አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ በጎንደር የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ሐምሌ 7 ቀን 2005ዓ.ም. እንዲቀየር መወሰኑን በደብዳቤ አሳውቋል፡፡

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) ሰኔ 30 ቀን 2005 ዓ.ም. በጎንደር የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ መንግስት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ለሓምሌ 7ቀን 2005 ዓ.ም ማስተላለፉን ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጨ አስታወቀ፡፡ ከሰላማዊ ሰልፉ ጋር በተያያዘ የታሰሩ አባላቱ በአፋጣኝ እንዲለቀቁ ጠይቋል፡… የአንድነት ፓርቲ የስራ አስፈፃሚና የብሔራዊ ም/ቤት አባላት በሰለላማዊ ሰልፉ ላይ በመሳተፍ ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸውም ተገልጧል፡፡
አንድነት ፓርቲ ዛሬ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው በጎንደር የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ወደ ለሓምሌ 7 ቀን 2005 ዓ.ም ያስተላለፈው መንግስት ሰላማዊ ሰልፉ በሚደረግበት ዕለት የሀይል እጥተት አለብኝ የሚል ጥያቄ በማቅረቡ መሆኑን ገልጧል፡፡
የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ አቶ ግዛቱ አቢዩ ጌታው አንድነት ሰላማዊ ሰልፉ እንዳያደረግ ከመወሰናቸው በተጨማሪ ሰላማዊ ሰልፉን ለማደናቀፍ ከአማራ ክልላዊ መስተዳደር ከመደበኛ የፖሊስና የፀጥታ ኃይሎች በተጨማሪ ልዩ ግብረኃይል መቋቋሙን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገልፀዋል፡፡ የከተማው ምክትል ከንቲባ በበኩላቸው ፓርቲው ሰኔ 30 ሊደረግ የታቀደው ሰላማዊ ሰልፍ እንዲዛወር የጠየቁ ሲሆን የዞኑ የአንድነት ፓርቲ በበኩሉ ሰላማዊ ሰልፉ ሐምሌ 7 ቀን 2005ዓ.ም. እንዲቀየር መወሰኑን በደብዳቤ አሳውቋል፡፡
የክልሉ መንግስት ሰላማዊ ሰልፉን ለማደናቀፍ የአንድነት ፓርቲ አመራሮችንና አባላትን በማሰር ላይ ይገኛሉ፡፡ እስከ አሁንም 10 አመራሮችና አባላት በህገወጥ መንገድ ታስረዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰሜን ጎንደር ዞን የምዕራብ አርማጮ ወረዳ ነዋሪ እና የአንድነት ፓርቲ የወረዳው አመራር አቶ ተገኝ ሲሳይ ከወረዳው ሳንጃ ከተማ በፀጥታ ኃይሎች ታፍነው ተወስደው እስካሁን ያሉበት አይታወቅም፡፡
ሰኔ 22 ቀን 2005 ዓ.ም በአብርሀጅራ ከተማ የታሰሩት 4 የአንድነት አባላትና አመራሮች ሰኔ 24 ቀን 2005ዓ.ም. በወረዳው ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ፖሊስ ለምርመራ የ14 ቀን ጠይቆ ተቀባጥነት አጥቶ ጠነበረ ቢሆንም በአስገራሚ ሁኔታ ዛሬ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ለፖሊስ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ተፈቅዶለታል፡፡ ይህንንም ተከትሎም ታሳሪዎቹ ከአርብ ሰኔ 28 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ የርሃብ አድማ በማድረግ ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ አንድነት ፓርቲ በብሔራዊ ምክር ቤቱ ባስወሰነው መሰረት በመላ ሀገሪቱ በሚደረጉት ሰላማዊ ሰልፎች ላይ የፓርቲው ስራ አስፈፃሚዎችና የብሄራዊ ም/ቤት አባላት ከፊት በመሆን ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸው ታውቋል፡፡
ምንጭ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s