ ባሻገር የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣን ከህትመት ያገደ ሲሆን ፤ ይህም ዛሬ ሀገሪቱን ምንም ነፃ የፕሬስ ዉጤት ከሌላቸዉ የአለማችን ሀገሮች ተርታ አሰልፏታል፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s