አሰቸኳይ ወገናዊ ጥሪ!

ጎጠኛው የወያኔ ገዢ ቡድን በኢትዮጵያ ታሪክ ከነበሩት አገዛዝ ሁሉ እጅግ በከፋና በባሰ መልኩ የአገሪቱን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የጣለ፤ ሕዝብን ከቦታውና ከቀየው እያፈናቀለ ለከፍተኛ ሥቃይና መከራ በመዳረግ ለይ ይገኛል።

እንዲሁም በኃይማኖት እምነት ጣልቃ እየገባ፤ የአገሪቷን ድንግል መሬት ለባዕዳን በመሸጥ ወገኖቻችንን በማንነታቸው እንዲያፍሩና አገር አልባ እንዲሆኑ በማድረግ፤ ለእርስ በርስ ግጭትና ለከፋ ችግር ዳርጓቸዋል..

ከዚህም ባሻገር ይህ ጠባብ አረመኔ ቡድንና ጭፍሮቹ በሙስና የአገሪቱን አንጡራ ሀብት እየዘረፉ በማራቆትና ይባስ ብሎም በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ከተሞች ለሆዳቸው ባደሩ ካድሬዎች አማካኝነት ስደተኛውን በመደለል ለማስበዝበዝ ከሚሞክሯቸው ስልቶች መሃከል ጥቂቶቹ፦

1. ለአባይ ግድብ ገንዘብ አዋጡ፤ ቦንድ ግዙ እያሉ ሕዝቡን ቁም ስቅሉን ማሳየት

2. ለአገር ውስጥ ፍጆታ ሊውሉ የሚችሉ ምርቶችን በጭፍሮቻቸው አማካይነት ወደ ውጭ አገር በመላክ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለግል ኪሳቸው ከማጋበስ አልፈው ልጆቻቸውንም በዓለም ዙሪያ በታወቁ ታላላቅ የትምህርት ተቋማት ሲያስተምሩ በተቃራኒው ደግሞ የአገሪቱን ሕፃናት ትምህርት እንዳያገኙ ሥርዓተ ትምህርቱን ከማዳከም አልፈው የዕለት ጉርሳቸውን በመንፈግ ትውልድን ማጠፋት መቀጠሉ እንደምሳሌ የሚጠቀሱ ናቸው።

3. አሁን በቅርቡ ደግሞ አርባ ለስልሳ (40/60) በሚል መርሃ ግብር መሬት እንሰጣለን መሬት በምደባ ወይም በማህበር እንድትሰሩ እናደርጋለን እያሉ የውጪ ምንዛሬ እጥረታቸውን ለማሟላትና የጭካኔ አገዛዝ ዘመናቸውን ለማራዘም በመላው ዓለም እየተዘዋወሩ ለሌላ ዝርፊያ እየተዘጋጁ ነው።

ስለዚህ ከዚህ ከደሃ ህዝብ እየተነጠቀ የሚሰጣችሁ ወይም የደሃ ቤት እየፈረሰ የምትገዙት መሬት ለሚፈናቀለው ወገን ሥቃይና መከራ ከህሌና ወቀሳና ከታሪክ ተጠያቂነት አትድኑም።
በመሆኑም ማንኛውም ለአገርና ለወገን ተቆርቋሪ ነኝ የሚል ኢትዮጵያዊ ሁሉ ወያኔ/ኢሕአዴግ አገራችንን ከነአካቴው ለማጥፋት የጠነሰሰውን ሴራ ለማከሸፍ ይረዳ ዘንድ፤

1. ወያኔ/ኢሕአዴግ በተለየ መልኩ በሙዚቃና በመዝናኛ ምሽት ሰበብ በሚያደረገው የገንዘብ ማሰባሰቢያ (ፈንድሬይዚንግ) ዝግቶች አለመሳተፍ፣

2. ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎሮሮ እየተነጠቀ ውጭ አገር እየተላከ የሚሸጠውን እንጀራና ሌሎችንም ቁሳቁሶች አለመግዛት፤
ማሳሰቢያ

ሀ. የወያኔ/ኢሕአዴግ አገዛዝ እያሳደደን ነው ብላችሁ ጥገኝነት ከጠየቃችሁና ከተፈቀደላችሁ በኋላ ከዚህ አምባገነንና ጎጠኛ አገዛዝ ጋር በመመሳጠር ህዝብን ከሚጎዳ ተግባር ካልተቆጠባችሁ ለሚመለከተው ህጋዊ አካል በማሳወቅ እርምጃ የምናስወስድ መሆኑን አሰቀደመን እናሳውቃለን።

ለ. ነጋዴዎችም ሆናችሁ ወይም ግለሰቦች ለውጭ ምንዛሬ ፍጆታ ይሆን ዘንድ የወያኔ/ኢሕአዴግን ጠባብና ጎጠኛ አገዛዝ የሥልጣን እድሜውን ለማራዘም ህጋዊም ሆነ ህገ ውጥ በሆኑ አጀንዳዎቻቸውና መልካቸውን እየተቀያየሩ ከሚመጡ ከወያኔ የእርዳታ ተቋማትም ሆነ ከሥርዓቱ አቀንቃኝ ሆዳም ግለሰቦች ጋር እንዳትተባበሩ፤ ለኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችሁ የሥቃይና የመከራ ዘመን ማራዘሚያ አትሁኑ፤ ለዚህ ከልጅ ልጅ ከሚተላለፍ አሰነዋሪ ተግባር በመቆጠብ ከህሌና እዳ ነፃ በመሆን ወገናዊ ግዴታችሁን ተወጡ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

በቶሮንቶና አካባቢው የተቆርቋሪ ኢትዮጵያውያን
አሰተባባሪ ከሚቴ

Source: http://ethioandinet.wordpress.com

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s