በኢድ አል አድሐ/አረፋ/ በዓል ላይ ሙስሊሙ ድፍረት የተሞላበት ተቃዉሞ አካሂዷል

By Betre Yacob

አንባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት ዲሞክራሲያዊ የመጅሊስ ምርጫ ተካሄደ እያለ በሚናገበት ሰዓት በአዲስ አበባ ስቴድየም እና አካባቢዉ የኢድ አል አድሐ/አረፋ/ በዓል ለማክበር የወጣዉ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝበ ሙስሊም ሰላት ከተጠናቀቀ በኃላ ከዚህ በፊት ከተደረጉት ሁሉ በላይ ጠንካራ ሊባል የሚችል ተቃዉሞ አካሂዷል፡፡

የኢድ ሰላት እንዳበቃ ህዝበ ሙስሊሙ ለመንግስት ማስጠንቀቂያ ያለዉን ቢጫ ካርድ ደጋግሞ ያዉለበለበ ሲሆን ፤ ቀጥሎም እጁን በካቴና እንደታሰረ በማስመሰል ሁለት እጁን አጣምሮ ወደ ላይ ከፍ በማድረግ እየተካሄደበት ያለዉን ጭቆና እና አፈና አሳይቷል፡፡ በመቀጠልም ተክቢራ በማሰማት  ፤  “በ50 ብር ምርጫ የለም!! ፣ ምርጫችን – በመስጂዳችን!! መንግስት በሐይማኖት ጣልቃ አይግባ!! ፣ ያልመረጥነዉ አይመራንም ፣ የታሰሩት – ይፈቱ!! ፣ ህገ-መንግስቱ ይከበር!! ፣ ኮሚቴዉ ይፈታ!! ፣ ለመብታችን እንሞታለን ፣ ለዲናችን እንሞታለን” እና የመሳሰሉ ጥልቅ መልዕክት ያነገቡ የተቃዉሞ መፈክሮችን እጅግ በደመቀና ከዚህ በፊት ተደርጎ በማይታወቅ ሁኔታ አሰምቷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ዋ! ዋ! ዋ! ዋ! ሲሉ ከባድ ማስጠንቀቂ ለመንግስት አስተላልፈዋል፡፡

በዚህ ተቃዉሞ ከላይ ከተጠቀሱት መፈክሮች በተጨማሪ “ግድያ ይቁም!!” ሲሉ መንግስት በሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ እየወሰደ ያለዉን ኢ-ፍትሀዊ እርምጃ አዉግዘዋል፡፡

እንደሚታወቀዉ ባለፈዉ ሳምንት በደቡብ ወሎ ዞን መንግስት የሙስሊም ተቃዋሚዎችን ከማሰሩ ጋር በተያያዘ በሙስሊሙ ህብረተሰብና በፌደራል ፖሊስ መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት 4 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ፤ ከ20 በላይ ደግሞ በጥኑ ቆስለዉ በደሴ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸዉ ይገኛል፡፡

በአዲስ አበባ በተካሄደዉ ተቃዉሞ ከመንግስት ቀጥሎ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ከምንግዜዉም በላይ ከፍተኛ ትችት የገጠመዉ ሲሆን ፤ “ኢቲቪ ዉሸታም!! ፣ ኢቲቪ ሌባ!! ፣ ዉሸት በቃን!”! እና የመሳሰሉት መፈክሮች ከተቃዋሚዎች በተደጋጋሚ ተደምጠዋል፡፡

በዚህ ተቃዉሞ ህዝበ ሙስሊሙ ከዚህ ቀደሙ በተለየ ሁኔታ ስታዲየም እና አካባቢዉን ለቅቆ የተቃዉሞ ድምፁን እያሰማ ወደተለያዩ አቅጫወች የተመመ ሲሆን ፤ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እና በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ህንፃ ፊት ለፊት በመቄምም ቁጣ የተቀላቀለበት ተቃዉሞዉን በድፍረት አሰምቷል፡፡

የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት መሰል ተቃዉሞዎች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተጠናክረዉ የተሰሙ ሲሆን ፤ በባህር ዳር ፣ በጎንደር  ፣ በደሴ ፣ በወልደያ እና በከሚሴ የተካሄደዉ ከሁሉም በላቀ መልኩ የደመቀ ነበር፡፡

ምንም እንኳን ይህን የኢድ አል አድሐ/አረፋ/ ተቃዉሞ ተከትሎ  በፌደራል ፖሊስ እና በሙስሊሙ ህብረተሰብ መካከል ግጭት ይፈጠራል ተብሎ ተፈርቶ የነበረ ቢሆንም ፤ ያ ሳይሆን ቀርቶ ሁሉም ነገር በሰላም ተጠናቋል፡፡ ህብረተሰቡም እንደተለመደዉ ሁሉ ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ ተቃዉሞዉን እያሰማ ወደ መጣበት ተበትኗል፡፡

በዚህ ተቃዉሞ ከሙስሊሙ ጎን ብዙ ቁጥር ያላቸዉ ክርስቲያኖች አብረዉ የታዩ ሲሆን ፤ ይህም በሙስሊሙ ህብረተሰብ የተጀመረዉ ተቃዉሞ ሁሉንም ወዳሳተፍ ህዝባዊ ተቃዉሞ እያመራ እንደሆነ የሚያመላክት ነዉ፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s