ማለቂያ የሌለው የወያኔዎች ጉድ …. የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ የሆነው አለቃ ጸጋዬ በርሄ ሰክሮ የሰው ሚስት ይዤ ካላደርኩ በማለቱ በቡጢ ተዘረረ።

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

በምእራብ አውስትራሊያ ኬንዊክ ግዛት በሚገኘው የትግራይ ተወላጆች ኮሚኒቲ ማእከል ግንቦት ሃያን በማስመልከት በተድረገ
ዝግጅት ላይ ለመታደም የዘመቱት የወያኔ ባለስልጣናት በገዛ ወዳጆቻቸው ተዋርደው ተመልሰዋል። በፖለቲካው መስክም ይሁን
በሴሰኝነታቸው እድል ያልሰመረላቸው የወያኔ ባለስልጣናት አብሯቸው ከተጓዘው አንዱ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ የሆነው አለቃ
ጸጋዬ በርሄ ሰክሮ የሰው ሚስት ይዤ ካላደርኩ በማለት ከፕሮቶኮል ውጪ በመንቀሳቀሱ የራያው ተወላጅ አቶ ተከስተ በትደጋጋሚ
ለ4 ጊዜ ቡጢ ሲያቀምሳቸው በክፍተኛ ደረጃ በማእከሉ ውስጥ ድንጋጤ ተፈጥሮ ነበር።
ሁኔታውን ለማረጋጋት ቢሞከርም ከሌሎች የጸጋዬ ባለሟሎች ጋር ግብግብ በመያያዝ .. እኔ ወዲ ራያ በማለት አቶ ተከስተ
በጸጋዬ እና ተከታዮቹ ላይ ጉዳት አድርሰዋል። በትግራይ የራያ ተወላጅ እና የቀድሞ የሕወሃት አባል የሆኑት አቶ ተከስተ
ባለቤታቸው ይዘው በዝግጅቱ ላይ የመጡ ቢሆንም በወቅቱ በነበረው ክፍተኛ የመጠጥ ብዛት ከልክ በላይ የጠጡት አለቃ ጸጋዬ
በቆንጆ የራያ ልብስ ደምቃ በሹሩባ ያጌጠችው የአቶ ተከስተ ሚስት አይናቸው ገብታ እንዲያመጡላቸው ቢያዙም የሰው ሚስት
እንደሆነችና ባለቤቷ አብሮ እንዳለ ቢነገራቸውም ሊሰሙ ባለመቻላቸው ያለችበት ቦታ ድረስ በስካር መንፈስ ሰተት ብለው ሲሄዱ
ነገሩ የገባው የቀድሞ የሕወሓት አባል አቶ ተከስተ በቡጢ ተቀብሏቸው መሬት ላይ ዘርግፏቸዋል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ በምእራብ አውስትራሊያ ኬንዊኪ የሚገኘው የትግራይ ኮሚኒቲ ለሁለት ተከፍሎ የወያኔ መሪዎችን
በማፋጠጥ ክባድ የፖለቲካ ኪሳራ እንደተፈጠረ ወዳጆቻችን ገልጸውልናል። ሕወሓት በኢትዮጵያ የሚያደርገው ድርጊት ለነገ
ልጆቻችን ቂም ማትረፍ ነው ወደዳችሁም ጠላችሁን ሕዝቡ ተለያየ ብላችሁ እያሰበችሁ ከሆነ አትሳሳቱ ሁሉ አድፍጦ እየጠበቀ
ነው ድንገት የፈነዳ እለት ይበቀላቹሃል። በቀሉም ለትግራይ ተወላጆች ይተርፋል መፍትሄ አምጡ በማለት የመከሩ ሲሆን
በሌላው ወገን ደሞ አማራው አድብቷል የአማራው ጅብ እንዳይበላችሁ እናንተ እርስ በርስ እየተባላችሁ ነው አታናቆሩ ሲሉ
መካሪዎችን ሮሮ አስምተዋል።
ከእራት በፊት በቤተክርስቲያናት መካከል የተከፋፈለውን አካል ለማስታረቅ የሞከሩት የወያኔ ባለስልጣናት በፍጹም ለማስማማት
ባለመቻላቸው በአቡነ ማትያስ ስም ለማስፈራራት ቢሞክሩም መሳቂያ ሆነዋል። የተዋህዶ ቤትክርስቲያን በመንደርተኖች
የተክፈለች ሲሆን የአድዋ እና የተንቤን ተብለው የሚጠሩት ቤተክርስቲያኖች ሲኖሩ በኮሚኒቲ ማእከሉ ውስጥ ያለውን ከሕወሓት
ቢሮ ጋር አብሮ የተጣበቀውን አድዋዎች ሲያስተዳድሩት ተንቤኖች ደሞ የራሳቸውን ቤተክርስቲያን በመመስረት ተገንጥለው
ወተዋል። ይህንን ግኡዳይ ለመፍታት እና ወደ አንድነት ለማምጣት በቦትው የተገኙት የፖለቲካ ባለስልጣናት አለቃ ጸጋዬ እና
የአባይ ወልዱ ባለቤት እንዳልተሳካላቸው ሲታወቅ ከተንቤን ተወላጆች ጠንካራ ሂስ ቀርቦባቸዋል።# ምንሊክሳልሳዊ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s