በኢድ አል አድሐ/አረፋ/ በዓል ላይ ሙስሊሙ ድፍረት የተሞላበት ተቃዉሞ አካሂዷል


By Betre Yacob

Image

አንባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት ዲሞክራሲያዊ የመጅሊስ ምርጫ ተካሄደ እያለ በሚናገበት ሰዓት በአዲስ አበባ ስቴድየም እና አካባቢዉ የኢድ አል አድሐ/አረፋ/ በዓል ለማክበር የወጣዉ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝበ ሙስሊም ሰላት ከተጠናቀቀ በኃላ ከዚህ በፊት ከተደረጉት ሁሉ በላይ ጠንካራ ሊባል የሚችል ተቃዉሞ አካሂዷል፡፡

የኢድ ሰላት እንዳበቃ ህዝበ ሙስሊሙ ለመንግስት ማስጠንቀቂያ ያለዉን ቢጫ ካርድ ደጋግሞ ያዉለበለበ ሲሆን ፤ ቀጥሎም እጁን በካቴና እንደታሰረ በማስመሰል ሁለት እጁን አጣምሮ ወደ ላይ ከፍ በማድረግ እየተካሄደበት ያለዉን ጭቆና እና አፈና አሳይቷል፡፡ በመቀጠልም ተክቢራ በማሰማት  ፤  “በ50 ብር ምርጫ የለም!! ፣ ምርጫችን – በመስጂዳችን!! መንግስት በሐይማኖት ጣልቃ አይግባ!! ፣ ያልመረጥነዉ አይመራንም ፣ የታሰሩት – ይፈቱ!! ፣ ህገ-መንግስቱ ይከበር!! ፣ ኮሚቴዉ ይፈታ!! ፣ ለመብታችን እንሞታለን ፣ ለዲናችን እንሞታለን” እና የመሳሰሉ ጥልቅ መልዕክት ያነገቡ የተቃዉሞ መፈክሮችን እጅግ በደመቀና ከዚህ በፊት ተደርጎ በማይታወቅ ሁኔታ አሰምቷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ዋ! ዋ! ዋ! ዋ! ሲሉ ከባድ ማስጠንቀቂ ለመንግስት አስተላልፈዋል፡፡

በዚህ ተቃዉሞ ከላይ ከተጠቀሱት መፈክሮች በተጨማሪ “ግድያ ይቁም!!” ሲሉ መንግስት በሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ እየወሰደ ያለዉን ኢ-ፍትሀዊ እርምጃ አዉግዘዋል፡፡

እንደሚታወቀዉ ባለፈዉ ሳምንት በደቡብ ወሎ ዞን መንግስት የሙስሊም ተቃዋሚዎችን ከማሰሩ ጋር በተያያዘ በሙስሊሙ ህብረተሰብና በፌደራል ፖሊስ መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት 4 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ፤ ከ20 በላይ ደግሞ በጥኑ ቆስለዉ በደሴ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸዉ ይገኛል፡፡

በአዲስ አበባ በተካሄደዉ ተቃዉሞ ከመንግስት ቀጥሎ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ከምንግዜዉም በላይ ከፍተኛ ትችት የገጠመዉ ሲሆን ፤ “ኢቲቪ ዉሸታም!! ፣ ኢቲቪ ሌባ!! ፣ ዉሸት በቃን!”! እና የመሳሰሉት መፈክሮች ከተቃዋሚዎች በተደጋጋሚ ተደምጠዋል፡፡

በዚህ ተቃዉሞ ህዝበ ሙስሊሙ ከዚህ ቀደሙ በተለየ ሁኔታ ስታዲየም እና አካባቢዉን ለቅቆ የተቃዉሞ ድምፁን እያሰማ ወደተለያዩ አቅጫወች የተመመ ሲሆን ፤ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እና በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ህንፃ ፊት ለፊት በመቄምም ቁጣ የተቀላቀለበት ተቃዉሞዉን በድፍረት አሰምቷል፡፡

የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት መሰል ተቃዉሞዎች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተጠናክረዉ የተሰሙ ሲሆን ፤ በባህር ዳር ፣ በጎንደር  ፣ በደሴ ፣ በወልደያ እና በከሚሴ የተካሄደዉ ከሁሉም በላቀ መልኩ የደመቀ ነበር፡፡

ምንም እንኳን ይህን የኢድ አል አድሐ/አረፋ/ ተቃዉሞ ተከትሎ  በፌደራል ፖሊስ እና በሙስሊሙ ህብረተሰብ መካከል ግጭት ይፈጠራል ተብሎ ተፈርቶ የነበረ ቢሆንም ፤ ያ ሳይሆን ቀርቶ ሁሉም ነገር በሰላም ተጠናቋል፡፡ ህብረተሰቡም እንደተለመደዉ ሁሉ ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ ተቃዉሞዉን እያሰማ ወደ መጣበት ተበትኗል፡፡

በዚህ ተቃዉሞ ከሙስሊሙ ጎን ብዙ ቁጥር ያላቸዉ ክርስቲያኖች አብረዉ የታዩ ሲሆን ፤ ይህም በሙስሊሙ ህብረተሰብ የተጀመረዉ ተቃዉሞ ሁሉንም ወዳሳተፍ ህዝባዊ ተቃዉሞ እያመራ እንደሆነ የሚያመላክት ነዉ፡፡

የተለመደዉ የአንባገነኖች የስልጣን አለቅም ግብ-ግብ መጨረሻ ፤ ዉርደት ፣ እስርና ሞት


ባደጉትና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት በቻሉት የምዕራቡ ሀገሮች አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ወይም ግለሰብ ሰላማዊ በሆነ የህዝብ ምርጫ ስልጣን ላይ ይወጣል፡፡ ግዳጁን ባጠናቀቀ ግዜ ወይም በወከለዉ ህዝብ ዘንድ አመኔታን ሲያጣ ደግሞ እንደ አወጣጡ ሁሉ ያለ ምንም ጭቅጭቅ ከስልጣኑ ዉልቅ ይላል፡፡ በእነዚህ ሀገራት ከዚህም በተለየ ሁኔታ መሪዎች በሀገር ላይ ከሚጋረጡ ፈተናዎች ጋር በተያያዘ ሀላፊነታችንን መወጣት አልቻልንም ሲሉ ተፈፀሙ ለሚሏቸዉ ስህተቶች ሁሉ ሀላፊነቱን በመዉሰድ ሌላ አቅምና እዉቀት ለሚፈቅድላቸዉ ሰዎች ስልጣናቸዉን አስረክበዉ በሰላምና በፍቅር ከነሙሉ ክብራቸዉ ሹልክ ይላሉ፡፡

አሁን አሁን ይህን መሰል ዲሞክራሲያዊ የስልጣን ሽግግር በብዙ ሀገሮች እየተስፋፋና እየተለመደ የመጣ ሲሆን ፤ እንደ ጋና ባሉ ኃላ ቀር በሚባለዉ የአፍሪካ አህጉር ዉስጥ በሚገኙ ሀገራትም መታየት ጀምሯል፡፡ ሆኖም ያለመታደል ሆኖ ዛሬም ቢሆን በብዙ የአፍሪካ ሀገሮች መሰል ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ፈታኝ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት አሁንም ገዥዎች ወደ ስልጣን የሚወጡትም ሆነ ከስልጣናቸዉ የሚወርዱት በጠመንጅ ብቻ ነዉ፡፡ እዚህ ላይ ባለፉት 50 ዓመታት ዉስጥ በሀገራችን የተካሄዱ የስልጣን ሽግግሮች ለዚህ አይነተኛ ማሳያ ይሆናሉ፡፡
ብዙዉን ግዜ በእንደዚህ ዓይነት በሐይል በታጀበ የስልጣን ሽግግር ወቅት ስልጣናቸዉን የሙጥኝ የሚሉ አንባገነኖች መጨረሻቸዉ ዘግናኝና አሳፋሪ ዉድቀት ነዉ፡፡ ብዙዎቹ በስልጣን ልቀቅ አለቅም ትግሉ ሕይወታቸዉን ሲያጡ የቀሩት ደግሞ ስልጣናቸዉን ሲነጠቁ በስልጣን ዘመናቸዉ በፈፀሙት ግፍ ስም ወደ ግዞት ይወረወራሉ ወይም ከተወለዱባት እናት ሀገራቸዉ ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ ተዋርደዉ ይሰደዳሉ ፤ አንዳንዴም ከዚህ የከፋ ነገር ይገጥማቸዋል፡፡

ለምሳሌ ያህል ከቱንዚያ ተነስቶ የአረቡን ዓለም ያዳረሰዉ አሁንም የት ላይ እንደሚቋጭ ያልታወቀዉ የፀደዩ አቢዎትን ተከትሎ ከስልጣናቸዉ በሰላም እንዲወርዱ ሲለመኑ አሻፈረኝ በማለት ከህዝብ ጋር ግብ ግብ የገጠሙትን የኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊን መጨረሻ መመልከት ይቻላል፡፡ ጋዳፊ ስልጣን በሰላም አስረክቦ ከነሙሉ ክብሩ ሹልክ ማለት እየቻለ በእብሪት ተወጥሮ አሻፈረኝ በማለቱ ከራሱ አሳፋሪና ወራዳ ሞት ባሻገር የልጆቹን ህይወት እንደ ቅጠል አርግፏል፡፡

በተመሳሳይ ስልጣን በሰላም እንዲያስረክብ ሲጠየቅ እንቢ ሲል የኖረዉ የግብፁ ሙባረክም አረፍ ብሎ ሰላማዊ አየር እየተነፈሰ ጣፋጭ የሆነ ህይወት ከቤተሰቦቹ ጋር በሚያጣጥምበት ዕድሜዉ ተዋርዶ ወደ እስር ቤት የተወረወረ ሲሆን ፤ የእርሱ ጦስ ለልጁም ሊተርፍ ችሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እነሎረንስ ባግቦን ፣ አሊ አብደላ ሳላህን ፣ ቤን አሊንንና ሌላ በርካታ አንባገነኖችን መጥቀስ ይቻላል፡፡
የሀገራችንንም ታሪክ ስንመለከት በአፄ ሐይለ ስላሴና ባለስልጣናቶቻቸዉ እንዲሁም እነሱን ተክተዉ ወደ ስልጣን በመጡት የደርግ ባለስልጣናት ላይ የደረሰዉ ያዉ የተለመደዉ ዉርደት ፣ እስር እና ሞት ነበር፡፡

የኢህአዴግ ባለስልጣናት መጨረሻ ምን ሊሆን ይችላል?

ምንም እንኳን የአንባገነኖች ከስልጣን አንለቅም ግብ ግብ ዉጤቱ ከላይ እንዳየነዉ በጣም የከፋ ቢሆንም የወቅቱ የሀገራችን መሪዎችና ባለስልጣናቱ ትንሽ እንኳን ከታሪክ መማር አቅቷቸዉ የህዝብ የሆነን ስልጣን ሙጭጭ በማለት ወደ ዉድቀት አፋፍ በፍጥነት እየተንደረደሩ ይገኛል፡፡

እንደሚታወቀዉ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ከስልጣን ዉረዱ አንወርድም ግብግቡን በ1997 ከተካሄደዉ ሀገር አቀፍ ምርጫ ማግስት ጀምሮ በይፋ የጀመሩት ሲሆን ፤ በተለይም ከቅርብ ግዜ ወዲህ የተቀዋሚ ፓርቲወችን አመራሮች እና አባላትን በማሳደድ የነፃዉን ፕሬስ ዉጤቶች ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ሁኔታ በማጥፋትና ጋዜጠኞቻቸዉንም በሐሰት ዉንጀላ በግፍ በማሰር አፈናዉን ከምን ግዜዉም በላይ አጠናክረዉ ቀጥለዋል፡፡

ይህ እየሆነ ባለበት ሁኔታ የኑሮ ፈተና ፣ የፍትህ ማጣት ፣ ጭቆናና እንግልት… የበዛበት ምስኪን ኢትዮጵያዊ ብሶቱ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መጦ ዛሬ ለመፈንዳት ቋፍ ላይ ይገኛል፡፡ እንግዲህ ይህ በግልፅ የሚያመለክተዉ በስልጣን ላይ የሚገኙ ባለስልጣናት በታሪካችን እንዳየናቸዉ እና በነኮሎኔል ጋዳፊ እንደደረሰዉ ሁሉ የከፋ አወዳደቅ ለመዉደቅ ቀናቸዉን እየቆጠሩ እንደሆነ ነዉ፡፡
በተለይም የህወሓት ጠንሳሽና የኢህአዴግ መስራቹ እንዲሁም ሀገሪቱን ለ21 አመታት በመዳፋ አስገብቶ የገዛዉ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በህመም ከስልጣኑ ከተገለለበት ቆይቶም ከሞተበት ግዜ ጀምሮ በብሶት ተወጥሮ የኖረዉ ጭቁን ህዝብ ከምግዜዉም በላይ ለለዉጥ የበለጠ በማቆብቆብ ላይ ነዉ፡፡ ይህንንም ተከትሎ የተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ልዩነታቸዉን ወደ ጎን በመተዉ እየተሰባሰቡና እተጠናከሩ ሲሆን አለማቀፋዊ ጫናዉም በአገዛዙ ላይ እየበረታ ይገኛል፡፡ አገዛዙ ለርካሽ ትርፍ ሲል የፈለሰፈዉ የጎሳ ፖለቲካም ዛሬ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ከስልጣን መገለል ተከትሎ በተነሳዉ የስልጣን ሽኩቻ በራሱ በኢህአዴግ ላይ የማይጠግኑት ትልቅ ስንጥቅ እየፈጠረ ነዉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እንደ ስልጣናቸዉ መከታ በሚቆጥሩት ጦር ዉስጥም ትልቅ ቅሬታ እየተፈጠረ ይገኛል፡፡ እንግዲህ ይህ ሁሉ ተደማምሮ አገዛዙን ከምን ግዜዉም በላይ ከዉድቀት አፋፍ ላይ አድርሶታል፡፡

እንዴዉም የሙስሊሙ ህብረተሰብ መንግስት በእምነታችን ጣልቃ መግባቱን ያቁም ሲል አስፈሪ የሆነ ህዝባዊ ተቃዉሞ ከወዲሁ የጀመረ ሲሆን ፤ ለሌላዉም የህብረተሰብ ክፍልም ጥያቄወቹን በሰላማዊ ተቃዉሞ እንዲጠይቅ ትልቅ ምሳሌ በመሆን ለታላቅ ህዝባዊ ተቃዉሞ በር ከፍቷል፡፡

ሆኖም ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማሪያም “ለአንዳንድ ሰዎች ቁልቁለት ቁልቁለት መሆኑ የሚታወቃቸዉ ወርደዉ ወርደዉ ወድቀዉ ሲከሰከሱ ነዉ” ሲሉ “አደጋ ያንዣበበበት የአፍሪካ ቀንድ” በሚለዉ መፅሐፋቸዉ እንደፃፉት ሁሉ አገዛዙ ከዉድቀት አፋፍ ላይ ባለበት በአሁኑ ሰዓትም ባለስልጣናቱ ከአጠገባቸዉ የተለዩትን የአገዛዙ ጭንቅላት የነበሩትን ሰዉ በሌላ አንባገነን በመተካት ጭቆናቸዉን ለማስቀጠል ደፋ ቀና በማለት ላይ ይገኛሉ፡፡ በሰከነ አዕምሮ በማሰብ የህዝቡን የስልጣን ልቀቁ ጥያቄ ዲሚክራሲያዊ በሆነ መንገድ በመመለስና ሌላም የህዝቡን ቁጣ ማብረጃ እርምጃዎችን በመዉሰድ ከፊታቸዉ እየመጣ ካለዉ አስፈሪ ሕዝባዊ ማዕበል እንደማምለጥ ፤ እራሳቸዉንና ቤተሰቦቻቸዉን ከሚመጣዉ መዓት እንደማዳን እነሱ ግን በጭፍን አዕምሮአቸዉ ስልጣናቸዉን ሙጭጭ እንዳሉ የማያዋጣ ግብ ግብ ከህዝብ ጋር ይዘዋል፡፡ የዚህ ግብ ግብ መጨረሻም እየየቀረበ ይገኛል፡፡

የኢህአዴግ ባለስልጣናት መጨረሻቸዉን ለማሳመር ምን ማድረግ ይችላሉ ?

የኢህአዴግ ባለስልጣናት ከፊት ለፊታቸዉ እየመጣ ካለዉ የከፋ አወዳደቅ እራሳቸዉን ለማትረፉ 11ኛዉ ሰዓት ላይ ሲሆኑ ፤ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አሁኑኑ ከተንቀሳቀሱ ከዉድቀቱ ለመዳን አማራጮች አሏቸዉ፡፡ በተያያዙት የጭፍን ጉዞ ከቀጠሉ ግን በቅርቡ እነርሱም በታሪክ እንዳየናቸዉ ግዞት ቤታቸዉ እንግልት ሕይወታቸዉ እንደሚሆን ጥርጥር የለዉም ፤ ሲልም ከዚያ የከፋ ነገር ሊገጥማቸዉም ይችላል፡፡ ከእነዚህ አማራጮች መካከል አሁኑኑ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እርምጃወች በመዉሰድ ያስከፉትን ህዝብ ማስደሰትና ይቅርታዉን ማግኘት ዋናዉና በጣም ቀላሉ ሲሆን ፤ ይህንን በመፈፀማቸዉ እራሳቸዉንና ቤተሰቦቻቸዉን ከሚመጣባቸዉ ችግር ከማዉጣት ባሻገር ስማቸዉንም በኢትዮጵያ ታሪክ ዉስጥ በበጎ ይፅፋሉ፡፡ በህዝቡም ዘንድ ትልቅ ከበሬታን ይጎናፀፋሉ፡፡

ከእነዚህ የህዝቡን ይቅርታ ለማግኘትና ከበሬታን ለመጎናፀፍ ሊወስዷቸዉ ከሚገቧቸዉ አፋጣኝ እርምጃወች ዉስጥ የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ፡-

1. ስልጣናቸዉን ለተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማጋራትና ጥምር መንግስት መመስረት
2. የፖለቲካ እስረኞችንና ጋዜጠኞችን መፍታት
3. ብሔራዊ እርቅ ማካሔድ
4. በፖለቲካ ችግር ከሀገር የተሰደዱ ኢትዮጵያዉያንን ወደ ሀገራቸዉ እንዲመለሱ ከይቅርታ ጋር መጠየቅ ፡፡

By Betre Yacob

ኢትዮጵያ በቡድን እየተመራች እንደሆነ ታወቀ


Imageኢሳት የዲፕሎማቲክ ምንጮቹን ጠቅሶ ትናንት እንደዘገበዉ የቀድሞዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአሁኑ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር በሆኑት በአቶ ስዩም መስፍን የበላይነት የሚመራ 7 አባላትን ያቀፈ አንድ ቡድን ሀገሪቱን የመምራት ስራ የተረከበ ሲሆን ፤ 4 አባላቱ የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት ናቸዉ፡፡

ምንም እንኳን ሐይለማሪያም ደሳለኝ በግዜያዊነት ጠቅላይ ሚኒስትሩን በመተካት የአመራሩን ቦታ እንደተረከቡ በኢትዮጵያ መንግስት በይፋ ቢገለፅም ሀገሪቱን የመምራት ስልጣን ግን በዚህ ቡድን እጅ ነዉ ሲል ያተተዉ ይህ የኢሳት ዘገባ ቡድኑ የትግራዮች የበላይነት በሰፊዉ የነገሰበት ነዉ ሲል አብራርቷል፡፡

በዚህ የኢሳት ዘገባ እንደተገለፀዉ በአቶ ስዮም መስፍን በሚመራዉ ቡድን ዉስጥ ምክትል የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ብርሀነ ገብረ ክርስቶስ በምክትል ሊቀመንበርነት የተሰየሙ ሲሆን ፤ የመከላከያ ኢታማጆር ሹም የሆነዉ ጀኔራል ሳሞራ የኑስና የሀገሪቱ የፀጥታ መስሪያ ቤት ሀላፊ አቶ ጌታቸዉ አሰፋ በአባልነት ይገኙበታል፡፡ ተያይዞም እንደተጠቆመዉ በቡድኑ ዉስጥ ከብአዴን ፣ ኦህዴድና ዴህዴን አንድ አንድ አባላት ተካተዋል፡፡

ቡድኑ ላዕላይና ታህታይ በሚል መዋቅር የተከፈለ ነዉ ያለዉ የኢሳት ዘገባ ምንም እንኳን በላዕላይ የአመራር መዋቅር ዉስጥ አጋር ድርጅቶች ባይሳተፉም በታችኛዉ መዋቅር ዉስጥ ይገኛሉ ሲል ጠቁሟል፡፡

ዘገባዉ አያይዞ እንደገለፀዉ ስርዓቱ ይህንን የአመራር ቡድን ለመፍጠር የተገደደዉ ምራባዉያኑንም ያስማማዉ በህወሓት ዉስጥ ጭምር በታየዉ የጎላ መከፋፈል ምክንያት ሁሉን የሚያስማማ መሪ መምረጥ አስቸጋሪ ሁኖ በመገኘቱ ነዉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ከታሰቡ ሰዎች መካከል አቶ ስዩም መስፍንን ጨምሮ ዋና ዋና የህወሓት ባለስልጣናት የፓርላማ አባል አለመሆናቸዉ ሌላ እንቅፋት ነበር፡፡

በሌላ የኢሳት ዘገባ እንደተገለፀዉ የአለም አቀፉ የግጭት ተንታኝ ቡድን (ICG) የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ በመስከረም ሊያወጣዉ አስቦት የነበረዉን ሪፖርቱን ያወጣ ሲሆን ፤ በሪፖርቱም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት በምስራቅ አፍሪካ የሚታይ ተፅዕኖ እንደሚፈጥር ጠቁሟል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የህወሓትን የበላይነት በማስፈንና አፈናን በማንገስ ሀገሪቱን በመዳፋቸዉ አስገብተዉ ሲገዙ ነበር ያለዉ ሪፖርቱ የእርሱን ሞት ተከትሎ ህወሓት ብቻዉን የስልጣን ሽግግር ሊያደርግ እንደሆነ አጋልጦል፡፡

አያይዞም አለም አቀፉ ህብረተሰብ ፣ አሜሪካ ፣ እንግሊዝና የአዉሮፓ ህብረት ሽግግሩ ሁሉንም ብሔር ብሔረሰብ ያሳተፈ እንዲሆን ሊንቀሳቀሱ ይገባል ሲል ጥሪ አቅርቧል፡፡

 

By Betre Yacob

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለዩ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን አረጋገጠ


በትረ ያዕቆብ

Imageየኢትዮጵያ ቴሌቭዥን “ላለፉት 21 ዓመታት በከፍተኛ ብስለትና ብቃት ሀገራችንን ሲመሩ የቆዩት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ” በዉጭ ሀገር የህክምና እርዳታ ሲደረግላቸዉ ከቆዩ በኃላ በ57 ዓመታቸዉ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ ሲል ሲያወዛግብ የነበረዉን የጠቅላይ ሚኒስትሩን መሞት ለህዝብ ይፋ አድርጓል፡፡ አያይዞም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሞት በተመለከተ በተመረጡ ቃላት የተከሸነ ከመንግስት የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ አስተላልፏል፡፡

“ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ከድህነትና ኃላ ቀርነት ለማላቀቅ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ አገልግለዉ ከፍተኛ የለዉጥ ተስፋ ያሳዩትን የክብር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ህልፈተ ሕይወት ስንገልፅ በታላቅ ሀዘን በተሰበረ ልብ ነዉ” ያለዉ የመንግስት ይፋዊ መግለጫ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላለፉት ሁለት ወራት በተደረገላቸዉ ከፍተኛ የህክምና እርዳታ ጥሩ የጤና መሻሻል አሳይተዉ የነበረ ቢሆንም ከትናንት በስቲያ  በተከሰተ ድንገተኛ ኢንፌክሽን ምክንያት ትናንት ከምሽቱ 5 ሰዓት ከ40 ደቂቃ በድንገት አርፈዋል ብሏል፡፡

“ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከምንም በላይ ሀገራዉንና ህዝባቸዉን የሚወዱ ለዚህ ሀገርና ህዝብ የላቀ ራዕይ የነበራቸዉ መሪ ነበሩ” ሲል  ስለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጎ በጎዉን ያተተዉ ይህ የመንግስት ይፋዊ መግለጫ “ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ራዕያቸዉን እዉን ማድረግ የጀመሩና አስተማማኝ ዉጤት ማምጣት የቻለ ድርጅትና መንግስት የገነቡ እንዲሁም ኢትዮጵያ በአለም አደባባይ ከፍ ብላ መጠራት እንድትጀምር ያደረጉ ታላቅና እጅግ አርቆ አሳቢ መሪ ነበሩ” ሲል  አሞካሽቷቸል፡፡

አያይዞም “ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሀገራችን ህገ-መንግስታዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እዲገነባ  ፤ የዜጎች እኩልነትና የዜጎች ዲሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶች ህገ-ምንግስታዊ ዋስትና አግኝተዉ በተግባር ላይ እንዲዉሉ ፤ በሀገራችን መልካም አስተዳደር እንዲሰፍንና በድህነት የሚማስኑ ወገኞችን የንሮ ሁኔታ ለማሻሻል የተስፋ ብርሀን የፈነጠቀ ተግባር  የፈፀሙ ፤ ኢትዮጵያን በአዲስና ጥሩ ዲሞክራሲያዊ መሰረት ላይ ያዋቀሩ ታላቅ መሪ ነበሩ” ሲል አትቷል፡፡

ይህ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን “ሀገራችንን በከፍተኛ ደረጃ ለመለወጥ የሚያስችለዉ የታላቁ የ5 ዓመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መሀንዲስ” ሲል የጠራዉ የመንግስት መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካዉያንም ኩራትና ክብር የነበሩ በአፍሪካ መልካም አስተዳደርና ዲሞክራሲ እንዲያብብ የሰሩ መላዉ ዓለም ብቃታቸዉን የመሰከረላቸዉ  ታላቅ መሪ ነበሩ ሲል ጠቅላይ ሚኒስትሩን አወድሷል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም የመንግስት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን ረፋዱ ላይ ለተለያዩ ሚዲያወች የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሞት ያረዳ ሲሆን ፤ ዛሬ ማለትም ነሐሴ 15/2012 በመላ ሀገሪቱ የሀዘን ቀን ሆኖ እንደሚዉልና ባንዲራም ዝቅ ብሎ እንደሚዉለበለብ አስታዉቋል፡፡ በተያያዘም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሞት ተከትሎ በሀገሪቱ ምንም አይነት የፖሊሲና የስትራቴጅ ለዉጥ አይኖርም ሲል የተናገረ ሲሆን ፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ህገመንግስቱን ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ቦታ ይይዛሉ ብሏል፡፡

እንደሚታወቀዉ ግንቦት 10/2004 በዋሽንግተን ሬገን ሕንፃ ከባድ የሚባል ተቃዉሞ ከገጠማቸዉ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላለፉት 2 ወራት ከአይን ተሰዉረዉ የቆዩ ሲሆን ፤ ይህንን ተከትሎ የተለያዩ ሚዲያዎች ፣ ተቋማት እና ግለሰቦች ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጠና ታመዉ በሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኙ ሲናገሩ የነበረ ሲሆን  ቆይቶም መሞታቸዉን ሲገልፁ ቆይተዋል፡፡ ሆኖም የመንግስት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ ናቸዉ… ወደ ስራቸዉ ይመለሳሉ በማለት ሲያስተባብሉ የቆየ ሲሆን ፤ በቅርቡም ከኢትዮጵያዉያን የዘመን መለወጫ መስከረም በፊት በስራ ገበታቸዉ ላይ ይገኛሉ በማለት ተናግሮ ነበር፡፡ ይህም  ኢትዮጵያዉያን  በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁኔታ ላይ ግራ እንዲጋቡ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

የተለያዩ የፖለቲካ ተንታኞች መንግስት የጠቅላይ ሚኒስትሩን መሞት ሲያስተባብል የቆየዉ ይፋ ከመደረጉ ጋር ተያይዞ ሊመጣ የሚችለዉን ሕዝባዊ ተቃዉሞ በመፍራትና በተፈጠረዉ የዉስጥ የስልጣን ሽኩቻ ምክንያት ጠቅላይ ሚኒስትሩን በሌላ ሰዉ መተካት ስላልቻሉ ነዉ ሲሉ የቆዩ ሲሆን ፤ በርግጥም በፓርቲዉ መንደር መደናገጥ ፣ ዉዥንብርና ሽኩቻ በግልፅ እየተስተዋለ ይገኛል፡፡

 

በኢህአዴግ ዉስጥ የተፈጠረዉ የስልጣን ሽኩቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል


የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሕይወት መኖር አለመኖር አጠያያቂ በሆነበት በዚህ ሰዓት በኢህአዴግ ዉስጥ የተፈጠረዉ የስልጣን ሽኩቻ እያደገ መምጣቱንና በተለይም ሰሞኑን አፍለኛ የከተማ ካድሬዎች በበረከት ስምዖን ዙሪያ መሰባሰብ መጀመራቸዉን የኢህአፓ ድምፅ የሆነዉ ፍኖተ ህብረት የተሰኘዉ ሬድዮ ዘግቧል፡፡

በተያያዘም በዘገባዉ እንደተጠቆመዉ የኢህአዴግ የደቡብ ክንፍ የሆነዉ ደኢህዴን ከህወሓት ጋር እየወገነ ሲሆን ብአዴን ግን አሁንም በልዩነቱ ፀንቶ የዉስጥ ለዉስጥ ፍትጊያዉን አፋፍሞ ቀጥሏል፡፡

በቤተ-መንግስት አካባቢ አቶ በረከት ስምዖን እንዲሁም የጤና ጥበቃ ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ቴወድሮስ አድሀኖ እና የመከላካያዉ ኢታማጆር ሹም ሳሞራ የኑስ ብቻ በብዛት እንደሚታዩ የቤተ-መንግስት ምንጮችን ጠቅሶ የዘገበዉ ፍኖተ ህብረት ብዙ ሰዎች አገሪቱ በእነዚህ ሰዎች መዳፍ ስር ናት እያሉ ይገኛል ሲል አትቷል፡፡

አያይዞም የመከላካያዉ ኢታማጆር ሹም ሳሞራ የኑስ ቤተ-መንግስቱን በተጠናከረ ሁኔታ እየጠበቀ ነዉ ያለ ሲሆን ፤ በአሁኑ ሰዓት እየተካሄደ ያለዉን የስልጣን ሽኩቻ ተከትሎ ጀነራሉ አንዳንድ እርምጃዎችንም መዉሰድ ጀምሯል ሲል ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
በተያያዘ ዜና የአገዛዙ የመኮንኖች ኮሌጅ ለ5ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸዉን ከፍተኛ መኮንኖችና የጦር አለቆች ትናንት ነሐሴ 6ቀን ማስመረቁ ታዉቋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ በዚሁ የምረቃ በዓል ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እንደሚገኙ ለተመራቂዎች በተበተኑ በራሪ ወረቀቾች ላይ እንደተጠቀሰ ኢሳት በዚህ ሳምንት መዘገቡ የሚታወስ ነዉ ፤ ሆኖም ግን የተባለዉ በነበር ቀርቶ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በበዓሉ ላይ ሳይገኙ ቀርተዋል፡፡ በምትኩ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ሐይለማሪያም ደሳለኝ በበዓሉ ላይ በመገኘት ተማሪዎች መርቀዋል፡፡

የመንግስት የኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ የሆነዉ አቶ በረከት ስምዖን በመንግስት ስር በሚገኘዉ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እየቀረበ የመለስን በፅኑ መታመም ሆነ መሞት እያስተባበለ ሲሆን ፤ በቅርቡም እንደተለመደዉ ከኢትዮጵያዉያን የዘመን መለወጫ መስከረም በፊት በስራ ገበታቸዉ ይገኛሉ በማለት ተናግሯል፡፡ ሆኖም ግን ጠ/ሚኒስትሩ የት እንደሚገኙ አሁንም ሊገልፅ አልቻለም፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ አቶ ስብሀት ነጋ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕይወት አሉ ወይ ? ተብለዉ ሲጠየቁ ከት ብለዉ የሳቁ ሲሆን ፤ ይህም የነበረከት ስምዖንን መግለጫ ታማኝነት ትልቅ ጥያቄ ዉስጥ ከትቶታል ፤ በተጨማሪም የዉስጥ ሽኩቻዉ እየከረረ መምጣቱን ፍንትዉ አድርጎ አሳይቷል፡፡

የተለያዩ የፖለቲካ ተንታኞች በረከት ስምዖን እንዲህ እያስተባበለ ያለዉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መሞት ይፋ ከመደረጉ ጋር ተያይዞ ሊመጣ የሚችለዉን ሕዝባዊ ተቃዉሞ በመፍራት እና በተፈጠረዉ የዉስጥ የስልጣን ሽኩቻ ምክንያት ጠቅላይ ሚኒስትሩን በሌላ ሰዉ መተካት ስላልቻሉ ነዉ እያሉ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከአረብ-ሳት ወረደ ሲል ኢሳት ዘገበ


Image

Picture from: http://www.durame.com

ኢሳት በሰኞ ነሐሴ 7 ፕሮግራሙ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን በጠና መታመም እንዲሁም ስለ ሕልፈታቸዉ መዘገቡን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት በመገናኛ ብዙኀኝ ላይ የሚያደርገዉን አፈናና ቁጥጥር ከምን ግዜዉም በላይ አጠናክሮ ቀጥሏል ያለ ሲሆን ፤ በቅርቡ “የኤርትራን የሳተላይት ቴሌቪዥን ያወከ ሲሆን በዚህ ተግባሩ ምክንያትም የኢትዮጵያ ቲሌቪዥን ከአረብ-ሳት የሳተላይት ስርጭት ታግዷል በማለት ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በኤርትራ ቴሌቪዥን ላይ የሚፈፅመዉን የማወክ ተግባር ተከትሎ አረብ-ሳት የኢትዮጵያን መንግስት እኩይ ተግባር የማስቆም ህጋዊና ተቋማዊ ሀላፊነት አለበት ሲሉ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር ባለስልጣናት መናገራቸዉን የጠቆመዉ የኢሳት ዘገባ የኤርትራ ቴሌቪዥን በሚታወክበት ጊዜ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም ተመሳሳይ ችግር ገጥሞት እንደነበር አያይዞ ጠቅሷል፡፡

በተያያዘም የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስትር የሆኑት አቶ ይሳቅ ያሬድ “ይህ የሚያሳየዉ “የኢትዮጵያ መንግስት ለቴክኖሎጅ ያለዉን ባዕድነትና የራሱ ቴሌቪዥን ዋጋ-ቢስነት ነዉ” ሲሉ ለሚዲያ ተቋማት መናገራቸዉን የጠቀሰ ሲሆን ፤ በማከልም “የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን ከይዘቱ ባሻገር የድምፅና ምስል ችግር ያለበት አማተር ስታንዳርድ ላይ እንኳ መድረስ ያልቻለ” ማለታቸዉን አያይዞ ጠቁሟል፡፡

የኤርትራ ቴሌቪዥን ዳሬክተር የሆኑት አቶ አስመላሽ አብረሀ በበኩላቸዉ “የኢትዮጵያ መንግስት የአየር ላይ ዉንብድና እዉነትን ለመጋፈጥ አቅም እንደሌላቸዉ ያሳያል” ማለታቸዉን አያይዞ ጠቅሷል፡፡

የኢሳት ቴሌቪዥን ስርጭት መጀመርን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት የሳተላይት ስርጭት ማፈኛ ቴክኖሎጅ ወደ ሀገር ቤት ማስገባቱን እና የኢሳትን አንዳንድ ፕሮግራሞች ማስተላለፍ በመጀመሩ የኤርትራ ቴሌቪዥን ከዚህ በፊትም መታወኩን የጠቀሰዉ የኢሳት ዘገባ ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከአረብ-ሳት ወርዶ እንደ ነበር የጠቆመ ሲሆን ፤ አያይዞም የኢትዮጵያ መንግስት “የኤርትራን ቴሌቪዝን አላዉክም” በማለት ስምምነት መፈፀሙን ተከትሎ በሰኔ ወር ወደ አረብ-ሳት መመለሱን አስታዉሷል፡፡

ኢሳት በዚህ ዘገባዉ እንደጠቆመዉ የኢትዮጵያ መንግስት ይህን ስምምነት ከመቀበሉ በፊት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሚያሰራጨዉን የኤርትራ ተቃዋሚወች ፕሮግራም ለማቋረጥና በምላሹም በኤርትራ ቴሌቪዥን በኩል የሚሰራጨዉን የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዋሚወች ፕሮግራም እዲያቋርጡ በተለይም የኢሳትን ፕሮግራሞች ማስተላለፋቸዉን እንዲያቆሙ የኤርትራ መንግስትን  ጠይቆ የነበር ሲሆን ፤ የኤርትራ መንግስት ግን አናቋርጥም!! ከፈለጋችሁ የኛን ተቃዋሚዎች ፕሮግራም በቀን ለ24 ሰዓት እናዳሻችሁ አሰራጩት በማለት ጥያቄዉን ውድቅ ሊያደርገዉ ችሏል፡፡

 

ጋዜጠኛ ታደሰ እንግዳዉ የተገደለዉ በመንግስት እጅ ነዉ ተባለ


Image

ጋዜጠኛ ታደሰ እንግዳዉ

የኢህአፓ ድምፅ የሆነዉ ፍኖተ ህብረት ሬድዮ በነሐሴ 5/2004 ዘገባዉ ለሕዝብ ይፋ እንዳደረገዉ የጀርመን ድምፅ የአማርኛ ፕሮግራም ባልደረባ በመሆን ለረጅም ጊዜ ያገለገለዉ ጋዜጠኛ ታደሰ እንግዳዉ ሐምሌ 7 ቀን 2004 ዓ.ም የደረሰበት እና ለህልፈተ ሕይወት የዳረገዉ ከባድ የመኪና አደጋ ድንገተኛ ሳይሆን ሆን ተብሎ በመንግስት የደህንነት ሰዎች የተቀነባበረ የግድያ ሴራ ነዉ ብሏል ፡፡

ጋዜጠኛ ታደሰ እንግዳ ሐምሌ 6/2004 በወንድሙ የምረቃ በዓል ላይ በሐዋሳ ዩንቨርሲቲ ተገኝቶ በማግስቱ ማለትም በሐምሌ 7/2004 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ በሚመለስበት ሰዓት በመንገድ ላይ የመንግስት የደህንነት አካላት አስቁመዉ ማንነቱን ከጠየቁ በኃላ “አንተ ነህ የምታስቸግረን” በማለት ዝተዉበት ነበረ ያለዉ የፍኖተ ሕብረት ዘገባ ዝዋይ ለመድረስ 40 ኪሎሜትር ሲቀረዉ አንድ ከባድ የጭነት መኪና ሆን ብሎ በመግጨት ጋዜጠኛዉን ለሞት ዳርጎታል ብሏል፡፡

ከአደጋዉ በኃላም ለምርመራ በሚል ሰበብ ጋዜጠኛዉ የህክምና እርዳታ እንዳያገኝ የመንግስት የደህንነት ሐይሎች ያስተጓጎሉት ሲሆን ፤ በመጨረሻም ጋዜጠኛዉ ሊሞት ችሏል ሲል ዘገባዉ ጠቁሟል፡፡

የጋዜጠኛዉን መኪና የገጨዉ ከባድ መኪና ታርጋ አልነበረዉ ሲል የጠቆመዉ የፍኖተ ህብረት ዘገባ ይህ የወያኔ ሴራ ለመሆኑ አንዱ አመላካች ነዉ ብሏል፡፡

በመጨረሻ የወያኔ መሪዎች ለአፈናና ግድያ ያሰለጠኑዋቸዉ ደህንነቶች በአደባባይና በስዉር የሚፈፅሙትን ግድያ ለማስቆምና ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብ ህዝቡ በመተባበር መንቀሳቀሰ እንዳለበት በዘገባዉ ተጠቁሟል፡፡

 

 

Ethiopia/በዋልድባ ገዳም መከራና እስሩ ቀጥሏል ፤ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት መነኮሳቱ ተጠያቂ ሆነዋል


Imageኢሳት አንድ በገዳሙ ዉስጥ የሚኖሩ መነኩሴ ጠቅሶ እንደዘገበዉ በዋልድባ ገዳም አሁንም መከራና እስሩ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ፤ መነኮሳቱም እሮሮአቸዉን እያሰሙ ይገኛል፡፡

እኒህ አባት በስልክ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ እንደተናገሩት ባለፈዉ ሳምንት አርብ እለት የመነኮሳት ቤት ሲፈተሽ የዋለ ሲሆን ፤ በመጨረሻም አባ ወ/ጊወርጊስ እና አባ ወ/ማሪያም  የሚባሉ መነኮሳትን ይዘዉ ወደ ማይፀብሪ ወረዳ በመዉሰድ አስረዋቸዋል ብለዋል፡፡

በተጨማሪ በአሁኑ ሰዓት መንግስት የ49 መነኮሳትን ስም ዝርዝር አዉጥቶ እየፈለጋቸዉ ይገኛል ያሉ ሲሆን ፤ እኔም ከእነዚህ ዉስጥ አንዱ ነኝ ብለዋል፡፡ አያይዘዉም ከሚፈለጉት ዉስጥ ሶስቱን ማለትም አባ ገ/ስላሴን ፣ አባ ወልዴን እና አባ ገ/ማሪያምን በቁጥጥር ስር አዉለዋቸዋል ብለዋል፡፡

እኒህ አባት በቃለ-ምልልሱ እንደተናገሩት ማይበረ ከ28 በላይ የሚሆኑ መነኮሳት አባቶችና እናቶች ወጥተዉ ለምንድን ነዉ አባቶች እየታሰሩ ያሉት ብለዉ ለመጠየቅ ሙከራ ቢያደርጉም መንግስት ከተማ ገብተዉ በህዝብ እንዳይታዩ በማሰብ ገና በበረሀ በምንገድ ላይ እያሉ በማስቆም እናንተ ፖለቲከኞች ናችሁ ፣ ወደ ገዳሙ ሽፍታ አስገብታችኃል ፣  ወታደሮችን አስደብድባችኃል አስገድላችኃል ፣ ቡል-ዶዘሮችን አቃጥላችኃል በማለት መልሰዋቸዋል ብለዋል፡፡

አክለዉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞቱ እያላችሁ ታወራላችሁ ፣ ዳዊት ትደግማላችሁ ፣ መቁጠሪያና መቋሚያ እየጣላችሁ ትራገማላችሁ ፤ በእናንተ ምክንያት ይሄዉ ሁሉ ነገር እየተበላሸ ነዉ ፤ ለዚህም ተጠያቂ ናችሁ ብለዋቸዋል በማለት ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም እኒህ አባት እንደተናገሩት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መታመምና መሞት የገዳሙ መነኮሳት እንደ ምክንያትም እየተቆጠሩ ሲሆን ፤ በዚህም ምክንያት ብዙ ችግር እየደረሰባቸዉ ይገኛል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ሲያብራሩ በገዳሙ ጉዳይ ማመልከቻ እንዲያቀርቡ የተላኩት መነኮሳት ማመልከቻዉን በቀጥታ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ለማቅረብ ጥረት ሲያደርጉ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ዉስጥ የሚገኙ ሰዎች ሰድበዉና አሳዝነዉ  ስለመለሷቸዉ “በቃ ተዉት! እንግዲህ እነርሱም ስራቸዉን ጀምረዋል ፣ እግዚአብሔርም ስራዉን ጀምሯል” በማለት አባቶች ሱባኤ ገብተዉ ነበር ፤ ይህንን ተከትሎ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መታመም ሆነ ለደረሰባቸዉ ችግር እናንተ ተጠያቂ ናችሁ ፣ “እናንተ ምትሀታሞች” በማለት የሰደቡን ሲሆን በሰደፍም ደብድበዉናል ብለዋል፡፡   

በመጨረሻም እኒህ አባት ስለገዳሙ አጠቃላይ ወቅታዊ ሁኔታ ሲናገሩ ገዳሙ በትልቅ ችግር ላይ ይገኛል ያሉ ሲሆን ፤ የታሰሩት ታስረዉ የተረፉት መነኮሳት በረሀ በመዉረድ በየዋሻዉ ተቀምጠዋል ፤ ሆኖም በየዋሻዉ ወታደሮች እየመጡ ስለሚፈትሹ በጣም ተቸግረዋል ብለዋል፡፡  

 

ከኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰጠ የአስቸኳይ ሃገራዊ ጥሪ


by Eyouthm Abiyot on Thursday, 19 July 2012 at 10:25 •

መላው የኢትዮጵያ ህዝብና የዓለም ማህበረሰብ እንደሚገነዘበው ሁሉ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄም የአምባገነኑ የመለስ ዜናዊ ስርዓት እያከተመ እንደሚገኝ ይገነዘባል፡፡

የዓለማችን ተመሳሳይ ታሪኮች እንደሚዘክሩት ሁሌም በአምባገነኖች መዳፍ ስር የወደቁ ሃገራትና ህዝቦች ጨቋኞቻቸው ባልታሰበ ሁኔታ በሞት ሲሸኙ ቀጣዩ ሂደት በአብዛኛው ጊዜ እጅግ አሳዛኝና ወደባሰ አዘቅት ሲወስድ ታይቷል፡፡ በአንፃሩ ደግሞ አልፎ አልፎ በአንዳንድ ሃገራት በህዝቦች በሳል ትግልና መስዋዕትነት እንዲህ አይነቱን ፈታኝ አጋጣሚዎችን በአግባቡ በመጠቀም ወደ ህዝባዊ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት በመቀየር መልካም የታሪክ ትሩፋቶች ሆነው አልፈዋል፡፡

ከዚህም ታሪካዊ እውነታ በመነሳት የአምባገነኑ መለስ ዜናዊ ስርዓት ውድቀትን ተከትሎ የሚፈጠረውን የስልጣን ሽኩቻ ምን ያህል አሳሳቢ ሊሆን እንደሚችል በቀላሉ መገመት ይቻላል፡፡ አበው “ሌባ ሲሰርቅ ይስማማል፣ ሲካፈል ደግም ይጣላል” እንዲሉ ፤ በተለይም ሽኩቻው ላለፉት 21 ዓመታት በዙሪያው ባሰባሰባቸው ፈርጀ ብዙ ዘራፊ ቡድኖች መካከል ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ ይገመታል፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ይህ ዘረኛና እኩይ ሰው በማን አለብኝነትና በእብሪት በጎረቤት ሃገራት ላይ በወሰዳቸው አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነቶችና ወረራዎች ምክንያት ሃገራችንና ህዝባችን ሁሌም ለአደጋ እንዲጋለጡ አድርጓል፡፡ በዚህ ፈታኝ ወቅት የሚፈጠረውን ባለቤት አልባነት በንቃት የሚከታተሉና ለበቀል ያቆበቆቡ ጎረቤት ሃገራት የሁኔታውን አመቺነት በመጠቀም አሳፋሪ የታሪክ ጠባሳ ሊያሸክሙን ይችሉ ይሆናል፡፡

ከላይ ከተቀመጡት ግልፅ አደጋዎች በተጨማሪ እጅግ ብዙ አሳሳቢ ሁኔታዎችን ማንሳት ይቻላል፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ዋና አላማ አደጋዎችን ማመላከት ብቻ ሳይሆን በይበልጥ ይህንን የታሪክ አጋጣሚ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ በመጠቀም በኢትዮጵያ ህዝባዊ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት በዘላቂነት እንዲገነባ ማስቻል ነው፡፡

ይህንን እውነታ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድና በማስተዋል ከተጠቀምንበት ለእኛ ለኢትዮጵያውያንና ለምንወዳት ሃገራችን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ይከፍትልናል ብለን በፅኑ እናምናለን፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ በዚህ ፈታኝ ወቅት ለምንመኘው ታሪካዊ ድል በጎ አስተዋፅኦ ሊያደርጉ ይገባል የሚላቸውን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በአንድነት የሚያቀናጅ ሃገራዊ ጥሪ ከዚህ እንደሚከተለው ያቀርባል፡፡

1ኛ. ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ

መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ፆታ፣ እድሜ፣ ሃይማኖት፣ ጎሳና፣ ዘር ሳይለይ ለአለፉት ዘመናት በተለይም በአምባገነኖቹና በጨካኞቹ የመንግስቱ ኃ/ማርያምና የመለስ ዜናዊ ስርአቶች እንደ ባእድ ወራሪ በገዛ ልጆቹና ሃገሩ የግፍ ግፍ ሲፈፀምበት፣ ምድሪቱም በደም ጎርፍ ስትታጠብና፣ ሁሉም በሚችለውና በአቅሙ እነዚህን የሰው አውሬዎች ከላዩላይ ለማስወገድ ሲኳትንና በመራራ ትግሉና በውድ ልጆቹ መስዋዕትነት የመጀመሪያውን ጭራቅ አስወግዶ ሁለተኛውን እኩይ ሲተካ ሃዘኑ ያልጠናበትና ፈጣሪውን ያላማረረ ኢትዮጵያዊ የለም፡፡

ይሁንና ሁልግዜም ታሪክ እንደሚዘክረውና ድርሳናት እንደሚነግሩን “በጨለማ የነበረ ህዝብ ብርሃን አየ” ነውና በጭቆና ውስጥ ያለን እኛ ኢትዮጵያውያን ይዋል ይደር እንጂ ነፃነታችንን መቀዳጀታችን ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ እነሆ ዛሬ የአምባገነኑ መለስ ዜናዊ ጨቋኝ ስርዓት የጀመረውን የግፍና የጥፋት መንገድ ሳያጋምስ በሃያሉ የኢትዮጵያ አምላክ እጅ ለፍርድ ተይዟል፡፡

ይሁን እንጂ ይህ እኩይ ስርዓት በህዝባችን መካከል የዘራቸው የጥላቻ፣ የበቀል፣ የክህደትና፣ የመለያየት መርዞች ስራቸውን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ በተለይም የብሔርተኝነት፣ የጎሰኝነት፣ የጎጠኝነትና፣ ብሎም የመንደርተኝነት መርዙ ምን ያህል የከፋና የከረፋ መሆኑን በአለፉት 21 የሰቀቀንና የጭንቅ ዓመታት እሬት እሬት እያሉን አጣጥመናቸዋል፡፡ ይበልጡንም ወንድማችንና ጋሻችን የሆነውን ጨዋውን “የትግራይ” ህዝብ በስሙ በመነገድ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠልና ሌሎች ብሄረሰቦች በጠላትነት እንዲነሳሱበት ለማድረግ ያልተቆፈረ ጉድጓድና ያልተሸረበ ምድራዊ ሴራ አልነበረም፡፡ ነገር ግን የህዝባችን አንድነትና ፍቅር የተሸረበበት ድር የአለፉት እልፍ አእላፋት ትውልዶች ለአንድነትና ለነፃነት በተሰዋ ንፁህ ኢትዮጵያዊ ደም በመሆኑ የከፋፋዮቹ ህልም እስከ አሁኗ ሰአት ድረስ ሊሳካ አልቻለም፡፡ የተመኙትንም ኢትዮጵያን የማፍረስና ህዝቧን የማጫረስ ፋሽስታዊ ተልእኮና ህልም ሳያሳኩ ወደ ጥልቁ “በአቦሸማኔ” ፍጥነት እየተምዘገዘጉ ይገኛሉ፡፡

በአሁኑ ሰአት በሃገራችን የተፈጠረውን ታሪካዊ ክስተት የአምባገነኖች ቡድን እንዳይቀለብሰውና ወደ ህዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ሊደረግ የሚገባውን ታሪካዊ ጉዞ እንደለመዱት ለእኩይ አላማቸው መጠቀሚያነት እንዳያውሉት ህዝባችን ነቅቶ ሊጠብቅ ይገባል፡፡ ሁላችንም ልክ እንደ አባቶቻችን ሃገራችንና ህዝባችንን ከሁሉም ነገር በላይ በማስቀደም፤ በአንድነትና በፍቅር ፀንተን በመቆምና፤ በማስተዋል እኩዩ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ የዘራውን የመጠፋፋት መርዝ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ከስር መሰረቱ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማፅዳት ታሪክ የጣለብን አደራና ፈተና ነው ብሎ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ በፅኑ ያምናል፡፡

ስለዚህም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላቶቹ ያቀበሉትን የመለያየት አጀንዳ በማጥፍት፤ ለነፃነቱ መከበር በአንድነት በመቆም ለህዝባዊ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ምስረታ በፅኑ እንዲታገልና ከእጁ የገባውን ይህን ታሪካዊ አጋጣሚ ዳግም ለአምባገነናዊ ስርዓት አሳልፎ እንዳይሰጥ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ወገናዊ ጥሪውን ከታላቅ አክብሮት ጋር ያቀርባል፡፡

2ኛ. ለሃይማኖት ተቋማት

“ኢትዮጵያ የሃይማኖት ደሴት ናት!” የዓለም ታሪክና ታላላቆቹ የየዕምነቱ መሪዎች ከተናገሩልን፤ የሃይማኖት ድርሳናትም በትልቁና በደማቁ ከከተቡልንና ዛሬም የዓለም ህዝቦች በአድናቆትና በግርምት ከሚመለከቱት ማንነታችን መካከል ዋነኛው መገለጫችን ነው፡፡ እኛም ኢትዮጵያውያን በሁሉም ሃይማኖቶቻችን በመከባበርና በመቻቻል በአንድነት የኖርንባትና የምንኖርባት የቅድስት ሃገር ኢትዮጵያ ባለቤቶችና ጨዋ ህዝቦች መሆናችንን በኩራት የምንናገረው ሃቅ ነው፡፡ እንዲሁም ይህን ማንነታችንን በተለያየ ጊዜና ዘመናት ለአደጋ የሚያጋልጡ ክስተቶች እንደነበሩና አባቶቻችን በድል አድራጊነት እንደተወጡት እናውቃለን፡፡ እነሆም ዛሬ በእኛ ዘመን በተለያዩ አጋጣሚዎች ይህን ኩራታችንን ለመናድ የተለያዩ ትንኮሳዎችን አስተናግደናል፡፡ ይህም አልበቃ ብሎ የሃገሪቱን የመንግስት ስልጣን የያዘው የአምባገነኑ የመለስ ዜናዊ አስተዳደደር በሃይማኖት ተቋሞቻችንና ይዞታዎቻችን ቀጥተኛ ትንኮሳ፣ ወረራና፣ ግድያ ሲፈፅምብን ኖሯል፡፡እየፈፀመም ይገኛል፡፡ ይህንንም በእውነተኛና ታማኝ የሃይማኖት አባቶች፣ ምዕመናንና፣ ተቋማት ላይ ሲፈፀም የነበረውን ግፍና መከራ እስከ አሁን ድረስ በፅናት እየታገልን እንገኛለን፡፡ በዚህም ህዝባችን ድል እንደሚቀዳጅ እርግጠኞች ነን፡፡

ወገኖቻችን ! ዛሬ ሃገራችን ኢትዮጵያ እጅግ አሳሳቢ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች፡፡ ስለሆነም እንደ አንድ ኩሩና ጀግና ህዝብ በዚህ ሰአት ለገጠመን ሃገራዊ ፈተና ቅድሚያ በመስጠት እስከዛሬ በፅናት የታገላችሁላቸውን ሃይማኖታዊ ክብርና መብቶቻችሁን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በጋራ ያለምንምና ማንም ተፅዕኖ የምንጎናፀፈው በሃገራችን ሰላም፣ዲሞክራሲና፣ ፍትህ ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም ለዚህ ህዝባዊ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ቅድሚያ በመስጠት ትኩረታችሁን፣ ፀሎታችሁንና፣ ድጋፋችሁን በሃገራችን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲመሰረት ለምንፈልገው ሁሉንም ወገኖች በእኩልነት የሚያሳትፍ ስርዓት ምስረታ ታደርጉ ዘንድ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ወገናዊ ጥሪውን ከታላቅ አክብሮት ጋር ያቀርባል፡፡

3ኛ. ለፖለቲካ፣ ለሲቪክና፣ ለግብረ-ሰናይ ድርጅቶች በሙሉ

ለአለፉት ዘመናት ደከመንና ሰለቸን ሳትሉ ለሃገራችሁ እድገት፣ ለህዝባችሁ አንድነትና ነፃነት፣ እንዲሁም ለዲሞክራሲያዊ ህዝባዊ መንግስት ምስረታ ሌት ከቀን የባዘናችሁና በዱር በገደሉ የተንከራተታችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሲቪክ ተቋማት፣ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶችና፣ የሙያ ማህበራት በሙሉ እነሆ የታገላችሁለትን አላማ አጨናግፎና እናንተንም ለእስር፣ ለአካል ጉዳተኝነት፣ ለስደትና፣ ለሞት ይዳርጋችሁ የነበረው የእኩዩ የመለስ ዜናዊ ስርዓት ህልውና እያከተመ ይገኛል፡፡

ምንም እንኳ ይህ የአምባገነኖች ስርዓት የመጨረሻው ስንብት ላይ ቢሆንም “ሌባ ሲሰርቅ…..” እንደሚባለው ሁሉ እየተፈጠረ ያለው የሃይል ሚዛን መዛባት የዘራፊውን ቡድን እርስ በእርስ እንደሚያባላቸውና አሸናፊው የአውሬው ክንፍ ዝርፊያውን ለማስቀጠል መንበሩን ለመያዝና መሪውን ወደ ፈለገው ለመጠምዘዝ እንደሚሞክር እሙን ነው፡፡

ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ከህዝቡ ጋር ካለው ቀጥተኛ ግንኙትና ተጨባጭ መረጃ በመነሳት የመለስ ዜናዊ የግፍ አገዛዝ ያንገሸገሸው ህዝባችን በሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች ህዘባዊው ቁጣ ሊፈነዳ ጫፍ ላይ የደረሰ መሆኑን ያስገነዝባል፡፡ ስለሆነም እስከ ዛሬ ደንቃራ ሆኖ አንድነታችሁንና ህብረታችሁን የተፈታተነውን የንድፈ ሃሳብ ልዩነት ወደጎን በመተው ለማይቀረው ህዝባዊ ቁጣና ለህዝባዊ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ አፋጣኝ የጋራ አስተዋፅኦና ድጋፋችሁን ታበረክቱ ዘንድ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ወገናዊ ጥሪውን ከታላቅ አክብሮት ጋር ያቀርባል፡፡

4ኛ. ለመምህራን፣ ለተማሪዎች፣ ለአርሶ አደሩ፣ ለሲቪል ሰራተኛውና፣ ለነጋዴው የህብረተሰባችን ክፍሎች በሙሉ

የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ እስከዛሬ ድረስ የህልውናችን መሰረት በመሆን፤ ከትውልድ ትውልድ ታሪካዊ ሃላፊነታችሁን እየተወጣችሁ በተቻላችሁ መንገድና አቅም ሁሉ አምባገነኖችን በመታገል ላሳያችሁት ፅናትና ተጋድሎ ታላቅ አክብሮቱን ይገልፃል፡፡ በተመሳሳይ እንደ ቀደሙት ታሪካዊ ክስተቶች ሁሉ ዛሬም በጨካኙና በአምባገነኑ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ መወገድ ተከትሎ ሊፈጠር የሚችለውን አለመረጋጋትና ህገወጥነትን በመገንዘብ አካባቢያችሁን፣ ሃገራችሁንና፣ ማህበረሰባችሁን ከማንኛውም ጥቃትና ምዝበራ ነቅታችሁ ትጠብቁ ዘንድ፤ እንዲሁም ለሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ በሚደረገው የህዝብ ትግል ፍፁም ሰላማዊ በመሆ መንገድ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የተለመደውን ታሪካዊ ግዴታችሁንና ሃላፊነታችሁን ትወጡ ዘንድ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ወገናዊ ጥሪውን ከታላቅ አክብሮት ጋር ያቀርባል፡፡

5ኛ. ለሃገር መከላከያና ለፖሊስ ሰራዊቱ አባላት

ለአለፉት 21 ዓመታት አምባገነኑ የመለስ ዜናዊ መንግስት ያደርስባችሁ በነበረው ከፍተኛ ተፅዕኖ ምክንያት በህዝባችን ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍና መከራ ስታስፈፅሙ እንደነበራችሁ ይታወቃል፡፡ ይሁንና ዛሬ የአምባገነኑ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚወገድበት ወቅት መድረሱ እውን ሆኗል፡፡ ስለሆነም ይህ ታሪካዊ ክስተት ከማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል ይልቅ ለእናንተ ኢትዮጵያዊ ወገናችሁን ለመካስ የሚያስችል ልዩና መልካም አጋጣሚ ይዞላችሁ እንደመጣ እናምናለን፡፡

ይኃውም የሃገራችሁን ዳርድንበርና የህዝባችሁን ደህንነት በቅንነትና በታማኝነት የመጠበቅና የማገልገል ታላቅ ሃገራዊ ኃላፊነት በአግባቡ ትወጡ ዘንድ ያስችላችኃል ብለን እናምናለን፡፡ በተለይም በዚህ ወቅት ህዝባችሁንና ሀገራችሁን ከማንኛውም ጥቃትና አደጋ እንድትታደጉና ወደ ህዝባዊ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የሚደረገውን ፍፁም ሰላማዊ የህዝብ ትግል ከማንኛውም የአምባገነኖች ጥቃት ነቅታችሁ በመጠበቅና በመከላከል አኩሪ ታሪክ ትሰሩ ዘንድ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ወገናዊ ጥሪውን ከታላቅ አክብሮት ጋር ያቀርባል፡፡

6ኛ. ለብሔራዊ መረጃና ደህንነት አባላት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የመረጃና የደህንነት አባላት ህዝብ የጣለባችሁን ወሳኝ ሃገራዊ አደራ በአግባቡ እንዳትወጡና አምባገነኑን መለስ ዜናዊንና ስርአቱን ለመጠበቅ ሲባል ብቻ በግዴታ የኢትዮጵያን ህዝብ በማሳደድ አስነዋሪ ተግባር ውስጥ እንድትዘፈቁ መደረጉን በአለፉት 21 ዓመታት በህዝባችን ላይ የተፈፀሙት ግፎች ያረጋግጣሉ፡፡ ነገርግን ዛሬ ያ የጨቋኙ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ እንደሚወገድና በምትኩም ህዝባዊ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት የሚመሰረትበት አዲስ የታሪክ አጋጣሚ እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ለእናንተም እኩል እየመጣላችሁ መሆኑን እናምናለን፡፡
ስለሆነም እናንተም ይህን ታሪካዊ አጋጣሚ በአግባቡ በመጠቀም መላው ህዝባችሁንና ኢትዮጵያ ሃገራችሁን ከማንኛውም የውስጥና የውጭ ጥቃት በንቃት በመጠበቅ፣ እንዲሁም አሁን በጨቋኙ የመለስ ዜናዊ ስርዓት ውስጥ የተፈጠረውን የሃይል ክፍተት በመጠቀም በሃገራችን ውስጥ ሊከሰት የሚችለውን የስርዓት አልበኝነት ትከላከሉ ዘንድ ከወዲሁ ልናሳስብ እንወዳለን፡፡ በአጠቃላይ ህዝባችን ለሚያደርገው ፍፁም ሰላማዊ የሆነ የህዝባዊ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ መንግስት ምስረታ ሂደት የበኩላችሁን አስተዋፅኦ በማበርከት ታሪካችሁን በክብር መዝገብ ላይ ታሰፍሩ ዘንድ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ወገናዊ ጥሪውን ከታላቅ አክብሮት ጋር ያቀርባል፡፡

7ኛ. ለጋዜጠኞችና ለሚዲያው ማህበረሰብ በሙሉ

ከአምባገነኑ የመለስ ዜናዊ አውሪያዊ አገዛዝ ጋር ፊት ለፊት በመጋፈጥ ለእውነት፣ ለዲሞክራሲ፣ ለፍትህና፣ ለነፃነት አኩሪ ተጋድሎ እያደረጋችሁ ለምትገኙት ክቡራንና ክቡራት የኢትዮጵያ ነፃ ሚዲያ አባላት፤ እንዲሁም አቅማችሁ በፈቀደው ሁሉ መረጃ በመስጠትና በማስተለላለፍ ለተሳተፋችሁ “የእውነት ብርሃኖች” ሁሉ ዛሬ በሃገራችን እየተፈጠረ የሚገኘውን አዲስ የታሪክ ክስተት በንቃት እየተከታተላችሁ እንደምትገኙ እናምናለን፡፡

እንደሚታወቀው ምንም እንኳ የአምባገነኑ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ ፍፃሜ የተቃረበ ቢሆንም ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ሃገራችንን ወደ አዲስ የነፃነት፣ የዲሞክራሲና፣ የፍትህ ምዕራፍ ለማሸጋገር ይቻል ዘንድ በሁሉም አቅጣጫ ብልህነት የተሞላበት አካሔድ እንደሚያስፈልገው አያጠራጥርም፡፡

ስለሆነም ይህንን ታሪካዊ ክስተት ተከትሎ የሚከሰተውን ውጥንቅጥ በማጋለጥና በማጥራት፤ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ህዝብና ለዓለምዓቀፉ ማህበረሰብ ትክክለኛና ሚዛናዊ መረጃ በወቅቱ በማድረስ ህዝባችን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለሚያደርገው የህዝባዊ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ትግል የበኩላችሁን አስተዋፅኦ በማድረግ የዜግነት ግዴታችሁን ትወጡ ዘንድ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ወገናዊ ጥሪውን ከታላቅ አክብሮት ጋር ያቀርባል፡፡

8ኛ. ለመላው ኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ አባላትና ደጋፊዎች፤ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ወጣቶች በሙሉ

ለአለፉት 21 ዓመታት ሲያሰቃየን የኖረው እኩዩ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ እያከተመለት እንደሚገኝ እርግጥ ነው፡፡ በመሆንም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወጣት ከፊት ለፊታችን ተሰቅሎ የሚታየንን የአምባገነኖችን ዘላለማዊ የጨለማና የውርደት መቃብር በጉጉትና በተስፍ እየተመለከትን፤ ከውልደታችን ጀምሮ የምንናፍቀውንና የምንጓጓለትን ነገር ግን ልናየውና ልንኖርበት የተከለከልነውን ህዝባዊ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት የመገንባት መልካም አጋጣሚ በእጃችን እንደገባ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ይረዳል፡፡ እንዲሁም ከሁሉም በላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ያለምንም ገደብና ቅደመ ሁኔታ በእኩልነት፣ በነፃነትና፣ በፍትሃዊነት የምንኖርባትን ታላቋን ኢትዮጵያ ማየት የወጣቱ ትውልድ ታለቅ ራዕይ መሆኑንና የመገንባቱም ዕጣ-ፋንታ ዛሬ በትክሻው ላይ እንደወደቀ እናምናለን፡፡

ነገርግን እስከ አሁን ድረስ እግር በእግር እየተከተለ የነፃነት፣የፍትህ፣የእኩልነትና፣ የዲሞክራሲ ፍላጎትና ተስፋችንን እያመከ የሚገኘው የአምባገነኖች ርዝራዥ ሃይል ተጠቃሎ ከእነ እኩይ ምግባሩና ሴራው ከሃገራችንና ከህዝባችን ጫንቃ እስኪወገድ ድረስ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ የትግል መስክ እንደ አቅማችንና ችሎታችን ተሰልፈን በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ መስዋዕትነት እየከፈልን የምንገኝ ወጣቶች ሁሉ ወደ ዲሞክራሲያዊ ህዝባዊ ስርዓት ግንባታ የሚደረገው ጉዞ ግቡን እስኪመታ ድረስ በፅናትና በቁርጠኝነት ትግላችንን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እስከመጨረሻው እንድንቀጥል የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ለማሳሰብ ይወዳል፡፡ ስለሆነም በዚህ የታሪክ አጋጣሚ በአምባገነኖች መንደር ሊፈጠር የሚችለውን ትርምስ ተገንዝበን ለውጡ “የጉልቻ መለዋወጥ” ብቻ ላይ ተገድቦ ሂደቱ ዳግም የትውልድ ተስፋችንን እንዳያጨልምብንና ዳግመኛ ሃገራችን በሌላ አምባገነናዊ ስርዓት እንዳትጠለፍ ሂደቱን በንቃት በመከታተልና ባሉት ፍፁም ሰላማዊ እንቅስቃሴዎች በሙሉ ግንባር ቀደም ተሳታፊዎች በመሆን ሃገራችንን ወደ ምንመኘው ህዝባዊ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለማሸጋገር በአንድነት እንድንቆም የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ወገናዊ ጥሪውን ከታላቅ አክብሮት ጋር ያቀርባል፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ!

Posted on: http://escondera.blogspot.com/

The Ethiopian Government True Picture: Wikileaks in Reverse


Secrets the government was keeping from us through denials, brazen lies, and spins are out. Ethiopians have known all along what was going on; unfortunately, not so the outside world. Information Minister Bereket [of the Interahamwe fame] late last week delivered with an air of arrogance a panicky communiqué that inadvertently revealed the true nature of the beast. If you don’t believe us just read this piece with commentary brought to you by the only government ‘independent’ paper Ethiopian Reporter. We have commented in parentheses in the hope of making life a little bit easier for us all. Here we go:

“In response to the rumors that were spreading like wildfire, on Thursday, Bereket Simon, head of the Office for Government Communication Affairs (OGCA), tried to break the deadlock of his government by saying, ‘Meles is in a stable condition.’ Bereket began his press conference by saying that he came to brief the media on the current activities and developments which are being undertaken by the government. [Did he mean he was so busy with state affairs that he had to postpone meeting the press three times?] “As you know, we, the communications office, have pledged to hold a press conference and meet with media every two weeks and the Prime Minister will do so every two months,” Bereket said. However, despite all promises, OGCA called a press conference only twice in the last eight months. In addition, it has been more than a year since the PM held a press conference. [The reason being the government is accountable to no one, need not keep its promises and there is no free press in the country.]

“After being asked about the health of the PM, Bereket told members of the media that the doctors of Prime Minister Meles Zenawi have instructed the PM to take a long leave. [The dead do tend to take “long leave”, too. At any rate, alive or dead Meles’ aura could never be the same. After the desired time elapses the next news cycle will be, We thought the Prime Minister's health showed improvement BUT he expired late last night very unexpectedly.]

“[… Bereket] said that the weight loss that was observed during the G20 Summit in Mexico was due to the lengthy travel to the Central American country. [Did Bereket mean the air travel from Addis to Mexico actually caused weight loss? He must be thinking everyone except himself is easy to fool! It is possible Meles was undergoing chemotherapy – only a few months ago he had made a revealing statement in the context of Western economic prescriptions that “the medicine … turned out to be worse than the disease." What could that possibly be if not some sort of radiation he is being subjected to? It could also be he was poisoned in Mexico. According to Ethiomedia “American officials had asked a prominent Ethiopian American medical doctor to help treat Prime Minister Meles Zenawi after the premier collapsed following his return from the G-20 Summit in Mexico last June.” Whether by an agent from a foreign country or from within his own party is unimportant at the moment. Two comments, however, have piqued our interest. One was a comment by Dan Connell in the New York Times where he said “Ethiopia’s prime minister, Meles Zenawi, “has been cranking up the rhetorical level against Eritrea since last spring,” Mr. Connell said, with Mr. Zenawi openly calling for a change of governments in Eritrea. Meanwhile, Eritrea has vowed to defend itself, and, Mr. Connell said, “Whatever happens in this particular case will either happen right away or be reflected in another clandestine op aimed at” Ethiopia’s capital.”

Another comment by Sebhat Nega [founding member of the ethnic minority party] to the VOA was that “the government has been functioning normally during Meles’ absence and that the ‘system does not depend on one person.’” [Is Sebhat suggesting that Meles may have monopolized power and enjoyed the spotlight more and more that it is time that he be moved on to his deserved place? Is it also the case that Meles’ worsening human rights record and corruption is giving the US a bad breath Obama Administration would like to freshen up before the upcoming US elections? Ethiopian-Americans should not be deceived by such empty gestures!]

“Apart from that, the mounting pressures that come from implementing the GTP, continental affairs and global affairs all resulted in the PM’s fatigue. Of course, observers had earlier suggested that Meles ought to take a rest even before the 2010 elections. [This litany that he was overworked goes to show that Meles is not a good leader; good leaders delegate and recruit and enable other good leaders. The reality is that Meles could not stand a competitor. Remember that he did not show up for a public debate during the run up to the 2005 elections!]

“… When asked about the sickness and the current whereabouts of the PM, Bereket replied [] that it was not important to reveal the type of disease since there is a doctor-patient confidentiality. ‘There is also no need for mentioning his whereabouts,’ Bereket added. He was also unable to say how long the leave of absence would last but said ‘it will not be too long’ and that ‘we are expecting him to be back in days.’ According to Bereket, the leadership is stable and the country will continue to be a powerhouse in the Horn of Africa region. Asked about the secrecy surrounding the whole thing, Bereket responded by saying: “The communications office did not bother to release the information about the PM’s health since we did not want to make a public relations piece out of it. In addition, it is the culture of our party.” [Secrecy is his party’s culture? Meles is leader of a party and not leader of a nation? Bereket and his minority party are not obligated by law to tell the nation the whereabouts of the Prime Minister? Is that absurd or what?]

“Berket also spoke about the power vacuum that many are wondering about. ‘I don’t think there is any political crisis among the Ethiopian Peoples’ Revolutionary Democratic Front (EPRDF).’ [How deceptive of him to ascribe the goings-on to EPRDF instead of to TPLF? Ethiomedia and other sites have listed 6 or 7 in the leadership at the moment on the verge of deciding the next phase of events in our country. Shamefully, every one of them is a Tigrayan. This after 21 years indeed should be an embarrassing thing and a matter of dishonor to all reasonable Tigrayans and a disgrace to the rest of us!] Incidentally, one Tigrayan scholar recently injected into the discourse the word “EPRDFites” instead of the factual TPLFites!]
“Maybe, if there is anyone who has such a kind of wishes, they are making a wrong assumption. ‘With Meles on sick leave, I don’t think it creates any problem for the national security as it is a temporary leave. One of the problems was in Somalia but at this time Al-Shabaab is getting weak. [How many times have we heard Al-Shabab has been flushed out of Somalia?] The other issue might be related with Eritrea. Last time, Ethiopia has carried out proportional retaliation on Eritrea for the action the latter carried out on the Ethiopian border. We conveyed a loud and clear message. We don’t expect any permanent confrontation with them.’ Bereket said that more than ever, the country is strong enough to defend its territorial integrity and sovereignty. ‘I have no doubt that there will be any threat regarding stability,’ he said. [Repeating “stability” “weak Al-Shabab” “peace with Eritrea” is to assuage American fears, NOT Ethiopians' for the sole reason that most of the instability is deliberately caused by the regime itself. Remember, Muslims demonstrating at Maskal Square a while back when VOA’s Peter Heinlein was arrested for covering the event? Such situations are designed to make the ruling minority indispensable to Americans and at the same time siphon off fear-generated money. America cares less about human rights abuses or eviction and unlawful imprisonment of citizens or stolen aid money. America seems to be more interested in keeping the Drone Base in Arba Minch and recruiting someone like Meles to run errands as US military presence in the region continues to grow than worrying about the long term wellbeing of Ethiopians. Outsourcing such covert wars hides the facts from US public and conveniently delegates crimes committed against humanity; moreover, deaths will be confined to Ethiopians. In other words, a deal of this nature is cheaper for the US and lucrative and politically expedient for Ethiopian rulers.]

FREE ESKINDER NEGA, REEYOT ALEMU, AND ALL PRISONERS OF CONSCIENCE NOW!

Posted on: http://etrecycler.blogspot.com/

የሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ግልፅ መልዕክቶች


የተከበራችሁ መላው የሃገራችን ህዝቦች ፤ ሰላምታችን እና መልካም ምኞታችን ከሁሉም ነገር ይቀድማል፡፡ ይህን መልእክት ለእናንተ ለወገኖቻችን እንድንፅፍ ያነሳሳን ምክንያት አንድም በሃገሪቱ በመንግስትም ሆነ በማንኛውም ዜጋ ስለሚከናወኑ ጉዳዮች መረጃ የማግኘት መብታችሁን ከማክበር ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ሰሞኑን የራዲዮ እና የቴሌቪዥን ጣቢያዎቻችን ከወትሮው ለየት ያለ የጭንቅ ቀን አይነት መረጃ ማቅረብን በማዘውተራቸው አንድ ለህዝብ ግልፅ ሊሆን የሚገባ እውነታ በመኖሩ ይሄንን ሃላፊነት ለመወጣት ነው፡፡

አብዛኞቻችሁ እንደምታውቁት የሃገራችን ህገመንግስት በግልፅ ካስቀመጣቸው ድንጋጌዎች ውስጥ የሃይማኖት ነፃነትና የመንግስትንና የሃይማኖትን መለያየት ይገኝበታል፡፡ ይህ ድንጋጌ በሃገሪቱ የሚገኝ ማንኛውም ሰው በፈለገው የማመንንና ሲፈልግም በምንም አለማመንን መብት ያረጋገጠ በመሆኑ በልዩ ክብር የምንጠብቀው ነው፡፡ ነገር ግን ይህ በህገመንግስቱ ላይ በደማቅ ተፅፎ የሚገኘው ድንጋጌ በአስፈፃሚዎች አማካኝነት ቀስ በቀስ እየተሸረሸረ በመምጣት እምነትህን እኔ ካልመረጥኩልህ የሚባልበት ደረጃ ላይ የተደረሰበት ክስተት ሃምሌ 2003 ተፈጠረ፡፡ የህገመንግስት ጥሰቱንም በቡራኬ ይፋ ያደረጉት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትሩ ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም ሲሆኑ ጉዳዩንም ሰው በተሰበሰበበት በጊዮን ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነበር፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ ሸኽ አብደላ አልሃረሪ በሚባል ግለሰብ የተመሰረተና አመለካከቱ በገባባቸው ሃገሮች በሙሉ ትርምስ እና የእርስ በእረስ ፍጅት በማስከተል የሚታወቅ ‹አህባሽ› የተባለ እራሱን በእስልምና ስም ሸፍኖ የሚንቀሳቀስ አንጃ አለ፡፡ የአንጃውን ውስጠ ሚስጥር ሳይረዱት ቀርተው ይሆን ወይንም ያላወቅነው ሚስጥር በመኖሩ ክቡር ሚኒስትሩ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ ‹‹ይህንን አመለካከት በሃገራችን ለማስፋፋት እንዴት ብንሰራ ይሻላል በሚል መንግስት ለረጅም ግዜ ሲመክር ቆይቷል›› ሲሉ እጅግ አሳዛኝና አስተዛዛቢ ንግግር አደረጉ፡፡ የአንጃው ተወካይና ከፍተኛ አራማጅ ከቤሩት ተጉዘው በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ በመገኘት ካደረጉት ንግግር ደግሞ ‹‹ወደኢትዮጵያ በነዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም ተጋብዤ ስመጣ ነገሩን ለትንሽ ግዜ ለማሰብ ሞክሬ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን እምነት (አህባሽን) ለማስፋፋት መወሰኑ ትልቅ እርምጃ ነው›› በማለት መንግስት ሃይማኖት ሊመርጥልን እና በግልፅ የተቀመጠውን ህገመንግስታዊ ድንጋጌ በራሱ ሊንደው መነሳቱን አረዱን፡፡ እነዚህ ንግግሮች ደግሞ በደምፅ ተቀድተው ከበርካታ ህዝብ ዘንድ በተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች ደርሰዋል፡፡ ዛሬም ድረስ ለማንኛውም ሰው ማድመጥ ይቻላል፡፡

እስቲ አንድ ጥያቄ እንጠይቃችሁ፡፡ ለዘመናት የኖራችሁበትን እምነት መንግስት እና አስፈፃሚዎች በድንገት ተነስተው ‹‹እኛ ሌላ እምነት ለማስፋፋት አስበናልና እሱን መከተል አለባችሁ ብትባሉ ምን ይሰማችኋል? መልሳችሁስ ምን ሊሆን ይችላል?
ነገሩን ከባለስልጣናቱ ጋር በፊታውራሪነት ብዙውን ግዜ ደግሞ በታዛዥነት የሚያስፈፅመው ደግሞ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን መንፈሳዊ ህይወት በመምራት መንግስት የሰጠንን የሃይማኖት ነፃነት ሳይሸራረፍ እንዲከበር ጥብቅና ሊቆም የሚገባው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) አመራሮች ናቸው፡፡ የመጅሊስ አመራሮች ከህዝብ በሚሰበሰብ ገንዘብ እየተመሩ ለካንስ አስቀድመው የዚህ አዲስ እምነት ተከታይ እና አራማጅ በመሆን በህዝብ ላይ ሸፍጥ ሲሰሩ ኖረዋልና ይህንን ዘመቻ በይፋ ማፋፋም ጀመሩ፡፡ ነገሩ በዚህም ብቻ ሳያበቃ እያንዳንዱ የመስጂድ አሰጋጅ፤ አዛን አድራጊ እንዲሁም ሰባኪያንና ቁርአን አስተማሪዎች የዚህን እምነት ቀኖና ተምረው ተግባራዊ ካላደረጉ በስራቸው መቆየት እንደማይችሉ መጅሊሱ አውጆ በሰፊ ዝግጅት እና በህዝብ በጀት የእምነት ማስቀየር የግዴታ ስልጠና በመላ ሃገሪቱ ተጀመረ፡፡ ስልጠናውን አልከታተልም የሚል ወይንም ቀኖናውን የሚነቅፍ ‹‹አክራሪ›› እና ‹‹ፅንፈኛ›› እየተባለ ይብጠለጠል ጀመር፡፡ በመጅሊሱ መተዳደሪያ መሰረት የአመራሮቹ ምርጫ በየአምስት አመት መደረግ እንዳለበት የተደነገገ ቢሆንም ላለፉት 12 አመታት ህዝበ ሙስሊሙ ምርጫ የሚባል ነገር ባላየበት ሁኔታ እርስ በእርስ እየተሷሷሙ የመጡት አመራሮች የህዝብን ዝምታ ከሞት በመቁጠር እምነት ማስቀየር ዘመቻ ከባለስልጣናት ጋር በመሆን ተያያዙት፡፡ መጅሊሱ ከዚህም አልፎ ረዳት አልባዎች የሚረዱበት፤ ቀባሪ ያጡ የሚገነዙበትና የሚቀበሩበት፤ ከመዋእለ ህፃናት እስከ ኮሌጅ ድረስ ትምህርት ቤት እና ሆስፒታል ያለውን የአወሊያን ሚሽነሪ ትምህርት ቤት 50 መምህራንና ሰራተኞችን በአንድ ቀጭን ትዕዛዝ ከስራ አሰናበተ፡፡

የተከበራችሁ የሃገራችን ዜጎች ፤ እነዚህ ሁሉ አይን ያወጡ የህግ ጥሰቶች ሲፈፀሙ ህዝበ ሙስሊሙ በውስጡ ከመቃጠል እና ውስጥ ለውስጥ ከማጉረምረም የዘለለ ምንም ያሳየው ነገር አልነበረም፡፡ የመብት ጥሰቱ እየጨመረ ሲመጣና የሚጥሱትም አካላት እንደመብታቸው በመቁጠር በግላጭ ህግን ሲጥሱ ከስምንት ወራት በፊት ህዝቡ በመሰባሰብ መመካከር ጀመረ፡፡ ተከታታይ ውይይቶች ከተካሄዱም በኋላ በአንድ የአርብ ስግደት ላይ ጥያቄዎቻችንን ለመንግስት በማቅረብ መልስ ማስገኘት አለብን ከሚል ስምምነት ላይ በመድረስ ለችግሮቻችን ዋና መንስኤ የሆኑና ለመንግስት የሚቀርቡ ሶስት ግልፅ ጥያቄዎች ተለዩ፡፡ እነሱም፡-

1. በስልጣን ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች ያለምርጫ የመጡና ህዝቡን የማይወክሉ በመሆናቸው ህዝቡ በነፃ ፍላጎቱ፤ በገለልተኛ አስመራጮች እና በመስጂድ ደረጃ በሚመርጣቸው አመራሮች ይተኩልን፡፡

2. አህባሽ የተባለው እምነት እንደ ማንኛውም እምነት እራሱን ችሎ የመንቀሳቀስ መብት ይኖረዋል እንጂ በሙስሊሙ መስጂዶችና መዋቅር ውስጥ በግድ እንዲጫን ሊደረግ አይገባውም

3. አወሊያ የህዝብ ንብረት እንደመሆኑ መጠን እራሱን በአግባቡ ማስተዳደር ለማይችለው መጅሊስ መሰጠት የሌለበት ሲሆን ህዝብ በሚመርጣቸው የቦርድ አባላት ይተዳደር የሚሉ ጥያቄዎች እና 

4. ለነዚህ ጥያቄዎች መመለስ መንግስት አስፈላጊውን ትብብር ያድርግልን የሚል ነበር፡፡

እነዚህን ጥያቄዎች ለመንግስት ለማድረስና መፍትሄ ለማፈላለግ ደግሞ ህዝቡ በራሱ ፍቃድ 17 አባላት ያላቸውን ተወካዮች (ከሃገር ሽማግሌዎች፤ ከሃይማኖት ኣዋቂዎች፤ ከምሁራን እና ከሰባኪያን) አብዛኞቹ በሌሉበት በመጠቆም መረጦ ምርጫውን እንዲቀበሉ ጫና አሳደረ፡፡ ተወካዮቹም የህዝብን ጫና በመፍራት ጥቆማውን በመቀበል እና ከመላ ሃገሪቱ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የተፈረሙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የድጋፍ ፊርማዎችን በማስረጃነት በመያዝ እነዚህን ሶስት ጥያቄዎች ብቻ በመያዝ ምላሽ ለማፈላለግ ከላይ ታች ሲሉ ስምንት ወራት አለፉ፡፡ በሂደቱ ከክፍለ ከተማ እስከ የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት፤ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እስከ ሁሉም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ድረስ እነዚህን ጥያቄዎች በመተንተን በተለያየ ግዜ አቅርበዋል፡፡ ከዚህም አልፎ ቢያንስ ከሶስት ሚኒስትር መስሪያቤቶች ሚኒስትሮች ጋር ሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን መፍትሄው ግን እንደታሰበው ቀላል አልሆነም፡፡ የጥያቄዎቹ ግልፅነት፤ የአቀራረባቸው ሰላማዊነትና ህገመንግስታዊነት ግን ከኢህአዴግ ምክር ቤት ጀምሮ በተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ምስክርነት አግኝቶ ነበር፡፡ ነገር ግን ከሶስት ረጃጅም ቀጠሮ በኋላ ወሳኝ መልስ ይገኝበታል ተብሎ የሚጠበቅበት የካቲት 26 ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትሩ ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም እና ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሙሉጌታ ውለታው ጋር ከቀኑ 8 ሰአት እስከ ምሽቱ 2 ሰአት የደረሰ እጅግ ሰላማዊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን በእለቱ ከክቡራን ሚንስትሮቹ የማይጠበቅ ተግባር ተፈፀመ፡፡ ይኸውም ውይይቱ ሳይጠናቀቅ እና ተወካዮቹ ለመግሪብ ስግደት ለጥቂት ደቂቃዎች በወጡበት ቅፅበት ለሬዲዮ ፋና ‹‹የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎች መልስ ማግኘታቸውንና ከተወካዮቹም ጋር መግባባት ላይ መድረሳቸውን አወጁ፡፡ ይህም ተብሎ ከፀሎት መልስ የቀጠለው ውይይት ላይ ለተወካዮቹ የተነገራቸው መልስ

1. የመጅሊስ ምርጫ ይካሄዳል ግን መቼ እንደሚካሄድ መናገር አይቻልም፡፡ ነገር ግን ምርጫውን የሚያስፈፅመው አሁን በስልጣን ላይ ያሉት አመራሮች እንጂ ገለልተኛ አስመራጭ አይቋቋም፡፡ ምርጫውም በመስጂድ ደረጃ ሳይሆን በቀበሌ ነው የሚካሄደው፡፡

2. አህባሽን በተመለከተ ከዚህ በፊትም በግዴታ አልተሰጠም አሁንም በግዴታ አይሰጥም ስልጠናው ግን ይቀጥላል

3. አወሊያን መጅሊሱ ማስተዳደር ይቀጥላል፡፡ በቦርድ ይተዳደር የሚለው ተቀባይነት የለውም የሚሉ ነበሩ፡፡

 የተከበራችሁ የሃገራችን ዜጎች ፤ እዚህ ጋር እናንተው ልትፈርዱት የምትችሉት እውነት የትኛው ጥያቄ ይሆን በተጠየቀበት መልኩ መልስ ያገኘው? ነገሩ የእምነት ነፃነት ጉዳይ ነውና ተወካዮቹ ጥያቄዎቹ ተገቢውን መልስ አለማግኘታቸውን፡፡ ማለትም

1. የመጅሊስ ምርጫ በተቻለ ፍጥነት እና በገለልተኛ አስመራጭ አማካኝነት መካሄድ የሚኖርበት ሲሆን ጉዳዩም ሃይማኖታዊ እንጂ ፖለቲካዊ ባለመሆኑ በመስጂድ ሊካሄድ ይገባዋል

2. አህባሽ በራሱ ተቋም እንደ ሌላ እምነት ሊንቀሳቀስ ይገባዋል እንጂ በሙስሊሙ ንብረት በሚተዳደሩ የመጅሊስ መዋቅሮችና መስጂዶች ሊሰጥ አይገባውም

3. አወሊያም በህዝብ በሚመረጡ የቦርድ አባላት ይተዳደር በሚል ለጥያቄዎቹ መልስ አለማግኘቱን ነገር ግን የፌዴራል ጉዳዮች ቢያንስ በጉዳዩ ላይ ለመወያየት ያደረገውን ትብብር አመስግኖ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አንድ የመንግስት እርከን እንጂ የመጨረሻ ባለመሆኑ ጥያቄዎቹን ለቀጣይ የስልጣን እርከን እንደሚየቀርብ በደብዳቤ በማሳወቅ ከፌዴራል ጉዳዮች ጋር የነበረውን ውይይት ቋጨ፡፡

ይህንንም ተከትሎ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በጉዳዩ ላይ ውይይት ለማድረግ ካላቸው ጠባብ የስራ ወቅት ላይ ቀጠሮ እንዲይዙ የሚጠይቅ ደብዳቤ አስገባ፡፡ የውይይት ቀጠሮውን በመጠባበቅ ላይ ባለበት ወቅት ድንገት ሳይታሰብ ያ ሰላማዊ የተባለና በሚዲያ ደረጃ የተወደሰ ጥያቄ እና አቅራቢው ህዝብ ህገ ወጥ፤ ለሰላማዊ አካሄድ ዝግጁነት የሌለው እየተባለ በመግለጫ መብጠልጠል ተጀመረ፡፡ ይሄ በጣም አስደንጋጭ እና ያልተጠበቀ በመሆኑ ለግዜው ግራ ቢያጋባንም ነገሩን በሰከነ መንፈስ በመገምገም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀጠሮ እስኪገኝ በትዕግስት ለመጠበቅ ተወሰነ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩም ቀጠሮ መዘግየትና የአዝማሚያዎች አለማማር ተከትሎ ምናልባት እኛው በሰራነው ወንጀል ኃጢያት ሊሆን ይችላልና አምላክ ይምረን ዘንድ ምፅዋት እንስጥ በሚል ህዝቡ ገንዘቡን እያዋጣ ለነዳያንና ለህዝብ ሰደቃ በማዘጋጀት የፀሎት ፕሮግራሞች በመላ ሃገሪቱ መካሄድ ጀመሩ፡፡ እነዚህ የሰደቃ ፕሮግራሞች ህዝብ በልቶ፤ ፀልዮ እና በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ የሚለያይባቸው እንጂ ምንም አይነት የረብሻም ሆነ የአመፅ አካሄድ ያልተስተዋለባቸው ነበሩ፡፡ ለዚህ ደግሞ በስፍራው የተገኙ የፀጥታ ሃይሎች ሳይቀሩ ሊመሰክሩ ይችላሉ፡፡ የዚሁ አካል የሆነውና በአዲስ አበባ አወሊያ ሊካሄድ የታሰበው የሰደቃ (ምፅዋት) ፕሮግራም ለሃምሌ ስምንት ተቀጥሮ የእርድ ሰንጋዎች ገብተውና የማብሰያ ቁሳቁሶች ተዘጋጅተው አርብ ለቅዳሜ ሌሊት ምግብ ለመስራትና ግቢ ለማሰናዳት ከመሰጂድ ባደሩ ምእመናን ላይ ያልታሰበና ለምን እንደተደረገ ያልታወቀ ድንገተኛ ተኩስ ተከፍቶ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሲቆስሉ እስከአሁን የት እንደደረሱ ያልታወቁም ይገኛሉ፡፡ ቀሪዎቹን ለመክተፊያ ይጠቀሙበት የነበረውን ቢላዋ እያስያዙ በግድ በመቅረፅ ወደ እስር ቤት ወረወሯቸው፡፡

አንድ አደጋ ሲከሰት መስጂዶች አዛን ማድረግና ቤተክርስቲያኖች ደወል መደወል የተለመደ እንደመሆኑ በእለቱ በከተማው የሚገኙ በርካታ መስጂዶች አዛን አሰሙ፡፡ ይህንንም ተከትሎ በርካታ ምእመናን ወደመስጂድ ለፀሎት ሲተሙ በየአካባቢያቸው ተኩስ እየተከፈተ፤ አስለቃሽ ጭስ እየተተኮሰ እና ህዝቡ በዱላ እየተደበደበ እጅግ አሳዛኝ ሌሊት አነጋ፡፡ እንዲህም ሆኖ ግን ህዝቡ ተቃውሞውን ቅዳሜ እና እሁድ የገለፀው በአንድ ግቢ ውስጥ በመወሰን የማንንም መብት ሳይነካ በሃዘንና በለቅሶ ብቻ ነበር፡፡ ይህም ሆኖ በመንግሰስት መገናኛ ብዙሃን የተላለፈው ዜና ግን ህዝብን ሽምጥጥ አድርጎ የካደ እና የሚያሳዝን ሆነ፡፡ እንግዲህ ይህችን የሰደቃ ፕሮግራም ተከትሎ ነው ነገሮች ከመቅፅበት የተቀያየሩት፡፡ ሰላማዊነታቸው የተወደሰው የኮሚቴ አባላት እንደሽፍታ እየታደኑ ተይዘው ኢ ሰብአዊ የሆነ አያያዝ ስር ይገኛሉ፡፡ ሌሎች ሰባኪያንና የሃገር ሽማግሌዎችም ተመሳሳይ እጣ ፈንታ ገጥሟቸዋል፡፡ ይህንን መሪር ሃዘን ለመግለፅ በአንዋር መስኪድ የተሰበሰቡ በአስር ሺዎች በሚቆጠሩ ምእመናን ላይ ነው የሰሞኑ የሚዲያ ሽፋን የሆነው የጅምላ እስራትንና ድብደባ ያስተናገደው ክስተት የተፈጠረው፡፡ ይኼኛውም እንደሌሎቹ በመስጂድ ቅጥር ግቢ በተሰባሰቡ ምእመናን ላይ የተከፈተ ጥቃት እንጂ ህዝብ ለአመፅ የተነሳሳበት አካሄድ አልነበረውም፡፡ አይኖረውምም፡፡ 

የተከበራችሁ የሃገራችን ዜጎች እኛ እየጠየቅን ያለነው ግልፅ፤ ቀላል እና ንፁህ የሃማኖት መብት ጥያቄ ነው፡፡ ጥያቄዎቹ ማንም እንደፈለገው ዳግም አቡክቶ ቢጋግራቸው ሌላ ምንም ሊወጣቸው አይችሉም፡፡ ግልፅ ጥያቄአችንን በሃይል በመጠምዘዝ ፖለቲካዊ ይዘት ለማላበስ በመንግስት የሚደረገው ጥረት ምክንያቱ ባይገባንም ጥያቄአችን ንፁህ የመብት ጥያቄ ብቻ መሆኑን አሁንም ለመግለፅ አንደክምም፡፡ የፖለቲካ ጥያቄ ነው ያላቸው፤ እስላማዊ መንግስት ለማቋቋም ነው—-በሚል የሚነዙት ውሃ የማይቋጥሩ ተራ ወሬዎች ተናጋሪውን ከማቅለል ያለፈ ትርጉም የላቸውም፡፡ ይህንን ተራ አሉባልታ ለማጠናከር በሚልም ተደጋጋሚ ድራማዎችና በዘጋቢ ፊልም ስም የሚቀርቡ ውዥንብሮች ተበራክተዋል፡፡ በቀጣይም ይበልጥ ተጠናክረውና የህዝብ ለህዝብ አንድነትን ሊንዱ በሚችሉ መልኩ ተቀናብረው ሊቀርቡ እንደሚችሉ በብዙ ይጠበቃል፡፡ እኛም የሚነዙብን አሉባልታዎችን ወደ ጎን በመተው ከላይ የዘረዘርናቸውን ግልፅ ጥያቄዎቻችን እንዲመለሱ እና በመቶዎች የሚቆጠሩ የታሰሩ የእምነት ወነድሞቻችን እስኪፈቱ ሰላማዊ ትግላችንን እንደምንቀጥል ስንገልፅላችሁ የጥያቄአችንን ግልፅነትና ከፖለቲካ ንፁህነት እንደከዚህ ቀደም እንድትረዱልን በመጠየቅ ነው፡፡ 

ይህ ለመነሻ ግንዛቤ ያህል እንዲረዳ በማሰብ የተዘጋጀ እንጂ ዝርዝር ሃሳቦችን አለመያዙን እንረዳለን፡፡ በቀጣይ ሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ እንደምንፅፍ እየገለፅን አጠቃላይ ሂደቱን በይበልጥ ለመረዳት የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው ያሳተመውን ‹‹እውነቱ ይህ ነው›› የሚለውን መፅሃፍ እንዲያነቡ እንጋብዛለን፡፡

አምላክ ሃገራችንንም ዜጎቿንም ሰላም ያድርግልን

ይቸን ባሮም ሶሬሳ 

ይድረስ ለኢትዮጵያዊያን በሙሉ በያላችሁበት

Reblogged from Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት :

ጉዳዩ – በወያኔ እስር ቤቶች ሞልቶ ስለፈሰሰው የወገኖቻችሁ ስቃይና ሰቆቃ እንድታውቁት …

1. ትንሽ ስለ ራሴበወያኔ የወንጀል ምርመራ፣ የወህኒና የእስር ቤቶች አስተዳደር አካባቢ የምሰራ የፖሊስ፣ የፌደራልና የደህንነት ባልደረባ ነኝ። ባጭሩ እንድታውቁት የምፈልገው በሃገሪቱ እስር ቤቶችና ማእከላዊ እየተባለ......

Read more… 27 more words

የኦሮሞ ልጆችን እያፈሱ የሚከቱት ግን ኦነግን ፍራቻ ብቻ ነው?

Reblogged from Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት :

Click to visit the original post

በቢሾፍቱ ደብረዘይት በተከበረው የእሬቻ በአል ላይ ወያኔ ያፈናቸውን ወጣቶች እንዳለቀቀ እንዲሁም እስካሁን ፍርድ ቤት እንዳላቀረባቸው የውስጥ አዋቂ ምንጮች ገለጡ::የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ቀሳቃሽ እና አስተባባሪ  ናቸው በሚል ሰበብ የታሰሩት ዜጎች ተመርጠ...ው ከህዝብ መሃል ታፍሰው የተወሰዱ እንደነበር ተዘግቦ ነበር:;ይህን ተከትሎ የታሰሩትን ሰዎች ትፈታላቹ ከወጣቶቹ ጋር ከጀርባ ትተባበራላቹ በሚል የኦሮሚያ እና የፌዴራል ፖሊሶችም የታሰሩ ሲሆን ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ለ6 ወራት በእስር ቤት እየተንገላቱ መሆኑን ከቢሾፍቱ ደብረዘይት የመጡ መረጃዎች ጠቁሟል::     posted by Issa Abdusemed…

Read more… 21 more words

የኢትዮጵያ ህዝብ በምርጫ ስም በሚደረጉ ድራማዎች መሰላቸቱን ገለፀ

Reblogged from Ethio Andinet ኢትዮ አንድነት :

Click to visit the original post

ምርጫ የዴሞክራሲያዊ ስርአት መገለጫ ቢሆንም ምርጫን ያካሄደ መንግስት ሁሉ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ገንብቷል ለማለት አያስችልም፡፡ በተለያዩ የአለም ክፍሎች የሚገኙ አምባገነን መንግስታት እንደሚያደርጉት ሁሉ ኢህአዴግም....

በሀዲያ ዞን የፍትህ ስርዓቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለፀ


Bisrat Woldemichael

በሀዲያ ዞን ያለው የፍትህ ስርዓት የህዝብ አመኔታ እያጣ በመምጣቱ  ወደፍርድ ቤቶች ከመሄድ የሽምግልና ስርዓትን እንደሚመርጡን ባለው የፍትህ ስርዓት መዳኘት እንደማይፈልጉ ምንጮቻችን ከስፍራው ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡ከዚህ ጋር በተያያዘ በተለይ የሌሞ ወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት  ህግ ከማስከበር ይልቅ የህግ ጥሰት በመፈፀም በደል ያደረሱብኝ የወረዳው ፍርድ ቤት ዳኛም አንዱ ናቸው የሚል ጥቆማ ተሰምቶ ጉዳዩ ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስነስርዓት ጉዳይ ላይ እንዲታይ አቤቱታም መቅረቡን ከዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንትና ምክትል ፕሬዘዳንት ማረጋገጥ ችለዋል፡፡

በተለይ  በሌሞ ወረዳ ሲታይ የነበረው በመዝገብ ቁጥር 06066  በወይዘሪት ቤተልሔም ወልደመስቀል እና በአቶ ጌትነት በላቸው በተባሉ ግለሰቦች መካከል በሆሳዕና ከተማ ጎፈር ሜዳ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ሄሜ ኢንተርናሽናል ሆቴል አጠገብ በሚገኝ 400 ካሬ ሜትር ላይ ያለው ቤትና ቦታ ወራሽነት ይገባኛል በሚል በሚደረገው ክርክር ላይ የካቲት 26 ቀን 2005ዓ.ም.  በዳኛ ወ/ዮሐንስ  ለውሳኔ መዘጋጀቱ ተጠቁሟል፡፡ይሁን እንጂ ጉዳዩ የማይመለከታቸው በወረዳው ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት አቶ ተስፋዬ ሰጦሬ ተነጥቆ ውሳኔው እንዲስተጓጎል በማድረግ ህግ ተላልፈዋል በሚል ለከፍተኛ ፍርድ ቤት አቤቱታ ቀርቦባቸው በፕሬዘዳንቱ  የተነጠቁት ዳኛ ወ/ዮሐንስ አይተው ውሳኔ እንዲሰጡ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተላለፈው  መሰረት የክሱ  መዝገብ  መጋቢት 11 ቀን 2005ዓ.ም. ውሳኔ መሰጠቱ ታውቋል፡፡ ነገር ግን በተደረገው  ክርክር ላይ “ወራሽ ነኝ ያሉት ግለሰብ አቶ ጌትነት በላቸው እስካሁን በአካል ያልቀረቡና በወራሽነት ያለችውን ግለሰብ መብት ለማሳጣት  የወረዳው ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት ሆን ብለው ከህግ አግባብ ውጭ በማይመለከታቸው ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ተከራካሪ  ወገኖችን እያጉላሉ ነው” በሚል በተደጋጋሚ ቅሬታ ቀርቦባቸው እንደነበር ተጠቁሟል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው ውሳኔ የሰጡት ዳኛ ወልደዮሐንስ ሐንዲሶ “በርግጥ የህግ ስርዓትን ያልተከተለ ትዕዛዝ መጥቶ አላይም ብዬ በኋላ የወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት አቶ ተስፋዬ ጋር ከተወያየን በኋላ ማየት እንዳለብኝ ሲነገረኝ አይቼ ለውሳኔ በተዘጋጀሁበት ወቅት ተቃውሞ በመቅረቡ ውሳኔ ሳልሰጥ ቀርቻለሁ እንጂ አልተነጠኩም፡፡ ነገር ግን ጉዳዩን የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከመረመረ በኋላ ውሳኔውን እኔ እንድሰጥ በመደረጉ በድጋሚ አይቼ ውሳኔውን ሰጥቻለሁ ” ብለዋል፡፡ የወይዘሪት ቤተልሔም  ጠበቃ አቶ ተካልኝ ጴጥሮስ በበኩላቸው “ጉዳዩን የህግ ስርዓት ያልተከተለ አሰራር በወረዳው ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት አሰራር ላይ ቅሬታ ስላለን አቤቱታችንን የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማረም ችሎ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን የወረዳው ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት በማይመለከታቸው ጉዳይ እንደ ፍትህ አካል ሳይሆን እንደባለጉዳይ ከህግ አግባብ ውጭ እየተንቀሳቀሱና እያስፈራሩ  በመሆኑ አሁንም ለሚመለከተው አካል ቅሬታችንን አቅርበን ውሳኔ እየጠበቅን ነው” ሲሉ  ገልፀዋል፡፡

በደል ፈፅመዋል የተባሉት የወረዳው ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት አቶ ተስፋዬ ሰጦሬ በበኩላቸው “እኔ ከችሎት ላይ የነጠኩት የውሳኔ መዝገብም የለም፣ ሊኖርም አይችልም፤ እንዲህ ዓይት አሰራር ከዛሬ 20  እና 25 ዓመታት በፊት እንጂ በዚህ ስርዓት የለም፡፡ በዳኞች ላይ ተቃውሞ ሲቀርብ ግን በህግ አግባብ እንዳይታይ አድርጌ ነበር፤ በመጨረሻ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በሰጠው ብይን መሰረት ጉዳዩን የያዙት ዳኛ ወ/ዮሐንስ ውሳኔ እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡ አስፈራርተሃል የተባለውን በተመለከተ የስም ማጥፋት ዘመቻ ነው እንጂ ያስፈራራሁት አካል የለም” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ለማ ገ/እግዚአብሔር  በበኩላቸው ጉዳዩ ውስብስብ ቢሆንም በወረዳው ህጋው አሰራርን ያልተከተለ አሰራር ነበር ፤ በኋላ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ጉዳዩን አይቶ እርማት ሰጥቶ ቀደም ሲል የያዙት ዳኛ ውሳኔ እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡ ይሁን እንጂ አሁን በይግባኝ ጉዳዩ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ደርሶ እየታየ ይገኛል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በተለይ ከጉዳዩ ጋር እጃቸው እንዳለበት የሚጠረጠሩት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት አቶ ግርማ አበበ ከህግ አግባብ ውጭ የወራሽነት መብት ላይ እግድ ጥለዋል ከሚል ቅሬታ በተጨማሪ ከወረዳው ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት ጋር የጥቅም ትስስር ስላላቸው ጉዳዩ ላይ እግድ ጥለዋል የሚል ቅሬታ እንዳለባቸው ተጠቁሟል፡፡ አቶ ግርማ በበኩላቸው “እግድ የጣልኩት  ንብረት እንዳይሸጥና እንዳይለወጥ እንዲሁም ለሶስተኛ ወገን ተላልፎ እንዳይሰጥ እንጂ የወራሽነት መብት ላይ እግድ አልጣልኩም” ሲሉ  ለፍኖተ ነፃነት ገልፀዋል፡፡ በመጨረሻም የአቶ ጌትነትን ጠበቃ አቶ ኤርጃቦን ለማናገር ጥረት ብናደርግም አልተሳካም፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሌሎች በርካታ የፍትህ መጓደል በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ላይ እንደሚስተዋልና የአንዳንድ ዳኞች ሹመትም ቢሆን ከሙያ ብቃትና አገልግሎት ይልቅ የጎሳ ዝምድና ትስስር ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ተጠቁሟል፡፡ በዚህ ዙሪያ የዞኑ ፍትህ ጽህፈት ቤትን ምላሽ ለማግኘት ተደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም አልተሳካም፡፡

ኢህአዴግ ብቻውን እየተወዳደረም ህገወጥ ስራ እየሰራ መሆኑ ተገለፀ


በአዲስ አበባ የሚገኙ ባለሃብቶች “ኢህአዴግ ለሚያዚያ 2005 ዓ.ም. ለሚደረገው የአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ አስተዳደርና የአካባቢ ምርጫ ብቻውን እየተወዳደረም ለምርጫ ቅስቀሳ በሚል በግዳጅ ገንዘብ እየጠየቀ ህገወጥ ድርጊት እየፈፀመ እንደሆነና ድርጊቱም እንዳማረራቸው ለአዲስ ሚዲያ ገለፁ፡፡ “በተለይ እኛ ሳንፈልግ ለኢህአዴግ ምርጫ ቅስቀሳ የሚሆን ገንዘብ አዋጡ የሚል እደምታ ያለውና የመንግስት መስሪያ ቤት ማኀተም ያረፈበት አስገዳጅ ደብዳቤ በየድርጅታችን ስም እየላኩ የመኖርና የመስራት ነፃነታችንን እየተጋፉ ነው “ ሲሉ ቅሬታ የተሰማቸው ያነጋገርናቸው ነጋዴዎች ለአዲስ ሚዲያ ጠቁመዋል፡፡

በተለይ በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት መጋቢት 20 ቀን 2005ዓ.ም. በወረዳው ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ጽህፈት ቤት ማኀተም ባረፈበትና የወረዳው ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የስልክ አድራሻን በመጠቀም የተላከው ደብዳቤ “…ባለድርሻ አካላት” ላላቸው “የኢህአዴግ አባላት፣ አጋር ድርጅቶች፣ታዋቂ ካምፓኒዎች፣ ሪል ስቴቶች፣ ግለሰቦች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት” በሚል ከተላከው አስገዳጅ ደብዳቤ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በተላከው ደብዳቤ ማጠቃለያ ላይ አስገዳጅነቱን በግልፅ በሚያሳይ ማስፈራሪያ “የዚህ ፕሮግራም ማጠቃለያ የሚሆነው ለሚመለከተው አካል ጊዜውን የጠበቀ ዘገባ ማድረግ ይሆናል፡፡ ከዚህ በመነሳት ኢህአዴግን መምረጥ የሀገራችንን ህዳሴ ወደ ሌላ ምዕራፍ ማሸጋገር ስለሆነ አገረ ባለሃብቶችና ጥያቄ የቀረበላችሁ አካላት አስፈላጊውን ታደርጉ ዘንድ ማሳወቅ ነው::” በሚል ከፈቃደኝነት ይልቅ አስገዳጅነት ያለው ደብዳቤ በመላክ ምላሽ እንድንሰጣቸው ይጠይቁናል ሲሉ ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉ ባለሃብቶች ከተደገፈ መረጃ ጋር አስታውቀዋል፡፡

በዚህም ምክንያት ኢህአዴግ ብቻውን ሆኖ ይህን ህገወጥ ድርጊት መፈፀሙ የከዚህ በፊቱ ልምዱን ነው የሚያሳየው፣ ይህ አዲስ አይደልም፤ እንደውም ይባስ ብሎ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንኳ የእሱ አጋር መሆናቸውን መግለፁ ኢህአዴግ ህገወጥ ስራ መስራቱን የሚያረጋግጥ ነው ሲሉ ያነጋገርናቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገልፀውልናል፡፡

ይህንንም በሚመለከት ምርጫ ቦርድ ምን ይላል የሚለውን ለማረጋገጥ ጥረት ብናደርግም ለጊዜው አልተሳካም፤ ከዚህ በተጨማሪ በመንግስት ማኀተምና አድራሻ የኢህአዴግ ምርጫ ቅስቀሳ ደብዳቤ በትነዋል ከተባሉት መካከል በአዲስ አበባ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ስለሺ ካሳ መልስ እንዲሰጡን ብንሞክርም ያልተሳካ ሲሆን በወረዳው የመንግስት ቢሮ ውስጥ የህዝብ አደረጃጀት ኃላፊ በህዝብ ደመወዝ የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ስራን የሚሰሩት አቶ በረከት ዮሐንስ በበኩላቸው እኛ እንዲህ አላደረግንም ቢሉም ሰነዱ ግን በዝግጅት ክፍላችን የሚገኝ ሲሆን ቅጂው ለምርጫ ቦርድ ህዝብ ግንኙነት ክፍል እንደደረሰም ተጠቁሟል፡፡ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ዋና ፀሐፊ አቶ ወንድሞ ጎላ በበኩላቸው ከላይ የተጠቀሰው ድርጊት ተፈፅሞ ከሆነ የእርምት እርምጃ እንወስዳለን ፤ መረጃውን ግን እስካሁን አላየሁትም ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

CPJ expresses grave concern over the deteriorating health conditions of Reeyot Alemu


The New York-based Committee to Protect Journalists (CPJ) has expressed concern about the safety of Reeyot Alemu, a jailed Ethiopian journalist and teacher.

In a protest letter to Birhan Hailu, Ethiopia’s justice minister, Joel Simon, CPJ’s Executive Director asked that Alemu, whose health has reportedly deteriorated since being held on terrorism charges, to withdraw the threat of placing her in solitary confinement.
Human rights and press freedom groups have long accused Addis Ababa of using its controversial terrorism legislation to curb opposition and stifle the media in the East African nation.
“Prison authorities have threatened Reeyot with solitary confinement for two months as punishment for alleged bad behavior toward them and threatening to publicize human rights violations by prison guards” said CPJ’s letter, which was published on its website.
Despite pledges to the contrary Ethiopia’s Ministry of Justice has failed to ensure that Reeyot’s full human rights have not been violated during her detention, which began in June 2011.
“We urge you to fulfill Ethiopia’s promise to build a humane and democratic state by withdrawing the threat of solitary confinement against Reeyot and ensuring her access to adequate medical care” CPJ said.
“No journalists should face detention or imprisonment in the exercise of their duty”
Reeyot, a columnist for the now-defunct independent weekly Feteh, is being held of the basis of accusation that she was involved in a vague terrorism plot.
In January 2012 she was sentenced her to 14 years in prison under the country’s anti-terrorism law however an appeals court later in August, reduced the initial sentence to five years after the court dropped most of the terrorism charges pressed against the journalist, who is known for writing columns critical of the government.
CPJ has also expressed grave concern over the deteriorating health conditions of Reeyot saying she has been denied of access to adequate medical treatment after she was diagnosed with a tumor in her breast.
Reeyot is a 2012 winner of the International Women’s Media Foundation Courage Award.
International human right groups accuse Ethiopia of using the country’s broadly defined anti-terrorism law to punish critical journalists and opposition members, an allegation Addis Ababa denies.
In 2011 the United Nations special rapporteur on torture, Juan E. Méndez, urged the prohibition of “the imposition of solitary confinement as punishment – either as part of a judicially imposed sentence or a disciplinary measure.”
In the report the special rapporteur urged Ethiopia to fulfill its obligation as signatory to the United Nations Convention against torture and other cruel, inhuman or degrading treatment or punishment.
Source: Sudan Tribune

ከኮለኔል መንግስቱ እና ከአቶ መለስ ለኢትዮጵያ ሕፃናት አባት በመሆን ፋውንዴሽን ሊመሰረትለት የሚገባው ማነው?


”ጎዳና ቤቴ’

ሰኔ 25/2012 እአአቆጣጠር  በቢቢሲ ድህረ ገፅ ላይ በወጣ አንድ ዘገባ መሰረት ኢትዮጵያ በአመት 5ሺህ በላይ ሕፃናት በማደጎነት ወደ አሜሪካ  ብቻ እንደሚሄዱ  እና አሜሪካ ከዓለም ላይ በማደጎነት ከምትወስደው ሕፃናት ኢትዮጵያውያን ሕፃናት ከ አምስቱ አንዱ እንደሆኑይገልፃል።(http://www.bbc.co.uk/news/world-africa-18506474)

አዲስ አበባ ብቻ ዛሬ ከ አንድ መቶ ሺህ በላይ መግብያ ያጡ ”ጎዳና ቤቴ” ብለው አንቅልፍ በጣላቸው ቦታ ክልውስ ብለው የሚተኙ ሕፃናት ይኖሩባታል።ይህ የሆነው የኢትዮጵያ መንግስት ግዴለሽነት የመነጨ እንጂ ከድህነታችን ብቻ የሚመስለው ካለ ለመሳሳቱ እማኝ ላቅርብ።
ሕፃናት አሳዳጊ የሚያጡት ባብዛኛው የርስበርስ ጦርነት ሲኖር ወይንም ሰላም በተናጋበት ጊዜ ነው።ኢትዮጵያ ግን ጎዳና የወጡት ሕፃናቶቿ የበዙት በአንፃሩም ቢሆን ጦርነቱ ከቆመ ጊዜ ጀምሮ ነው ለምን?
በ 1969 ዓም በዚያድባሬ ሱማሌ ወረራ ሳቢያ ብዙ ሕፃናት አባት እናታቸውን አጡ።ሀገሪቱ በወቅቱ ገንዘብ የላትም።ምዕራባውያን ፊታቸውን አዙረውባት ነበር።ግን ሕፃናት ጎዳና አልተጣሉም ይልቁንም ኃላፊነት የተሰማቸው ኮለኔል መንግስቱ በ 16 ወራት ውስጥ የሕፃናት አምባ እንዲገነባ አድርገው በአንድ ጊዜ ከአምስት ሺህ ሕፃናት በላይ የሚይዝ ትልቅ የሕፃናት ማሳደግያ በአፍሪካ በግዙፍነቱ (በውቅቱ) እና በአቅሙ ቀዳሚ  ሆኖ ተገንብቷል። ኢህአዲግ መንግስት ከሆነበት ጊዜ  ጀምሮ ሲያዳክመው ቆይቶ በ 1990 ዓም ተዘጋ። ኢህአዲግ ወያኔ የነበረውን አስፋፍቶ ሕፃናትን ከጎዳና ኑሮ ከማዳን ይልቅ ሕፃናትን በማደጎነት እየሸጠ በአንድ ሕፃን በትንሹ 25ሺህ ዶላር መሰብሰብ እና ወደኪሱ  ማስገባቱን መረጠ።

ከኮለኔል መንግስቱ እና ከአቶ መለስ ለኢትዮጵያ ሕፃናት አባት በመሆን ፋውንዴሽን ሊመሰረትለት የሚገባው ማነው?

ዛሬ ኮለኔል መንግስቱ እንደጀመሩት ቢቀጥል ኖሮ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሕፃናት በተማሩበት እና ከጎዳና ኑሮ በዳኑበት ነበር። ሃቁ ይህ ነው።አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ላይ የተሰቀለው ቢል ቦርድ እና ኢቲቪ በአቶ መለስ የሞቱ ሰሞን ከዜና አንባቢው ጀርባ አቶ በለስ ጣታቸውን ወደ ሕፃናት ሲዘረጉ ያሳያል።ግን  እንዴት ነው አቶ መለስ የኢትዮጵያ ሕፃናት አባት የሚባሉት? በምን መስፈርት? ሕፃናቱን ጎዳና ወድቀው እሳቸው በሚያልፉበት መንገድ በወታደሮቻቸው ስለገፏቸው ነው?ወይንስ የሕፃናት አምባን ስለዘጉላቸው? ነው ወይንስ በአስር ሺዎች በማያውቁት ባእዳን እጅ እንዲያድጉ ስለሸጧቸው። ‘መሸጥ’ የሚለው ቃል ለቀረበው ዕቃ ወይም ሰው አልያም ሕፃናት ገንዘብ ከፍሎ ሕፃኑን መውሰድ የሚለውን ትርጉም እስከያዘ ድረስ መሸጥ ከሚለው ቃል የትሻለ ሊገኝ አይችልም።

ቅዳሜ ጧት

ከአምስት አመት በፊት በ 2001ዓም አንድ ቅዳሜ ጧት ወደ ዝዋይ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም 45 ሰዎችን አሳፍሮ አንድ መለስተኛ አውቶቡስ መመናንን ይዞ መንገድ ላይ ነበር።በመንገድ ላይ በእድሜ ጎልማሳ ካህን ስለገዳሙ ታሪክ ይናገራሉ።በአንክሮ በመገረም ነበር የምንሰማው።እውነተኛ ታሪኩ ይህ ነበር።
” አቡነጎርጎርዮስ የዝዋይ ገዳም መስራች አንድቀን የመንፈስ ልጆቻቸውን እያስተማሩ ኮለኔል  መንግስቱ ከአዋሳ ሲመጡ ጎራ ይላሉ።ወደ ገዳሙ ውስጥ ሳይገቡ ገና አጥሩን ሲመለከቱ በረጅሙ ታጥሮ ይመለከቱ እና ‘ይሄ መነኩሴ ይህን ይህል ቦታ አጥሮ አገሩ ታድያ ምን ተረፈ’ ይሉ እና አንዱን ወታደር አቡነ ጎርጎርዮስን እንዲጠራቸው ይልኩታል። አቡነ ጎርጎርዮስ መልክቱ እንደደረሳቸው ‘አሁን ትምህርት ላይ ነኝ ደግሞስ ፈላጊ ይመጣል እንጂ ተፈላጊ እንዴት ይሄዳል?’ ብለህ ንገረው ብለው መልሰው ይልካሉ።ኮለኔል መንግስቱ እንዲህ አይነት ድፍረት በመስማታቸው ምንም ሳይሉ ወደ አዲስ አበባ ይመለሳሉ። በቀጣዩ ቀናት አቡነ ጎርጎርዮስ ኮለኔል መንግስቱን ቅሬታቸውን ለመንገር ይመጣሉ።ቅሬታቸው ሌላ ነበር።እንደገቡ አቡነ ጎርጎርዮስ በቁጣ ”ለመሆኑ ሕፃናት አምባ የምታሳድጋቸው ልጆች አምላካቸውን ካላወቁ አውሬ እንደሚሆኑ ታውቃለህ?” ይሉታል ይደነግጣል። ”ምን ይደረግ?” ይላቸዋል።”ለእኔ ፍቀድልኝ እኔ የማደርገውን አውቃለሁ ” ይሉታል። ከድጋፍ ደብዳቤ ጋር ይልካቸዋል።
አቡነ ጎርጎርዮስ በህፃናት አምባ ውስጥ የቅዱስ ሚካኤል ታቦት አስይዘው በግቢው ውስጥ ለሕፃናቱ ቤተክርስቲያን ሰሩላቸው።ብዙ በስነምግባራቸው የታነፁ ሕፃናትን አፈሩ። በቀን በሚልዮን ብር ለጦርነት ታወጣ የነበረች ሀገር እንዲህ ልጆቿን ታሳድግ ነበር። ዛሬ የጎዳና ተዳዳሪ ሲበዛ መንግስት ኃላፊነት አይወስድም።ሕፃናቱን ለመሸጥ ግን ቢሮዎችን በየቦታው ባእዳን እንዲከፍቱ አርጎ የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ አደረጋቸው። ቢቢሲ ከላይ በጠቀስኩት ቀን ላይ ባወጣው ዘገባ ላይ እንዲህ ይላል።
”International adoption is big business in Ethiopia and the country accounts for almost one in five international adoptions in the US, but how ethical is the process?” http://www.bbc.co.uk/news/world-africa-18506474
”በኢትዮጵያ የማደጎ ሕፃናትን ወደውጭ መላክ የንግድ ሥራ ሆኗል።ይህም ወደአሜሪካ ከመላው አለም ከሚገቡት ውስጥ ከአምስቱ አንዱን እጅ ይይዛሉ።ነገር ግን ይህ እንዴት ሞራላዊ ሂደት ሊሆን ይችላል?” በማለት ይጠይቃል። እውነት እንዴት ሞራላዊ ሂደት ሊሆን ይችላል?
ግን ከኮለኔል መንግስቱ እና ከአቶ መለስ ለኢትዮጵያ ሕፃናት አባት በመሆን ፋውንዴሽን ሊመሰረትለት የሚገባው ማነው?
ይህንን በ ኮለኔል  መንግስቱ የተመሰረተውን ታሪካዊ የሕፃናት አምባ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ፊልም ይመልከቱ እና ኃላፊነት የሚሰማው መንግስት ስጠን በሉ።

ቅዳሜ ጧት

ከአምስት አመት በፊት በ 2001ዓም አንድ ቅዳሜ ጧት ወደ ዝዋይ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም 45 ሰዎችን አሳፍሮ አንድ መለስተኛ አውቶቡስ መመናንን ይዞ መንገድ ላይ ነበር።በመንገድ ላይ በእድሜ ጎልማሳ ካህን ስለገዳሙ ታሪክ ይናገራሉ።በአንክሮ በመገረም ነበር የምንሰማው።እውነተኛ ታሪኩ ይህ ነበር።

” አቡነጎርጎርዮስ የዝዋይ ገዳም መስራች አንድቀን የመንፈስ ልጆቻቸውን እያስተማሩ ኮለኔል  መንግስቱ ከአዋሳ ሲመጡ ጎራ ይላሉ።ወደ ገዳሙ ውስጥ ሳይገቡ ገና አጥሩን ሲመለከቱ በረጅሙ ታጥሮ ይመለከቱ እና ‘ይሄ መነኩሴ ይህን ይህል ቦታ አጥሮ አገሩ ታድያ ምን ተረፈ’ ይሉ እና አንዱን ወታደር አቡነ ጎርጎርዮስን እንዲጠራቸው ይልኩታል። አቡነ ጎርጎርዮስ መልክቱ እንደደረሳቸው ‘አሁን ትምህርት ላይ ነኝ ደግሞስ ፈላጊ ይመጣል እንጂ ተፈላጊ እንዴት ይሄዳል?’ ብለህ ንገረው ብለው መልሰው ይልካሉ።ኮለኔል መንግስቱ እንዲህ አይነት ድፍረት በመስማታቸው ምንም ሳይሉ ወደ አዲስ አበባ ይመለሳሉ። በቀጣዩ ቀናት አቡነ ጎርጎርዮስ ኮለኔል መንግስቱን ቅሬታቸውን ለመንገር ይመጣሉ።ቅሬታቸው ሌላ ነበር።እንደገቡ አቡነ ጎርጎርዮስ በቁጣ ”ለመሆኑ ሕፃናት አምባ የምታሳድጋቸው ልጆች አምላካቸውን ካላወቁ አውሬ እንደሚሆኑ ታውቃለህ?” ይሉታል ይደነግጣል። ”ምን ይደረግ?” ይላቸዋል።”ለእኔ ፍቀድልኝ እኔ የማደርገውን አውቃለሁ ” ይሉታል። ከድጋፍ ደብዳቤ ጋር ይልካቸዋል።

አቡነ ጎርጎርዮስ በህፃናት አምባ ውስጥ የቅዱስ ሚካኤል ታቦት አስይዘው በግቢው ውስጥ ለሕፃናቱ ቤተክርስቲያን ሰሩላቸው።ብዙ በስነምግባራቸው የታነፁ ሕፃናትን አፈሩ። በቀን በሚልዮን ብር ለጦርነት ታወጣ የነበረች ሀገር እንዲህ ልጆቿን ታሳድግ ነበር። ዛሬ የጎዳና ተዳዳሪ ሲበዛ መንግስት ኃላፊነት አይወስድም።ሕፃናቱን ለመሸጥ ግን ቢሮዎችን በየቦታው ባእዳን እንዲከፍቱ አርጎ የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ አደረጋቸው። ቢቢሲ ከላይ በጠቀስኩት ቀን ላይ ባወጣው ዘገባ ላይ እንዲህ ይላል።
”International adoption is big business in Ethiopia and the country accounts for almost one in five international adoptions in the US, but how ethical is the process?” http://www.bbc.co.uk/news/world-africa-18506474
”በኢትዮጵያ የማደጎ ሕፃናትን ወደውጭ መላክ የንግድ ሥራ ሆኗል።ይህም ወደአሜሪካ ከመላው አለም ከሚገቡት ውስጥ ከአምስቱ አንዱን እጅ ይይዛሉ።ነገር ግን ይህ እንዴት ሞራላዊ ሂደት ሊሆን ይችላል?” በማለት ይጠይቃል። እውነት እንዴት ሞራላዊ ሂደት ሊሆን ይችላል?
ግን ከኮለኔል መንግስቱ እና ከአቶ መለስ ለኢትዮጵያ ሕፃናት አባት በመሆን ፋውንዴሽን ሊመሰረትለት የሚገባው ማነው?
ይህንን በ ኮለኔል  መንግስቱ የተመሰረተውን ታሪካዊ የሕፃናት አምባ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ፊልም ይመልከቱ እና ኃላፊነት የሚሰማው መንግስት ስጠን በሉ።