የጋዜጠኞቹና የአክቲቪስቶቹ እስር አሳሳቢ ነው፡፡

ከኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ(ኢጋመ) የተሰጠ መግለጫ

ትላንት ሚያዝያ 17 2006 አመሻሽ ላይ ዞን 9 በተሰኘ ድረ ገጽ (ብሎግ) ላይ በሳል ፖለቲካዊና ማህበራዊ ትችቶችን በማቅረብ ከሚታወቁት ፀኀፍት መሀከል 7ቱ (ማህሌት ፋንታሁን በፍቃዱ ሀይሉ ናትናኤል ፈለቀ ዘላለም ክብረት አጥናፍ ብርሀነ አቤል ዋበላ ኤዶም ካሳዬ) እንዲሁም አስማመዉ ኃ/ጊዎርጊስ እና የአዲስ ነገር ባልደረባ የነበረው ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ይታወቃል፡፡ 

ግለሰቦቹ በተለያየ ቦታ በየስራ ገበታቸዉ ላይ እያሉ ሁሉም በተመሳሳይ ሰዓት በፀጥታ ሀይሎች ተይዘዉ በማዕከላዊ ምርመራ ማዕከል ታስረዉ የሚገኙ ሲሆን፤ የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት እስሩ በደንብ የታሰበበት ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ ታሳሪዎቹ ታሰሩ ከተባለበት ሰዓትና ደቂቃ ጀምሮ የሚገኙበትን አጠቃላይ ሁኔታ ለማጣራት አየሰራ ሲሆን ፤ እስካሁን በሰበሰበዉ መረጃ መሰረት ልጆቹን ለእስር የሚያበቃ ምን አይነት ማስረጃ እንደተገኘባቸው ለማወቅ አልቻለም፡፡

ሆኖም ግን ለእስር ከመዳረጋቸው በፊት ከመንግስት ሲርስባቸዉ በነበረዉ ህገወጥ ድርጊቶች ምክንያት ለረጅም ጊዜ ስራቸዉን ካቋረጡ በኋላ በቅርቡ ወደ ስራ መመለሳቸዉን ይፋ አድርገው እንደነበር ከድረገጻቸው ላይ ለመረዳት ችለናል፡፡ ይህ ጉዳይ እስሩን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎብናል፡፡ 

ስለሆነም የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ መንግስት ታሳሪዎቹን ለማሰር ያበቃዉ ተጨባጭ ማስረጃ ካለ ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ፤ ያ ካልሆነ ግን እስረኞቹን በአስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ እናሳስባለን፡፡ 

የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ 
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s