የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች 8 ሺህ ብር ዋስትና ተጠየቀባቸው

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ለህዝባዊ ስብሰባ ሲቀሰቅሱ በፖሊስ ተይዘው የታሰሩት የብሄራዊ ምክር ቤት አባል አቶ ዮሴፍ ተሻገር እንዲሁም የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል የሆነው ሲሳይ በዳኔ ዛሬ ህዳር 19/2007 ዓ.ም ሾላ አካባቢ በሚገኘው ፍርድ ቤት ቀርበው 8 ሺህ ብር ዋስትና እንዲያስይዙ ተወስኖባቸዋል፡፡

መርማሪው ም/ሳጅን ዳንኤል ከበደ የምርመራ መዝገቡ እንዳለቀ ቢያምኑም ‹‹ተጠርጣሪዎቹ ከወጡ ተመሳሳይ ወንጀል ስለሚፈጽሙ ተጨማሪ ቀነ ቀጠሮ ይሰጥልን›› ብለው ተከራክረዋል፡፡ ከታሳሪዎቹ መካከል አቶ ዮሴፍ ‹‹በህጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ አመራሮች በመሆናችን ወጥተንም የምንሰራው ህጋዊ ስራ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች በመሆናችን የዋስትና መብታችን ሊጠበቅልን ይገባል›› ሲሉ ተከራክረዋል፡፡

አቶ ሲሳይ በዳኔ በበኩሉ ‹‹አሁንም በምርመራ ወንጀል መስራታችን የሚያሳይ ነገር አላገኙም፡፡ ምንም አይነት ወንጀል ሳንሰራ ነው የታሰርነው፡፡ ቋሚ መኖሪያ ያለን ሰዎች ነን፡፡ በመሆኑም ዋስትናችን ሊከበርልን ይገባል›› ሲል ተከራክሯል፡፡ በመጨረሻም ዳኛ አያሌው ደስታ ሁለቱ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እያንዳንዳቸው 4 ሺህ ብር የገንዘብ ማስያዢያ (ዋስ) እንዲያቀርቡ ወስነውባቸዋል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ለእስር የተዳረጉት ሌሎች ሁለት የፓርቲው አባላት ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው ተጨማሪ ሰባት ቀናት የምርመራ ጊዜ እንደተሰጠባቸው የሚታወስ ነው፡፡ በተለያዩ ጊዜያት ሰማያዊ ፓርቲ ባደረጋቸው ሰልፎች በፖሊስ የሚያዙ የፓርቲው አባላት በተደጋጋሚ የገንዘብ ዋስትና ሲጠየቅባቸው ቆይቷል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s