አንድነት ፓርቲ በይፋ ህዝባዊ የተቃውሞ ንቅናቄ ጀመረ

Image

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት) ፓርቲ ገዥው የፓርቲ ኢህአዴግን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን እየጣሰ ነው በሚል ዛሬ ሰኔ 13 ቀን 2005 ዓ.ም.  ይፋዊ ህዝባዊ ንቅናቄ መጀመሩን አስታወቀ፡፡ ፓርቲው አዲስ አበባ ቀበና በሚገኘው ዋና ፅህፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት”(Millions of Voices For Freedom) በሚል መሪ ቃል መጀመሩን አስታውቋል፡፡

 የሚሊዮኖችን ድምፅ በመሰብሰብ ከህገ መንግስቱ ጋር የሚጋጨውን የፀረ ሽብርተኝነት ህግ በመቃወም እንዲሰረዝ የተቃውሞ ስምምነት ፊርማ(ፒቲሽን) በማሰባሰብ ለእስር ተዳረጉ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች እና የኃይማኖት ነፃነት ጠያቂዎች እንዲፈቱ እንጠይቃለን ብሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሀገሪቱ በተለያየ ምክንያት ገጠርና ከተማ ያሉ ከአዲስ አበባና ሌሎች ከተማ ያሉ ዜጎች አለአግባብ ከሚኖሩበት ቀዬ ማፈናቀል በተለይም ዘርን መሰረት በማድረግ ከጉራፈራዳና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ያሉ ነዋሪዎች እና  በልማት ስም ለውጭ ዜጎች መሬት እየተሰጠ እንደ ጋምቤላ ያሉ ዜጎቻችን  መፈናቀላቸው ህገወጥ ተግባር ነው በሚል በማውገዝ የድርጊቱ ፈፃሚዎችን ለፍርድ ማቅረብ እንደተዘጋጀና ለዚህም እንቅስቃሴያችንን የሚደግፉ ኢትዮጵውያን  ፊርማቸውን እንዲያኖሩ ጠይቋል፡፡   

ፓርቲው ከላይ የተጠቀሱትን ተግባራዊ ለማድረግ የተለያዩ የሰላማዊ ትግል ስልቶችን የቀየሰ ሲሆን