በናዝሬት ቅስቀሳዉን ፖሊሶች ለማስተጓጎል ቢሞክሩ ሕዝቡ በራሪ ወረቀቶች እየደረሱት ነው

በአዳማ ናadama1ዝሬት ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 28 ቀን ቅስቀሳ ሲደረግ እንደነበረ፣ የአንድነት ፓርቲ የአዳም/ናዝሬት ቅርንጫፍ በፌስቡክ ገጹ ገለጸ። የመኪና ቅስቀሳ እንዳይደረግና በትላልቅ ፖስተሮች ማስተወቂያ እንዳይለጠፍ ፖሊሶች ያከላክሉ የነበሩ ሲሆን በቅስቀሳዉ የተሰማሩ፣ ድሬዳዋ ሆቴል አካባቢ፣ ለሰዓታት ታስረው እንደነበረ የአዳማ/ናዝሬት አንድነት ቅርንጫፍ በፌስ ቡክ ገጹ ያቀረበው ዘገባ ያስረዳል።

የሰልፉን ሕጋዊነት የሚገልጥ ደብዳቤም ቀስቃሾቹ ለፖሊሶች ቢያሳዩም ፖሊሶቹ ለመልቀቅ ፍቃደኛ እንዳልነበሩና ሊለቋቸው እንዳልቻሉ ዘገባው ገልጾ፣ ሕዝብ ግን ከመኪናው ላይ በራሪ ወረቀቶችን እየተሻማ ሲወስድ እንደነበረም አትቷል። በቅስቀሳዉ ወቅት የታሰሩ የአንድነት አባላት ዘጠኝ እንደሆኑ፣ ከነርሱም መካከል የአዳማ/ናዝሬት አንድነት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ዋቅቶላ እነ ሌሎች አማራሮች እንደሚገኙበት ለማወቅ ችለናል።

«በዚህ ሁኔታ ቅሰቀሳቸውን የፀጥታዉ ክፍል ቢያስተጓጉልም፣ ከሰዓት በኋላም ቀጥለዋል፡፡ሆኖም ፖስተር መለጠፍ አትችሉም በማለታቸው ዛሬም አልተለጠፈም፡፡በራሪ ወረቀቱን ቢከለክሉንም አባላቱ በከተማው በመዟዟር ሲበትኑ ውለዋል» ያለው የአዳማ/ናዝሬት አንድነት፣ ቅስቀሳው በነገው እለትም በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል አስታወቋል። Source:  አቡጊዳ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s